AM/Prabhupada 0112 - ማናቸውም ነገር የሚወሰነው በውጤቱ ነው፡፡

Revision as of 17:39, 1 October 2020 by Elad (talk | contribs) (Text replacement - "(<!-- (BEGIN|END) NAVIGATION (.*?) -->\s*){2,15}" to "<!-- $2 NAVIGATION $3 -->")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Television Interview -- July 29, 1971, Gainesville

ቃለ መጠይቅ፡ ወደ እዚህ አገር የመጡት እኤአ በ1965 ነው፡፡ የመጡበትም ምክንያት የመንፈሳዊ አባትዎን ትእዛዝ በመከተል ነው፡፡ በመንገዳችን ላይ የመንፈሳዊ አባትዎ ማነው? ሽሪላ ፕራብሁፓድ፡ የእኔ መንፈሳዊ አባት “ኦም ቪሽኑፓድ ፓራማሀምሳ ብሀክቲሲድሀንታ ሳራስቫቲ ጎስቫሚ ፕራብሁፓዳ” ይባላል፡፡ ቀደም ብሎ ሲወርድ ሲዋረድ ስለመጣው የድቁና ስርዓት ተወያይተን ነበር፡፡ ይህም የድቁና ስርዓት ለዘመናት ወደ ኃላ ተያይዞ የሚሄድ ነው፡፡ ወደ ኋላ ተያይዞ በመሄድም ሽሪ ክርሽና ድረስ ይደርሳል፡፡ የእርስዎ መንፈሳዊ አባት ከእርሶ በፊት በሲህ ስርዓት ውስጥ የነበሩት ናቸውን? የድቁና ስርዓቱ የመጣው ከ 5,000 ዓመታት በፊት ከሽሪ ሽሪ ክርሽና ጀምሮ ነው፡፡ የመንፈዋዊ አባትዎ በሕይወት አሉ? በሕይወት የሉም፡፡ ያረፉትም እኤአ በ1936 ዓም ነው፡፡ እንግዲያው በአሁኑ ግዜ በዓለም ውስጥ ድቁና ስርዓቱን ተከትሎ ለመጣው እንቃስቃሴ ዋና ሀላፊው እርሶ ኖት ማለት ነው። ይህንን ለማለት እንችላለን? እኔ በርከት ያሉ መንፈዋዊ ወንድሞች አሉኝ፡፡ ቢሆንም ግን ከመጀመሪው ግዜ ጀምሮ ይህንን እንቅስቃሴ በዓለም ላይ እንድመራ በመንፈሳዊ አባቴ ትእዛዝ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ስለዚህ የማደርገው ነገር በሙሉ መንፈሳዊ አባቴን ለማስደሰት ነው፡፡ እንደምንረዳው ወደ አሜሪካ በመሄድ እንዲያስተምሩ ተለከው ነበር፡፡ የተሰጦት ወሰን ይህ ነበር ለማለት ይቻላል? ወሰን ሳይሆን የተሰጠኝ ትእዛዝ “እንግሊዘኛ ሊረዱ የሚችሉ አገሮች ሁሉ በመሄድ ይህንን የቫይሽናቫ ፍልስፍና አስተምር፡፡” የሚል ነበር፡፡ “እንግሊዘኛ ሊረዱ የሚችሉ አገሮች ሁሉ፡፡” አዎን፡፡ በተለይ ለምእራባውያን አገሮች በማለት ትእዛዝ ሰጥቶኝ ነበር፡፡ ከ 15-16 በፊት ወደ እዚህ አገር ሲመጡ እና እንቅስቃሴውን ሲጀምሩ... ሽሪላ ፕራብሁፓድ፡ የመጣሁት 15-16 ዓመት በፊት ሳይሆን ... ቃለ መጠይቅ፡ ይቅርታ ከ5-6 