AM/Prabhupada 0017 - የመንፈሳዊ ሀይል እና የቁሳዊ ዓለም ሀይል

From Vanipedia


Spiritual Energy And Material Energy - Prabhupāda 0017


Lecture on Sri Isopanisad, Mantra 1 -- Los Angeles, May 2, 1970

በዚህ አለም ላይ ሁለት አይነት ኃይሎች:ይገኛሉ:የመንፈሳዊ ሃይል እና የአለማዊ ሃይል የአለማዊ ሃይል ማለትም: እነዚህን 8 አይነቶች የምድራዊ ንጥረ ነገሮች ማለት ነው: ”ብሁሚር አፖ ናሎ ቫዩህ“ ብ ጊ 7 4 )“መሬት:ውሃ: እሳት: አየር: ሰማይ: ሃሳብ: አእምሮ: ህልውና” እነዚህም ሁሉ አለማዊ ንጥረ ነገሮች ናቸው:ከስስ ጀምረው እስከ የጎሉ ማለት ነው: ለምሳሌ:ውሃ ከአፈር የሳሳ ሁኖ ይገኛል: እሳት ደግሞ ከውሃ የሳሳ ሁኖ ይገኛል: አየር ደግሞ ከእሳት የሳሳ ሁኖ ይገኛል:ሰማይ ደግሞ ከአየር የሳሳ ሁኖ ይገኛል: እንደዚህም ሁሉ: እውቀት ከሰማይ የሳሳ ሁኖ ይገንኛል:ወንንም አእምሮ ከሰማይ የሳሳ ሁኖ ይገኛል ሃሳብ ደግሞ: ስለ ሃሳብ ብዙ ምሳሌ ሰጥቻለሁ: ስለ ሃሳብ ፍጥነት: በአንድ ሴኮንድ ውስጥ: ሃሳብ ብዙ ሺህ ማይሎችን መጓዝ ይችላል: እና የሳሳ በሆነ ቁጥር: ሃይሉም ከፍ ያለ ይሆናል: እንደዚህም ሁሉ:ወደ መንፈሳዊ ደረጃ ስትደርሱ: በጣም የሳሳ እና ለሁሉም ምንጭ የሆነው ነፍስ: በጣም ሃይል ያላት ናት: ይህም የመንፈሳዊ ሃይል ነው: ይህም በብሃገቫድ ጊታ ተገልጿል: ያስ የመንፈሳዊ ሃይል ምንድን ነው? ያም የመንፈሳዊ ሃይል ነዋሪዋ ነፍሳችን ናት: “አፓረያም ኢታስ ቱ ቪድሂ ሜ ፕራክቲም ፓራ (ብ ጊ 7 5) ክርሽናም እንዲህ ይላል ”እነዚህ ምድራዊ ሃይል ናቸው:ከዚህም አልፎ ግን ሌላ መንፈሳዊ ሃይል እና ምድር አለ“ ”አፓረያም“ አፓራ ማለት ዝቅተኛ ማለት ነው: ”አፓሬያም“ ”እነዚህ ቀድሞ የተገለጹት ሁሉ:ዝቅተኛ ሃይሎች ናቸው“ ”ከነዚህም በላይ ከፍተኛ ሃይሎች አሉ:የእኔ አርጁና“ ይህስ ምንድን ነው? “ጂቫ ብሁታ ማሃ ባሆ” “ “እነዚህ ነዋሪ ነፍሶች” እነዚህም ነፍሶች ሃይሎች ናቸው:እኛም ነፍሶች ሃይሎች ነን: ነገር ግን ምድባችን ከከፍተኛ ሃይል ጋር ነው: ምን ያህል ከፍተኛ? ምክንያቱም ”ያዬዳም ድሃርያቴ ጃጋት“ (ብ ጊ 7 5) የከፍተኛው ሃይል:የዝቅተኛውን ሃይል በቁጥጥሩ ስር ያደርገዋል: የምድር ተፈጥሮ እንደ ነፍስ ሃይል የለውም: በተፈጥር ንጥረ ነገሮች ተሰርቶ: ትልቅ አይሮፕላን ወይንም ማሽን ሊበር ይችላላል ነገር ግን ያለ መንፈሳዊ ሃይል ወይንም ያለ ፓይለት ዋጋ ሊኖረው አይችልም: ለብዙ ሺህ አመት አይሮፕላኑ ያለ ፓይለት መንቀሳቀስ አይችልም: ትንሿ ነፍስ ወይንም ፓይለቱ ካልነካት አይሮፕላኗ ልትበር አትችልም: እና አማላክን ለመረዳት የሚያዳግተን ለምንድን ነው? እና ይህም ትልቅ ግዙፍ አይሮፕላን: በአለም ላይ ብዙ ግዙፍ ማሽኖች አሉ: ነገር ግን ያለ መንፈሳዊ ሃይል ሊንቀሳቀሱ አይችሉም: ይህም የሰው ልጅ ወይንም ሌላ ነዋሪ ነገር: እንዴት ይህ አለም: ያለ ማንም ቁጥጥር: በአውቶማቲክ ሊሰራ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ? እንዴትስ ክርክራችሁን በዚህ ትመሰርታላችሁ? ይህ ሊሆን አይችልም: ስለዚህ ይህ አስተሳሰብ: ዝቅተኛ አስተሳሰብ ላላቸው ሰው ነው: ይህ አለም እንዴት በጌታ አምላክ እንደሚተዳደር ሊረዱ ያዳግታቸዋል: