AM/Prabhupada 0027 - ከዚህ ሕይወት ባሻገር ሌላ ሕይወት እንዳለ አያውቁም፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on CC Adi-lila 7.1 -- Atlanta, March 1, 1975

የመጽሃፍ ንባብ: "በዚህ አለም በተወሰነ አይነት ኑሮ የሚኖር ሰው ሁሉ: እርዳታ የሌለው ሁኔታ ላይ ሁኖ ይገኛል" ነገር ግን ይህ ውስን ላይ ያለ ነፍስ ሁሉ: በማያ ምትሃት ወይንም በአማላክ የውጪያዊ ሃይል አማካኝነት እንዲህ ብሎ ያስባል: "እኔ በአገሬ: በህብረተ ሰቤ: በጓደኞቼ እና በፍቅር ተደግፌአለሁ:" ነገር ግን ሞት ስትመጣ ማንም ሊደግፈው እንደሚችል አይገነዘብም: ይህ ምትሃት ወይንም ማያ ይባላል: ነገር ግን ይህንን አያምንም:: በማያ ምትሃትም: ምን ሊያድነው እንደሚችልም ሊረዳ ወይንም ሊያምን አይችልም:: መዳን ማለት እራስን ከዚህ ከተደጋጋሚ መወለድ እና መሞትን ማዳን ማለት ነው:: ይህ ነው መዳን ማለት:: እንሱ ግን ይህንን አይረዱም:: ንባብ: "የተፈጥሮ ህግጋት ሃይለኛ ከመሆናቸው የተነሳ: የትኛውም አለማዊ ሃብታችን: ከዚህ ከክፉ ሞት ሊያድነን አይችልም:: ሁሉም ሰው ይህን ያውቃል:: ይህ ነው ትልቁ ችግራችን:: ማነው ሞትን የማይፈራው? ሁሉም ሞትን ይፈራል:: ለምን? ምክንያቱም ነፍስ ሟች ስለአልሆነች ነው:: ነፍስ ዘለአለማዊ ናት:: ስለዚህም ትውልድ: ሞት: እርጅና: እና ህመም እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሁሉ: ለነፍስ አሸባሪዎች ናቸው:: ምክንያቱም ነፍስ ዘላለማዊ ናት:: ነፍስ አትወለድም:: "ና ጃያቴ" ነፍስ ስለማትወለድ: መሞትም አትችልም:: "ና ምርያቴ ካዳቺት" ይህ ነው የነፍሳችን ትክክለኛ ደረጃ" ስለዚህም ሞትን እንፈራለን:: ይህ ነው የተፈጥሮአዊ ዝንባሌያችን:: እና ከሞት ለመዳን ሁሌ እንጥራለን:: ይህ የሰው ልጅ የመጀመሪያ ጥረቱ ነው:: ይህንንም የክርሽና ንቃተ ትምህርት የምናስተምረው: የኑሮን አላማ ለማስተማር ነው:: ይህ የሁሉም ሰው አላማ መሆን አለበት:: ይህም የቅዱስ መጽሃፍቶች ህግጋት ነው:: እነዚህ የሚንከባከቡን ሁሉ: መንግስት: አባት: አስተማሪ: የልጆች ተንከባካቢዎች ናቸው:: የአለምን ህዝብ እንዴት እንክብካቤ መስጠት እንዳለብንም ማወቅ አለባቸው:: "ና ሞቻዬድ ያህ ሳሙፔታ ምርትዩም" እና ይህ ፍልስፍና በአለም ላይ የት አለ? ይህ ፍልስፍና በአለም ላይ አይታይም:: ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበራችን: ይህንን ፍልስፍና እያስተማረ ይገኛል:: እንዲሁም በግምት ሳይሆንም: ስልጣን ያለውን የቬዲክ ቅዱስ ጽህፈቶችን ተመርኩዞ ነው:: ይህ ነው የእኛ ትእዛዝ: በተለያየ ቦታም የምድር ሰውን ለማገልገል ቅርንጯፎች ከፍተናል:: ይህም የህይወትን አላማ የሰው ልጅ ስለዘነጋ ነው:: ከሞትም በኋላ ህይወት እንዳለ የሰው ልጅ ስለዘነጋ ነው:: ይህንን ሁሉ የሰው ልጅ ዘንግቷል:: ያለ ምንም ጥርጣሬ: ከሞት በኋላ ህይወት አለ: ከሞት በኋላ ላለውም ህይወት በዚህ ኑሮ አችን መዘጋጀት እንችላለን:: ወደ ከፍተኛም ፕላኔቶች ሂዶ ከዚህ ምድር የበለጠ ምቾት ያለው ህይወት ለማግኘት መዘጋጀት ይቻላል:: እዚህም የተረጋገጠ ኑሮ መያዝ ይቻላል:: እዚህ የተረጋገጠ ማለቴም አለማዊ ህይወት ከተፈለገ ማለት ነው:: እንዲህም ተብሏል: "ያንቲ ደቫ ቭርታ ዴቫን ፒትርን ያንቲ ፒትር ቭራታሃ ብሁታኒ ያንቲ ብሁቴያ ማድ ያጂኖ ፒ ያንቲ ማም (ብጊ 9 25) እንዲሁም ሁሉ ወደ አለማዊ ገነት ውስጥ ለመግባት: በዚህ አለም ላይ መዘጋጀት ትችላላችሁ:: ወይንም እዚህ አለም ላይ በተሻለ ህብረተሰብ ውስጥ ለመወለድ መዘጋጀትም ትችላላችሁ:: ወይንም ጎስቶች ያሉበት እና የሚቆጣመሩበት ፕላኔትም ለመሄድ ይቻላል:: ወይንም ደግሞ ጌታችን ክርሽና ወደ አለበት ፕላኔትም መሄድ ይቻላል:: ሁሉም ነገር ለሰው ልጅ ክፍት ነው:: "ያንቲ ብሁቴጅያ ብሁታኒ ማድ ያጂኖ ፒ ያንቲ ማም" እራሳችሁን ማዘጋገት ብቻ ነው የሚገባችሁ:: ልክ በወጣት ግዜያችሁ ትምህርት ትማራላችሁ:: ከዚያም አንዱ ኤንጂንዬር ሊሆን ይችላል:: ሌላው የመድሃኒት ትምህርት ተምሮ ይመረቅ ይሆናል:: ሌላው የህግ ምሩቅ ሊሆን ይችላል:: እዲሁም ብዙ ባለሙያዎች ይመረቃሉ:: ለዚህ ሁሉ የሚዘጋጁትም በትምህርት ነው:: እንደዚህም ሁሉ ለወደፊት ትውልዳችሁ አሁን መዘጋጀት ትችላላችሁ:: ይህ ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም:: ሰዎች ከሞት በኋላም ህይወት እንዳለም አያምኑም:: ምንም እንኳን ለመረዳት ቀላል ቢሆንም:: ከሞት በኋላም ህይወት እንዳለ የምንረዳው ክርሽና ስለ ነገረን ነው:: በትንሽም እውቀት ይህን ፍልስፍና: ሌላ ህይወት እንደሚኖረን እንረዳለን:: ስለዚህ የእኛ አሰተያየት: "ለሚቀጥለው ህይወታችሁ አሁን የምትዘጋጁ ከሆነ: ለምን ወደ መጣንበት የአማላካችን ቤት ተመልሰን ለመሄድ ጥረት አናደርግም? ይህ ነው የእኛ አሰተያየት::