ዓመት በፊት ማለቴ ነው፡፡ ወደ እዚህ አገርም ሲመጡ በዚያን ግዜ በአገሪቱ ውስጥ የሀይማኖት ልምድ ስላነበረ ሊሆን አይችልም፡፡ በአሜሪካ ውስጥ ብዙ የተለያዪ የሃይማኖት ልምዶች አሉ፡፡ እንዲያውም በዚህ አገር ያሉ ሰዎች እምነት ያላቸው ሰዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ብዙሀኑ ሰው ሀይማኖትን የሚከተል እና በአምላክ የሚያምኑ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ እነዚህም ሰዎች በሚያምኑበት ሀይማኖት ስር በመተዳደር ሲያገለግሉ ይገኛሉ፡፡ ታድያ ወደ እዚህ አገር ሲመጡ ምን አስበው ነው የመጡት? የሀይማኖት እምነት በሚገኝበትስ አገር ምን ለመጨመር ብለው ነው ያሰቡት? ወይስ ወደ እዝህ አገር በመምጣት የራስዎን ፍልስፍና ለማከል ነው የመጡት? አዎን፡፡ ወደ አሜሪካ በመጀመሪያ ግዜ ስመጣ “በበትለር” ውስጥ የሚገኝ የአንድ ሕንዳዊ ሰው እንግዳ ነበርኩ፡፡ በፔንሲልቨንያ? ሽሪላ ፕራብሁፓድ፡ አዎን በፔንሲልቨንያ ውስጥ፡፡ በዚህም እያለሁ ምንም እንኳን አውራጃው ትንሽ ብትሆንም በርከት ያሉ ቤተክርስቲያኖች በማየቴ በጣም ተደስቼ ነበር፡፡ ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች? ሽሪላ ፕራብሁፓድ፡ አዎን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖች፡፡ እዚያም እያለሁ ከቤተክርስቲን አስተዳደሮች ጋር ተወያይቼ ነበር፡፡ እንግድነት የነበርኩበት ሰውም አስተዋውቆኝ ስለነበረ ነው፡፡ ስለዚህ የመጣሁበት ዓላማ በአገሪቱ ውስጥ የነበረውን የሀይማኖት ስርዓት ለመቃወም አልነበረም፡፡ ዓማላዬ ይህ አልነበረም፡፡ የእኛ ሚስዮን ዓላማ የጌታ ቼታንያን ሚስዮን ግብ ለማድረስ ነው፡፡ ይህም እያንዳንዱ ሰው ዓብዩ ጌታን እንዴት ማወቅ እንደሚችል እና እንዴት ፍቅሩን ለማዳበር እንደሚችል ነው፡፡ ይህን በአሁኑ ግዜ በምን ዓይነት ለማድረግ እንዳሰቡ መጠየቅ እችላለሁን? አምላክን ለማፍቀር እንድንችል እርሶ የሚያስተምሩት ትምህርት እንዴት አድርጐ ነው ከሌሎች የሀይማኖት ትምህርቶች ለየት ብሎ የሚቀርበው? ወይም ደግሞ እንዴት አድርጐ ነው እዚህ አገር ከሚሰጠው የሀይማኖት ስርዓት ተለይቶ ሊቀርብ የሚችለው? እነዚህም የሀይማኖት ስርዓቶች በምእራባውያን አገሮች ውስጥ በብዙ መቶ ዓመታት ሲቀርቡ የነበሩ ናቸው፡፡ ሽሪላ ፕራብሁፓድ፡ ይህ ትክክል ነው፡፡ ምክንያቱም ግን እኛ የምንከተለው የጌታ ቼታንያን ፈለግ ነው፡፡ ጌታ ቼታንያ በቬዲክ ስነፅሁፍ ውስጥ ሽሪ ክርሽና እንደመሆኑ ተገልጿል፡፡ እኛም ተቀብለነው መመሪያውን በመከተል ላይ እንገኛለን፡፡ ቃለ መጠይቅ፡ ይህስ የትኛው ጌታ ነው፡፡ ፕራብሁፓድ፡ ጌታ ቼታንያ ቃለ መጠይቅ፡ ከ500 ዓመታት በፊት ወደ ሕንድ አገር መጥቶ የነበረው ነውን? አዎን፡፡ እርሱም ክርሽና እራሱ ነው፡፡ የመጣበትም ዓላማ እንዴት አድርገን የክርሽናን ፍቅር ለማዳበር እንደምንችል ለማስተማር ነው፡፡ ስለዚህ እርሱ የሰጠን ስርዓት መንፈሳው ስልጣን ያለው ነው፡፡ ለምስሌ አንተን በምትሰራበት ድርጅት ውስጥ ባለሙያ ነህ፡፡ አንድ ሰራተኛም ስራውን በደንብ እንዲሰራ ሙያህን ብታስተምረው ይህ ስልጣን ያለው ስርዓት ነው፡፡ ስለዚህ የዓብዩ ጌታን ንቃት ዓብዩ ጌታ ሲያስተምረን ይገኛል፡፡ ለምስሌ በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ሽሪ ክርሽና ዓብዩ ጌታ ሆኖ ስለ ራሱ ማንነት ሲገልፅልን ይገኛል፡፡ በመጨረሻም እንዲህ ሲለን ይገኛል “ሙሉ ልቦናችሁም ለእኔ የሰጣችሁ ከሆነ እኔ ሁሉን ነገር ልንከባከብላችሁ እችላለሁ፡፡” ይህንን ግን ሰዎች በትክክል አይረዱትም፡፡ ስለዚህ ሽሪ ክርሽና ራሱ እንደ ጌታ ቼታንያ ሆኖ በመምጣት እንዴት ሰዎች ሙሉ ልቦናቸውን ለዓብዩ ጌታ ለመስጠት እንደሚችሉ ለማስተማር መጣ፡፡ እኛም ይህንን ስልጣን ያለውን ስርዓት በመከተል የጌታ ቼታንያን ፈለግ ስለምንከተል ስርዓቱ ውጤታማ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የውጭ አገር ሰዎች ስለ ጌታ ክርሽና ፈፅሞ ሰምተው የማያውቁት እንኳን ሙሉ ልቦናቸውን ለዓብዩ ጌታ ሲሰጡ ይገኛሉ፡፡ ይህም ስርዓት የዓብዩ ጌታን ፍቅር ለማዳበር ሀይል ያለው ነው፡፡ ዓላማዬም ይህንን ስርዓት የተመረኮዘ ነው፡፡ “ይህ ሀይማኖት ከዚህ ሀይማኖት ይበልጣል፡፡” በማለት ለማወጅ አልመጣንም፡፡ ወይንም ደግሞ የእኔ ስርዓት ከሌላው የተሻለ ነው ለማለት አልመጣንም፡፡ ውጤታማ ወደሆነው ስርዓት ግን ለማተኮር እንፈልጋለን። በሳንስክሪት ቋንቋ “ፍሀሌና ፓሪቺያቴ” የሚል አባባል አለ፡፡ አንድ ነገር በውጤቱ ይገመገማል፡፡ አንድ ነገር በምን ይገመገማል? ሽሪላ ፕራብሁፓድ፡ በውጤቱ ቃለ መጠይቅ፡ ትክክል ነው፡፡ አንተ የእኔ ስርዓት ይሻላል ልትል ትችላለህ፡፡ እኔም የእኔ ስርዓት ይሻላል ልል እችላለሁ፡፡ በመጨረሻ ግን ልንፈርድ የምንችለው ስርዓቱ ምን ያህል ስኬታማ መሆኑን ለማሳየት ስንችል ነው፡፡ የቬዳዎች ብሀገቫታ መፅሀፍም እንደሚገልፀው አንድ የሀይማኖት ስርዓት ስኬታማ ነው ለማለት የምንችለው አንድ ሰው ምን ያህል የዓብዩ ጌታ ፍቅር እንዳደረበት ሲታይ ነው፡፡