AM/Prabhupada 0111 - ትእዛዞችንም ሁሉ ተከተሉ፡፡ በዚህም በሄዳችሁበት ሁሉ የተጠበቃችሁ ትሆናላችሁ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

Follow the Instruction, Then You are Secure Anywhere - Prabhupāda 0111


Morning Walk -- February 3, 1975, Hawaii

ድቮቲ 1:ሽሪላ ፕራብሁፓድ:አንድ ሰው ስልጣኑን የሚያገኘው ከየት ነው?

ፕራብሁፓዳ:የእርሱ ጉሩ: ባለስልጣኑ ነው:

ድቮቲ 1:አይደለም: እርሱን አውቃለሁ:ግን ስለሚሰራው ስራ:ከ4 ቱ መመሪያዎቹ መከተል እና ከ 16 ግዜ ጃፓ ከማድረጉ ውጪ ማለቴ ነው: በቀን ውስጥ ብዙ ነገር ሊያደርግ ይችላል:ለምሳሌ በቤተ መቅደሱ ባይኖር ከየት ነው ባለስልጣን የሚያገኘው? ፕርብሁፓድ:አልገባኝም:ባለስልጣኑ ጉሩው ነው:የተቀበልከው ጉሩ:ባሊ ማርደና:ለሁሉም ነገር? ጃያቲርትሃ:ለምሳሌ ውጪ እኖራለሁ እንበል: 50½ ገቢዬን ደግሞ አላቀርብም እንበል: እና ይህ ስራ የምሰራው በጉሩዬ ስልጣን ስር ነውን? ፕራብሁፓድ: እንዲህ ከሆነ የጉሩህን ትእዛዝ አትከተልም ማለት ነው:ይህም እርግጥ ነው: ጃያቲርትሃ:ታድያ ሙሉ ቀን ስሰራ የዋልኩት ስራ:ከጉሩዬ ትእዛዝ ውጪ ሊሆን ይችላልን?በስልጣን ያልታዘዘ ስራ ሊሆን ይችላልን? ፕራብሁፓድ:አዎን:የጉሩህን ትእዛዝ የማትከተል ከሆንክ:አንተ የወደቅህ ሰው ነህ: ይኅው ነው:አለበለዚያ ለምንድነው እንዲህ የምትዘምረው?“ያስያ ፕራሳዶ ብሃገቨት ፕረሳዶ” የእኔ ሃላፊነት ጉሩዬን ማስደሰት ነው:አለበለዛ የትም አልደርስም: የትም ለመድረስ ካልፈለግህ:እንደልብህ አለመታዘዝ ትችላለህ: ነገር ግን ባለህበት ደረጃ:ረጋ ያልክ ለመሆን ብትፈልግ ግን:የጉሩህን ትእዛዝ በትክክል መከተል አለብህ:

ድቮቲ 1:መመሪያዎችህን ሁሉ መፅሃፍቶችህን በማንበብ ብቻ መረዳት እንችላለን:ፕራብሁፓድ:አዎን ልክ ነው:መመሪያውን ተከተሉ:ያ ነው የሚያስፈልገው: ባላችሁበት ቦታ:መመሪያውን ተከተሉ:የት እንደሆናችሁ ለውጥ አያመጣም:ደረጃችሁ የጠበቀ ይሆናል: መመሪያውን ተከተሉ:የትም ቦታ ብትሆኑ ደረጃችሁ የጠበቀ ይሆናል:የት እንደሆናችሁ ለውጥ አያመጣም: ልክ እንደ ነገርኳችሁም:የእኔን ጉሩ ማሃራጅ ያየሁት ከ10 ቀን በላይ አይሆንም:ነገር ግን:ትእዛዙን እድሜ ልኬን በመከተል ላይ እገኛለሁ: ግርሃስታ ነበርኩኝ (ባለ ትዳር) ቤተ መቅደስ ውስጥም አልኖርኩም: ብዙዎች መንፈሳዊ ወንድሞቼ “የሙምባይ ቤተ መቅደስ ሃላፊ መሆን አለበት: ወይንም ሌላ ሃላፊነት” እያሉ ይጠይቁ ነበር: ነገር ግን:ጉሩ ማሃራጅ ውጪ ቢኖር ይሻለዋል ይላቸው ነበር: የሚያስፈልገውን ነገር ወደ ፊት ይፈጽማል ይላቸው ነበር: ድቮቲዎች:ጃያ!ሀሪ ቦል!ፕራብሁፓድ:እንዲህም ብሎ ነበር: በዚህም ግዜ ከእኔ ምን እንደሚጠብቅ አላውቅም ነበረ: በእርግጥ:እኔ መስበክ እንደሚጠበቅብኝ ግን አውቅ ነበር: ያሾዳናንዳና:ይህንንም በትልቁ ደረጃ አድረገኅዋል:ድቮቲዎች:ጃያ!ፕራብሁፓዳ:ሀሪ ቦል!

ፕራብሁፓዳ:አዎን በትልቁ ደረጃ:ይህም የጉሩ ማሃራጄን ትእዛዝ በደንብ ስለተከተልኩኝ ነው:ሌላ የለም: አለበለዛ ግን ምንም ሃይል የለኝም: ማጂክ አልሰራሁም: ሰራሁ እንዴ?ወርቅ ፈጥሪያለሁ? (ሳቅ) እንዲሁም ሁኖ:እኔ ወርቅ ከሚፈጥር ጉሩ በላይ:ጥሩ ተከታዮች አሉኝ: