AM/Prabhupada 0093 - ብሀገቨድ ጊታም እራሱ ክርሽና ነው፡፡

Revision as of 17:33, 1 October 2020 by Elad (talk | contribs) (Text replacement - "(<!-- (BEGIN|END) NAVIGATION (.*?) -->\s*){2,15}" to "<!-- $2 NAVIGATION $3 -->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Lecture on Brahma-samhita, Lecture -- Bombay, January 3, 1973

ሽሪማድ ብሀገቨታም የተባለው መፅሀፍ የቬዳንትራ ሱትራ ስነፅሁፍ ዋነኛው ገለፃ ነው፡፡ በዚህም በቬዳንትራ ሱትራ ገለፃ ወይንም በሽሪማድ ብሀገቨታም መፅሀፍ ውስጥ እንደተገለፀው "ጃንማዲ አስያ ያታሀ አንቫያት ኢታራታስ ቻ አርትሄሹ አብሂግናሀ ቴኔ ብራህማ ህርዳ አዲ ካቫዬ ሙህያንቲ ያትራ ሱራያሀ (SB 1.1.1)" እንደዚህ የመሰለ ገለፃ በመፅሀፉ ውስጥ ይገኛል፡፡ ስለዚህ "አዲ ካቪ" አዲ ካቪ ማለት ብራህማ ማለት ነው፡፡ ብራህማ "አዲ ካቪ" ነው፡፡ እንዲሁም "ቴኔ ብራህማ" ብራህማ ማለት "ሻብዳ ብራህማን" ወይንም የቬዲክ ስነፅሁፍ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን እውቀት ወደ ብራህማ ልብ አስተላለፈ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ቁሳዊ ዓለም በመጀመሪያ ሲፈጠር የነበረው ፍጡር ጌታ ብራህማ ብቻ ነበረ፡፡ እርሱም ከፍጥረታት ሁሉ የመጀመሪያው ነው፡፡ ስለዚህ ልንጠይቅ የሚገባው ነገር ቢኖር "ይህ ጌታ ብራህማ በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን የቬዲክ እውቀት እንዴት ለመማር ቻለ?" ለዚህም "ቴኔ ብራህማ" ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ ብራህማ "ብራህማ" ማለትም የቬዲክ እውቀት ማለት ነው፡፡ "ሻብዳ ብራህማን" ገለፃው ወይንም የዓብዩ ጌታ መረጃም "ብራህማን" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ብራህማን ፍፁም ነው፡፡ በብራህማን እና ስለብራህማን በሚገለፅ ስነፅሁፍ ምንም ልዩነት የለም፡፡ እንደዚህም ሁሉ በብሀገቨድ ጊታ የተቀደሰው መፅሀፍ እና በተቀደሰው የዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና በመሀከል ምንም ልዩነት የለም፡፡ ብሀገቨድ ጊታ እራሱ ከክርሽና ተነጥሎ አይታይም፡፡ ይህ ካልሆነማ እንዴ ይህ መፅሀፍ ሊሰገድለት ይችላል? ይህም የሚሰገድለት ከ5000 ዓመታት ጀምሮ ነው፡፡ ታድያ ይህ ብሀገቨድ ጊታ ክርሽና ራሱ ካልሆነ እንዴት ሊሰገድለት ይችላል? በዚህ ዓለም ላይ ብዙ ስነፅሁፎች እና መፅሀፎች ይታተማሉ፡፡ ቢሆንም ግን ከአንድ፣ ከሁለት ወይንም ከሶስት ዓመታት በኃላ ማንም ሰው ስለነዚህ መፃህፍት ግድ አይሰጠውም፡፡ ማንም ሰው ግድ ስለማይሰጠውም ሰዎች ሲያነቧቸው አይታዩም፡፡ በዓለም ታሪክ ላይ ማናቸውንም መፃህፍት ብትወስዱ ለአምስት ሺህ ዓመት የኖረ መፅሀፍ ልታገኙ አትችሉም፡፡ ይህም ማለት በተደጋጋሚ በብዙ ምሁራን፣ የሀይማኖት ተከታዮች እና ፈላስፋዎች እየተነበበ ማለት ነው፡፡ ታድያ ለምን መፅሀፉ እንዲህ ሊሰገደልት በቃ? ይህም ክርሽና ራሱ በመሆኑ ነው፡፡ ክርሽና እንዲሁም በብሀገቨድ ጊታ እና በብሀገቫን ምንም ዓይነት ልዩነት የለም፡፡ “ሻብዳ ብራህማን" ስለዚህ የብሀገቨድ ጊታ መፅሀፍ እንዲሁ በቀላሉ መታየት አይገባውም፡፡ ማንም ሰው ገና ሀ ሁ ሂን አወቀና ስለዚህ መፅሀፍ መረጃ ለመስጠት መቃኘት አይገባውም፡፡ ሞኞች እና ተንኮለኞችም ገና ለገና ትንሽ እውቀት ያዝኩኝ ብለው መረጃ ለመስጠት ይጥራሉ፡፡ ይህም የሚቻል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ”ሻብዳ ብራህማን“ በመሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ እውቀት ሊከሰትልን የሚችለው የሽሪ ክርሽና የፍቅር ትሁት አገልግሎትን መስጠት ስንጀምር ብቻ ነው፡፡ ”ያስያ ዴቬ ፓራ ብሀክቲር ያትሀ ደቬ“ የቬዲክ ትእዛዞች እነዚህ ናቸው፡፡ ”ያስያ ደቬ ፓራ ብሀክቲር ያትሀ ደቬ ታትሀ ጉሮ ታስያይቴ ካትሂታ ሂ አርትሀህ ፕራካሻንቴ ማሀትማናሀ“ (ሽኡ 6 23) እነዚህ የቬዲክ መፃህፍቶች በዓብዩ ጌታ ፀጋ ብቻ የሚገለፁ ናቸው፡፡ አንድ ሰው እውቀት ስላለው ብቻ ሊገለፁለት የሚችሉ አይደሉም፡፡ ማለትም የብሀገቨድ ጊታን መፅሀፍ ልገዛ እችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የቋንቋ ስዋሰው በደንብ ልረዳ የምችል ሆንኩና ብሀገቨድ ጊታን በደንብ ልረዳው እችላላሁ ማለት አይደለም፡፡ “ቬዴሹ ዱርላብሀ” በብራህማ ሰምሂታ ጥቅሶች ውስጥ ቬዴሹ ዱርላብሀ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ ይህም ማለት መላ የቬዲክ ስነፅሁፎችን በስነፅሁፍ ጠቢብነታችሁ ትከታተሉ ይሆናል፡፡ “ዱርላብሀ” ነገር ግን በዚህ ፈለግ ቬዳዎችን ለመረዳት አይቻልም፡፡ “ቬዴሹ ዱርላብሀ” ስለዚህም ብዙ ሰዎች ብሀገቨድ ጊታን በጠቢብነታቸው በማጥናት ትርጉም ሊሰጡት ሲጥሩ ይገኛሉ፡፡ ቢሆንም ግን ማንም ሰው የእነርሱን ትርጉም ግድ ሰጥቶት ሲከታተል አይታይም፡፡ ወይንም አንድ ሰው እንኳን እነዚህን መፃህፍቶች በመከታተል ህይወቱን ለሽሪ ክርሽና የትሁት አገልግሎት ሲሰጥ አናይም፡፡ በቦምቤ ከተማ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ብዙ ሰዎች እናያለን፡፡ እነዚህም ሰዎች ብሀገቨድ ጊታን ለብዙ ዓመታት ሲያስተምሩ ይታያሉ፡፡ ቢሆንም ግን አንድን ሰው እንኳን ወደ ሽሪ ክርሽና አገልጋይነት ሲቀይሩ ዓይተን አናቅም፡፡ ይህ ነው ሚስጥሩ፡፡ ቢሆንም ግን ይኀው ብሀገቨድ ጊታ በአሁኑ ግዜ ልክ እንደተዘመረው በማቅረብ አትመን አቅርበናል፡፡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አውሮፓውያኖች እና አሜሪካኖች ምንም እንኳን ቤተሰባቸው ወይንም ዘር ማንዘራቸው ስለ ክርሽና ሰምተው ያማያውቁ ቢሆኑም እነርሱ ግን የሽሪ ክርሽና ትሁት አገልጋዮች በመሆን ቀርበዋል፡፡ የብልፅግናም ሚስጥሩ ይኅው ነው፡፡ እነዚህ በሞኝነት የተጠቁ ሁሉ ግን እውቀቱ የላቸውም፡፡ ብሀገቫድ ጊታን ሙያቸውን እና እውቀታቸውን በመመካት እና በመተርጎም የመፅሀፉን ሚስጢር ለማስረዳት የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ ግን የሚቻል አይደለም፡፡ “ናሃም ፕራካሽ ዮጋማያ ሳማቭርታሀ” ሽሪ ክርሽና ለእነዚህ ሞኞች እና ቀጣፊዎች በቀላሉ ሊገለፅ የሚችል አይደለም፡፡ ሽሪ ክርሽና ፈፅሞ ሊገለፅላቸው አይችልም፡፡ “ናሀም ፕራካሻህ ሳርቫስያ” (BG 7.25) በእነሺህ ሞኞች እና ቀጣፊዎች በቀላሉ ሊታወቅ ወይንም ሊገለፅ የሚችል አይደለም፡፡ የሚቻል አይደለም፡፡ ሽሪ ክርሽና እንዲህ ብሏል፡፡ “ናሃም ፕራካሻሀ ሳርቫስያ ዮጋ ማያ ሳማ” (ብጊ፡ 7 25) ማኑስያናም ሳሀስሬሱ ካሽቺድ ያታቲ ዲድሀዬ ያታታም አፒ ሲድሀናም ካሽቺድ ቬቲ ማም ታትቫታሀ፡፡ (BG 7.3)