AM/Prabhupada 0016 - መስራት እፈልጋለሁ፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 7.1 -- San Francisco, March 17, 1968

እንዴት ከጌታ ክርሽና ጋር መገናኘት እንደምንችል ማወቅ አለብን: ክርሽና ሁሉም ቦታ ላይ ይገኛል: ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ነው: ይህ የክርሽና ንቃት ነው: እንዴት ከተለያዩ ፎርሞች ክርሽናን እንደምናገኝ ማወቅ አለብን: ከእንጨትም ሆነ: ከብረት: ከተገኘው ነገር: ክርሽና ከሁሉም ቦታ ይገኛል: እንዴት በሁሉም ነገር ከክርሽና ጋር መገናኘት እንደምንችል መማር አለብን: ይህ በዚህ ዮጋ ሲስተም ተገልጧል እና መማር ትችላላችሁ: የክርሽና ንቃትም ዮጋ ነው: ትክክለኛው ዮጋ: ከዮጋዎች ሁሉ በከፍተኛ ደረጃ የሚታየው ዮጋ ነው: ማንም ዮጊ ቢመጣ ይህንን ለማሳመን እንችላለን: ይህም የዮጋ 1ኛ ዮጋ ሲስተም ነው ማለት እንችላለን: ይህ 1ኛ ነው:ሁኖም ለመለማመድም በጣም ቀላል ነው: ገላችሁን ማለማመድ አያስፈልጋችሁም: ለምሳሌ አቅመ ደካማ ልትሆኑ ትችላላችሁ: ለክርሽና ንቃት ግን: ምንም ድካም አይሰማችሁም: የእኛ ተማሪዎች በክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ስራ:በጣም አገልግሎቱ እንዲበዛላቸው ነው ምኞታቸው: “ስዋሚጂ ምን ላድርግ? ምን ልስራ?” ብለው ሁሌ እንደጠየቁ ነው: በጣም ጥሩም ስራ እየሰሩ ይገኛሉ: ድካምም አይሰማቸውም: ይህ የክርሽና ንቃት ነው: በዚህ ምድራዊ አለም ከስራ በኋላ ድካም ይመጣል: እረፍትም ያስፈልጋል: ይህንንም ስል እየአጋነንኩት አይደለም: እኔ የ72 አመት እድሜዬ የገፋ ሰው ነኝ: አንድ ግዜም ታምሜ ወደ ሕንድ ሂጄ ነበረ: ነገር ግን ተመልሼ መጥቻለሁ: ለማገልገልም እሻለሁ: ለመስራት እፈልጋለሁ: ከዚህ ሁሉ ስራ ተርፌ: ጡረተኛ ሁኜ: መቀመጥ እችል ነበር: ነገር ግን ምኞቴ ለማገልገል ነው: እስከቻልኩኝ ድረስ: ለማገልገል እሻለሁ: ቀን እና ሌሊት ማገልገል እሻለሁ:ማታ ማታ በዲክታ ፎን እየተጠቀምኩ እሰራለሁ: ካልሰራሁኝም ቅር ይለኛል: ይህ የክርሽና ንቃት ነው: ለማገልገል ሁላችን በጣም ፍላጎት እንዲኖረን ያስፈልጋል: ይህ እንቅስቃሴ የሌለው ህብረተሰብ አይደለም: የሚበቃ ስራ በእጃችን አለ: ወረቀቶችን ማረም: ማተም:እና የመሽጥም ስራ አለ: እንዲሁም የክርሽና ንቃት እንዴት እንደሚስፋፋም ጥታት አድርጉ: ይህ የተግባራዊ የክራሽና ንቃት ስራ ነው: