AM/Prabhupada 0025 - ከልብ የመነጨ ነገር ለሰው ከሰጠን ሊሰራ ይችላል፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

If We Give Genuine Thing, it Will Act - Prabhupāda 0025


Conversation with Yogi Amrit Desai of Kripalu Ashram (PA USA) -- January 2, 1977, Bombay

ዮጊ አምርት ደሳይ: እንዲህ አለ “ለአንተ በጣፍ ፍቅር ስለአለኝ:አንተን ለማየት መጥቻለሁ” ብሎ ተናገረ: ፕራብሁፓዳም:አመሰግናለሁ አለ: ዮጊ አምርት ደሳይ:“አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲህ እላቸው ነበር” ፕራብሁፓዳ: "ከዶክተር ሚሽራ ጋር ነህን?“ ዮጊ አምርት ደሳይ:”አይደለሁም: እዚህ ያሉትን አገልጋዮች እንዲህ እላቸው ነበር“ ”ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ምእራባዊ አገሮች የብሃክቲን ትምህርት ያመጣው ሽሪላ ፕራብሁፓዳ ነው: ይህም በጣም አስፈላጊ ነበረ:“ ምክንያቱም እዚህ ብዙ ሃሳብ ጭንቅላት ውስጥ አለ:ማሰብ:ማሰብ:ማሰብ: ይህ የፈጣሪ ፍቅር በጣም ጥልቀት ያለው ነው: ፕራብሁፓዳ:”እየውልህ: ንጹህ እና ልክ የሆነ ነገር ካቀረብን:“ ዮጊ አምርት ደሳይ:”በጣም የታመነ“ ፕራብሁፓዳ: ”ሰው ሊረዳው እና ሊቀበለው ይችላል“ ዮጊ አምርት ደሳይ:”ለዚህም ነው ድርጅቱ በቆንጆ መንገድ እያደገ የሚገኘው:ምክንያቱም በጣም የታመነ ስለሆነ ነው:“ ፕራብሁፓዳ: ”ስለዚህም የእያንዳንድ ህንድ ሃላፊነት ይህንን የታመነ ትክክለኛ ትምህርት ለአለም መስጠት ነው“ ይህም ”ፓራ ኡፓካር“ ይባላል:”እኔም ከመምጣቴ በፊት ብዙ ስዋሚዎች እና ዮጊዎች ከህንድ መጥተው ሊያታልሏቸው ተሰማርተው ነበረ:“ ዮጊ አምርት ደሳይ:”አይደለም:እውነትን ለመስጠት ፈርተው ነው:ይህም ሰው ይቀበለናል ብለው ፈርተው ስለነበረ ነው:“ ፕራብሁፓዳ: ”እውነት ምን እንደሆነ አያውቁም: ፈርተው ግን አይደለም“ ለምን?አንድ ሰው እውነትን ከያዘ መፍራት የገባውናልን? ዮጊ አምርት ደሳይ:”እርግጥ ነው“ ፕራብሁፓዳ: “ከቪቬካናንዳ ጀምሮ:እውነት ምን እንደሆነ አያውቁም ነበረ:” ዮጊ አምርት ደሳይ:”ይህ ሙሉ በሙሉ ትክክል ነው: ይህንንም አንተ ከመጣህ በኋላ አይተነዋል“ እኔም በ1960 እዚያ ነበርኩ: ዮጋ ማስተማርም ጀምሬ ነበረ: ነገር ግን አንተ ከመጣህ በኋላ:ፍርሃቴ ጠፍቶ ብሃክቲ እና መቁጠሪያ ማስተማር ጀመርኩ: አሁን ብዙ የብሃክቲ ማስተማርያ ገዳሞች አሉን:ብዙ የብሃክቲ ይህንንም ክብር ለአንተ እሰጣለሁ ምክንያቱም በፊት ይህንን ለማስተማር እፈራ ነበር: እንዲህም አስብ ነበር ”እነዚህ ክርስቲያኖች ናቸው:ቡዙ የፍቅር አገልግሎትን መስጠት አይፈልጉ ይሆናል: ላይረዱትም ይችላሉ: ነገር ግን አንተ ተአምር ሰርተሃል:አማላክ ጌታችን ክርሽናም በአንተ በኩል ተአምር ሊሰራ በቅቷል: ይህንንም ትልቅ ተአምር በመሬት ላይ ማየት በጣም የሚያስገርም ነው: ይህም በጣም ጥብቅ ሁኖ ይሰማኛል: ፕራብሁፓዳ: “ይህንን ቃል መስጠትህ ሩህሩህነትህ ነው” “የታመነ ንጹህ ነገር ከሰጠን:ይህ ይሰራል:” ዮጊ አምርት ደሳይ:“በእርግጥ:ይህንን ነው እኔም ለማድረግ የምሞክረው:ሁላችንም:” 180 ሰዎች በገዳማችን ይኖራሉ:ሙሉክስናም እይተለማመዱ ነው: ጥዋትም በ 4 ኤ ኤም ተነስተው:በ 9 ፒ ኤም ይተኛሉ እርስ በእርስም አይነካኩም: በተለያየ ክፍልም ተኝተው ያድራሉ: ለመዘመር ሲቀመጡም ተለያይተው ነው:ሁሉም ነገር ጥብቅ ነው: አልኮል መጠጥ:ስጋ: ሻይ: ቡና:ነጭ ሽንሁርት:ቀይ ሽንኩርት ሁሉ አይፈቀድም:ንጹህ ኑሮ አላቸው: ፕራብሁፓዳ: “በጣም ጥሩ ነው: እኛም ይህን ሁሉ እንከተላለን” ዮጊ አምርት ደሳይ:“አዎን” ፕራብሁፓዳ: “ታድያ እናንተም ዴይቲ አላችሁ?” (የክርሽና ፎርም) ዮጊ አምርት ደሳይ:“አዎን ያለንም ዴይቲ የክርሽና እና የራድሃ ነው” የኔም ጉሩ ስዋሚ ክርፓሉ አናንዲ ይባላል: ባሮዳ ህንድ አገርም አንድ ገዳም አለው: በመንፈሳዊ አለም 27 አመት አገልግሏል:በፀጥታ ደግሞ 12 አመት ተቀምጧል: ባለፉት ሁለት አመታት ግን አንድ ወይንም ሁለቴ ተናግሯል: ይህም ሰው በጣም ስለጠየቀው ነው: ፕራብሁፓዳ: “ታድያ አይዘምርም እንዴ?” ዮጊ አምርት ደሳይ:“ይዘምራም:በፀጥታው ግዜ መዘመር የተፈቀደ ነው” ይህም የአምላክን ስም በማወደስ ነው: ይህም ፀጥታን እንደማፍረስ አይቆጠርም: ስለዚህም ይዘምራል: ፕራብሁፓዳ: ፀትታ ማለት አሉባልታ አለማውራት ማለት ነው:ሀሬ ክርሽና መዘመርም ይገባናል: ይህም ፀትታ ማለት ነው: ግዜ ከማባከን እና ይህን አለማዊ ነገር ከማውራት: ሀሬ ክርሽና መዘመር ይገባናል: ይህ ትክክለኛ ነው: ፀጥ ማለት ግን ትክክል አይደለም: ሴንስ የሌለው ነገር መናገር አቁመን ሴንስ ያለው ነገርን መናገር ይገባናል: ዮጊ አምርት ደሳይ:“ይህ ትክክል ነው” ፕራብሁፓዳ: “ፓራም ድርስትቫ ኒቫርታቴ (ብጊ 2 59)ፓራም ድርስትቫ ኑቫርታቴ” አንድ ሰው አሉባልታውን ቢያቆም: ከዚያም “ፓራም” አማላክን “ፓራም ድርስትቫ ኒቫርታቴ” ”ጥሩ ነገር በእጅህ ሲገባ: መጥፎ የያዝከውን ነገር ትጥላለህ“ ”አለማዊ የሆነ ነገር ሁሉ ቆሻሻ ነው“ “ካርማ:ግያና: ዮጋ: እነዚህ ሁሉ አለማዊ ናቸው” “ካርማ: ግያና: ዮጋ: ዮጋ የሚባለው ሁሉ አለማዊ ናቸው”