AM/Prabhupada 0065 - እያንዳንዱ ሰው ደስተኛ ይሆናል፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Arrival Lecture -- Gainesville, July 29, 1971

እንግዳ: በህብረተሰባችሁ ውስጥ:ለሌላ ሰዎች ቦታ አለ? ይህም ክርሽናን በቀጥታ ባልሆነ መንገድ: ማለትም ቤተ መቅደስ እየኖሩ ሙሉ ቀን ከመዘመሩ ሌላ: ፕራብሁፓዳ:አይደለም:የእኛ መመሪያ እንዲህ ነው:ለምሳሌ ውሃን በዛፉ ስር ላይ ብታጠጡ: ይህ ውሃ በዛፉ ቅጠላ ቅጠል:ግንዶች እና ቅርንጫፎች ሁሉ ይሰራጫል:ዛፉም የለመለመ ሊሆን ይችላል: ነገር ግን ቅጠሉን ብቻ የምታጠጡት ከሆነ ቅጠሉም ይደርቃል:ቅርንጫፎቹም ሁሉ ይደርቃሉ: ምግባችሁን ወደ ሆዳችሁ ከላካችሁት: የሰውነታችሁ ሃይል ወደ ጣቶቻችሁ: ወደ ፀጉራችሁ: ወደ ጥፍራችሁ ሁሉ ይሰራጫል: ምግቡን ግን ወደ ሆድ ሳይሆን እጃችሁ ላይ ብቻ ብታስቀሩት:ምንም ፋይዳ አይኖረውም: ምግቡም ይባክናል: ይህም የበጎ አድራጎት ስራ ሁሉ የክርሽና ንቃት ከሌለው የሚባክን በጎ አድራጎት ይሆናል: በብዙ መንገድ የሰው ልጅ ህብረተሰብን ለመርዳት እየሞከሩ ነው: ነገር ግን ሁልግዜ ፋይዳ ቢስ እይሆነ እና በውጤቱ አለመደሰት አለ: ይህም የክርሽና ንቃት ስለሞሚጎለው ነው: ሰዎች እንዴት የክርሽና ንቃትን እንደሚያዳብሩ ከተማሩ:ሁሉም ሰው ደስተኛ ይሆን ነበረ: ስለዚህም ይህን ህብረተሰብ የሚገባ:የሚያዳምጥ:የሚተባበር ሁሉ ደስተኛ ይሆናል: ስለዚህ የእኛ መመሪያ የተፈጥሮ መመሪያ ነው: አምላክን መውደድ:አምላክንም የመውደድ ችሎታችን የዳበረ ከሆነ:በተፈጥሮአችን ሁሉንም ሰው መውደድ እንችላለን: ልክ እንደ ንቃት ያለው ሰው:አምላክን ስለሚያፈቅር:እንስሶችንም ያፈቅራል: ወፎችንም:አውሬዎችንም:ሁሉንም ይወዳል: ግን እነዚህ በጎ አድራጊ ነኝ የሚሉ ግን: ለሰው ልጅ ፍቅር እያሳዩ: እንስሳዎችን ግን ይገሏቸዋል: ታድያ ለምንድን ነው እንስሳዎቹን የማይወዷቸው?ምክንያቱም የበጎ አድራጎት እንከን ስለአላቸው ነው: ነገር ግን የክርሽና ንቃት ያለው ሰው:እንሰሳ ከመግደል ፈጽሞ ይወገዳል:ለእንስሳዎችም ችግር አይፈጥሩባቸውም: ይህም የዩኒቨርሳዊ ፍቅር ነው: ወንድምህን እና እህትህን ብቻ የምታፈቅር ከሆነ:ይህ የዩኒቨርሳዊ ፍቅር አይደለም: ዩኒቨርሳል ፍቅር ማለት:ሁሉንም ማፍቀር ማለት ነው: ይህም የዩኒቨርሳል ፍቅር የሚመሰረተው:የክርሽናን ንቃት በማዳበር ነው:በሌላ መንገድ ሊሆን አይችልም: ሴት እንግዳ:እንደሰማሁት ከሆነ አንዳንድ ድቮቲዎች (አገልጋዮች) ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተዋል: ይህም ከወላጆቻቸው ጋር ስለሆነ:ይህም በቤተሰቡ ቅሬታ ፈጥሯል: ምክንያቱም ቤተሰቦቻቸው ይህንን ሊረዱት አይችሉም: ስለዚህ አንተ ይህን እንዲቀልላቸው ምን ልትላቸው ትችላለህ? ፕራብሁፓዳ: በክርሽና ንቃት ያለ ልጅ: ለቤተሰቡ:ለወላጆቹ:ለአገሩ ሰው:ለህብረተሰቡ:ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው: ክርሽና ንቃትስ ባይከተሉ:ምን አይነት ስራ ነበር ለወላጆቻቸው የሚሰሩት? ብዙዎቹም የተለያዩ ነበሩ: ነገር ግን: ልክ ፕራላድ ማሃራጅ ትለቅ ድቮቲ እንደነበረው ሁሉ አባቱ ደግሞ ድቮቲ ያልሆነ ነበር: አልፎ ተርፎም አባቱ በነርሺንጋዴቫ ተገደለ: ነገርግን ፕራህላድ የሚፈለገውን ምርቃት እንዲያገኝ ሲጠየቅ: እኔ ነጋዴ አይደለሁም:የእኔ ጌታ: እኔ በፍቅር ለአደረግሁት ስራ:ክፍያ አያስፈልገኝም: ይቅርታ ይደረግልኝእና: ንርሺምሃም በጣም ተደሰተ:“ይህ ነው ንጹህ ድቮቲ ማለት” ነገር ግን ይህም ንጹህ ድቮቲ ጌታውን እንዲህ ብሎ ጠየቀው: ጌታዬ ሆይ:አባቴ በአማላክ የማያምን ነበር:ብዙ ሃጥያትም ፈጽሞ ነበር: እኔ የምለንምህ ነገር ቢኖር:አባቴ ከእንዚህ ሃጥያቶች ሁሉ ነፃ እንዲወጣ ነበር: ንርሺማዴቫም እንዲህ አለ:“ለአባትህ አንተ ልጁ ስለሆንክ:አባትህ ወዲያውኑ ነጻ ወጥቷል” ”ብዙ ሃጥያትም ይፈጽም እንጂ:አንተ ልጁ ስለሆንክ እሱ ነጻ ወጥቷል“ አባትህም ብቻ ሳይሆን:የአባትህም አባት እንዲሁም እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ሁሉም ነፃ ወጥተዋል: እንደዚሁም ሁሉ አንድ ቫይሽናቫ በቤቱ ካለ:ከሃጥያት ነፃ የሚያወጣው አባቱን ብቻ ሳይሆን:አያቱንም ቅድም አያቱንም ወዘተ ነው: ይህ ነው በጣም ጥሩ የሆነው የቤተሰብ አገልግሎት: በነገራችን ላይ ይህ ለአንዱ ተማሪዬ ተከስቶ ነበር:“ካርቲኬያ” እናቱም የእኛን ህብረተሰብ ትወድ ነበር:አንዳንድ ግዜም እናቱን ለማየት ሲፈልግ: እናቱም “አንተ እዚህ ቁጭ በል እኔ የዳንስ ፓርቲ አለብኝ” ትለው ነበረ: ይህም ልጅ የክርሽና ንቃት ስለአለው: ለእናቱ ስለክርሽና ብዙውን ግዜ ያጫውታት ነበር: በሞት ደረጃም ላይ እያለች:ልጁን እንዲህ ብላ ጠየቀችው:“ያንተ ክርሽና የት አለ? ይኅውና!” ከዚያም ወዲያውኑ ሞተች: ይህም ማለት በሞት አፋፍ ላይ እያለች:ክርሽናን ለማስታወስ በቃች ማለት ነው:በዚህም ምክንያት ወዲያውኑ ከዚህ አለም ነጻ ለመውጣት ቻለች: ይህም በብሃገቨድ ጊታ ተገልጿል:“ያም ያም ቫፒ ስማራን ሎኬ ትያጃትዪ አንቴ ካሌቫራም (ብጊ 8 6 ) በሞት አፋፍ ያለ ሰው:ክርሽናን ለማስታወስ ከቻለ:ህይወቱ የተሳካ ሊሆን ይችላል: ታድያ ይህችም እናት:የክርሽና ንቃት ያለው ልጅ ስለአላት:ነፃ ወጣች: እንደዚሁም ሁሉ:ወደ ክርሽና ንቃተ ባህር እንኳን ሳትመጣ:ነጻነትዋን አገኘች: ስለዚህም ይህ ነው ጥቅሙ: