AM/Prabhupada 0024 - ክርሽና በጣም ሩህሩህ ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 3.25.26 -- Bombay, November 26, 1974

አርጁና ክርሽናን ፊት ለፊት እያየው: ክርሽና ብሃገቫድ ጊታን አስተማረ:: ይህ ክርሽናን መመልከት እና: ብሃገቫድ ጊታን ማንበብ:አንድ የሆነ ነገር ነው: ምንም ልዩነት የለውም:አንዳንዶችም “አርጁና በጣም እድለኛ ነው” ይላሉ: ይህም ክርሽናን ፊት ለፊት እያየ:ትእዛዝ ስለተቀበለ ነው:ነገር ግን ይህ ትክክለኛ አስተያየት አይደለም: የሚያይ መንፈሳዊ የፍቅር አይን እስከአለን ድረስ: ክርሽና ወዲያው ሊታየን ይችላል: ስለዚህም እንዲህ ተጽፏል:“ፕሬማንጀና ቹሪታ” ፕሬማ እና ብሃክቲ: አንድ ናቸው: “ፕሬማንጃና ቹሪታ ብሃክቲ ቪሎቻኔና ሳንታህ ሳዳይቫ ህርዳዬሹ ቪሎካያንቲ” (ብ ሰ 5 38) ከዚህ ጋራም የተያያዘ አንድ ታሪክ ልነግራችሁ እችላለሁ:በደቡብም ህንድ አገር አንድ ብራህማና ነበር:(ቄስ) “ራንጋናት" የሚባል ቤተ መቅደስ ውስጥም የብሃጋቫድ ጊታን ቅዱስ መጽሃፍ ያነብ ነበር: ቢሃንም ግን የሳንስክሪት ቋንቋም ሆነ ደብዳቤ እንኳን ለማንበብ የማይችል ሰው ነበር: በጎረቤትም ያለ ሰው ሁሉ ይህንን ያውቁ ነበር: እንዲህም አሰቡ :“ይህ ሰው ማንበብ አይችልም:ነገር ግን ብሃጋቫድ ጊታ እያነበበ ይመስላል“ መፅሃፉንም እየገለጠው ነው:”አሃ አሃ“ ከዚያም አንዱ እየቀለደ ጠየቀው ”ብራህመና ሆይ:እንዴት ነው ብሃጋቫድ ጊታ የምታነበው?” እርሱም የሰውየውን አቀራረብ ተረዳ “ይህ ሰው ማንበብ የማላውቅ በመሆኔ ነው የሚቀልደው” ብሎ አሰበ: በዚህም ግዜ ጌታ ቼይታንያ በዚሁ በራንገናት ቤተ መቅደስ ውስጥ ነበረ: ጌታ ቼታንያም ይህ ሰው “የክርሽና አገልጋይ” መሆኑን ተረዳ: ስለዚህም ጠጋ ብሎ እንዲህ ጠየቀው “ውድ ብራህማና: ምን እያነበብክ ነው ያለኀው?“ ብራህመናውም ይህ ሰው እንደማይቀልድበት ተረዳ: እንዲህም አለ:”የኔ ጌታ:የማነበው ብሃጋቫድ ጊታ ነው:ለማንበብም እየሞከርኩ ነው:ነገር ግን ማንበብ አልችልም“ ብሎ ተናገረ: የኔ ጉሩ (የመንፈሳዊ አስተማሪዬ)እንዲህ አለኝ:”በቀን በቀን 18 ምእራፎች ማንበብ አለብህ“ ብሎ አዞኛል: እኔ ግን ምንም እውቀት የለኝም:ማንበብም አልችልም: ቢሆንም ጉሩ ማሃራጅ አዞኛል:ስለዚህ እኔም ትእዛዙን ለመከተል እየሞከርኩኝ ነው: እና ገፆቹን ብቻ ነው የምገልጠው እንጂ ለማንበብ አልችልም:ብሎ ተናገረ: ጌታ ቼይታንያም ”ስታነብ አንዳንድ ግዜ ስታለቅስ አይሃለሁ“ አለው: እርሱም ”አዎ አንዳንድ ግዜም አለቅሳለሁ“ አለ: ”ታድያ ማንበብ የማትችል ከሆነ: እንዴት ለማልቀስ ቻልክ“ ብሎ ጠየቀው: ”የብሃጋቫድ ጊታ መጽሀፉን ሳነብ:አንድ ስእል አያለሁ“ ”በዚህም ስእል ክርሽና በፍቃዱ የጋሪ ነጂ ሁኖ ይታያል:”የአርጁና ሳረቲ“ ወይንም ጋሪ ነጂ: “አርጁና የክርሽና አገልጋይ ቢሆንም:እዚህ ላይ ክርሽና በፍቃዱ የአርጁና አገልጋር ሁኖ ይታያል” ”አርጁናም ትእዛዝ ሲሰጥ እና: ክርሽናም ሲያገለግለው ይታያል:“ “ክርሽና በጣም ሩህሩህ ነው:ይህንንም ስእል በሃሳቤ ቀርጬ ሳየው:ለቅሶ እና እንባዬ ይመጣብኛል” ጌታ ቼይታንያም ወዲያውኑ አቀፈው:ከዚያም ”አንተ ብሃጋቫድ ጊታን እያነበብክ ነው“ አለው: “ያለ ምንም ትምህርት ብሃጋቫድ ጊታን እያነበብክ ነው ያለኅው” ከዚያም እቅፍ አደረገው:እንዴትም በጥሞና ስእሉን ይመለከት እንደነበረ ተረዱ: የክርሽናም ፍቅር ስለነበረው: ጥቅሶቹን ቢያነብም ባያነብም ምንም ለውጥ አያመጣም ነበረ: ልቦናው በክርሽና ፍቅር ተመስጦ ነበረ:እንዲሁም ተመስጦ ይመለከት ነበረ: ክርሽና ተቀምጦ:የአርጁናን ጋሪ ይነዳ ነበረ: