AM/Prabhupada 0066 - በክርሽና ፍላጎት መስማማት ይገባናል፡፡
Lecture on BG 16.4 -- Hawaii, January 30, 1975
አሁን ይህ የእኛ ምርጫ ነው:ወይ የአማላክ አገልጋይ መሆን ወይንም አለመሆን: ወይንም ሰይጣናዊ ሁኖ መቅረት:ይህ ይሆን ይሆናል ምርጫችን: ክርሽና እንዲህ ይላል:“ይህንን ሰይጣናዊ ባህርያችሁን እርግፍ አድራጋችሁ ጥላችሁ:ለእኔ ሙሉ ልቦናችሁን ስቶጡ” ይህ የክርሽና ፍላጎት ነው: ነገር ግን የክርሽናን ፍላጎት ለማሳካት የማትሹ ከሆነ: የራሳችሁን ፍላጎት ለሟሟላት የምትሹ ከሆነ: ክርሽናም ደስ ብሎት የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ ያሟላላችኋል: ነገር ግን ይህ ጥሩ አይደለም:የእኛ ምኞት የክርሽናን ፍላጎት ማሟላት መሆን አለበት: የእኛ ፍላጎት እና የሰይጣናዊ ምኞታችን እንዲያድግ ማድረግ የለብንም: ይህም “ታፓስያ” ይባላል: የእኛን ፍላጎቶች መስዋእት ማድረግ አለብን:ይህም መስዋእት ይባላል: መቀበል ያለብን የክርሽናን ፍላጎት ብቻ መሆን አለበት:ይህ ነው የብሃገቨድ ጊታ ትእዛዝ: የአርጁና ፍላጎት ጦር ሜዳው ላይ ላለመዋጋት ነበር: የክርሽና ፍላጎት ደግሞ ጦርነቱ እንዲካሄድ ነበረ:ይህም ከአርጁና ፍላጎት የተቃረነ ነበር: አርጁናም ወዲያውኑ ከክርሽና ምኞት ጋራ ስምምነት አደረገ:“እሺ” አለ “ካሪስዬ ቫቻናም ታቫ (ብጊ 18 73)”እሺ የአንተን ምኞት ተከትዬ ሃላፊነቴን እወጣለሁ“ ብሎ ተናገረ: ይህ ”ብሃክቲ“ ይባላል:የ”ብሃክቲ“ እና የ”ካርማ" ልዩነቱ ይህ ነው: “ካርማ” ማለት የግል የራሴን ፍላጎት ሟሟላት ማለት ነው:“ብሃክቲ” ማለት ደግሞ የክርሽናን ፍላጎት ሟሟላት ማለት ነው: ይህ ነው ልዩነቱ:አሁን የራሳችሁን ምርጫ ማድረግ ትችላላችሁ: ወይ የራሳችሁን ፍላጎት ለሟሟላት ምኞት ይኖራችኋል: ወይንም ደግሞ የክርሽናን ፍላጎት ለሟሟላት ምኞት ሊኖራችሁ ይችላል: የክርሽናን ፍላጎት ደግሞ ለሟሟላት ውሳኔ ካደረጋችሁ:ህይወታችሁ እንከን የሌለው እና ውጤታማ ይሆናል: ይህ ነው የእኛ የክርሽና ንቃተ ማህበር ኑሮ: “ክርሽና ይፈልገዋል:መስራት አለብኝ:ለራሴ ጥቅም ግን ጊዜዬን አላባክንም” ይን የቭርንዳቫና አስተሳሰብ ነው:የቭርንዳቨና ነዋሪዎች ሁሉ ጥረታቸው የክርሽናን ፍላጎት ብቻ ለሟሟላት ነው: እረኞቹ ሁሉ:ጥጃዎቹ ሁሉ:ላሞቹ ሁሉ:ዛፎቹ ሁሉ:አበባዎቹ ሁሉ: ውሃው:ጎፑዎቹ ሁሉ:እድሜያቸው የገፋ ነዋሪዎች ሁሉ:እናት ያሾዳ:አባት ናንዳ: እነዚህ ሁሉ የክርሽናን ፍላጎት ለሟሟላት የተሰማሩ ናቸው:ይህ ቭርንዳቫና ነው: ስለዚህ ይህንን አለማዊ ምድር ወደ ቭርንዳቫና ለመለወጥ ትችላላችሁ: መስማማት ያለባችሁ ግን:የክርሽናን ፍላጎት ለሟሟላት ፍላጎት እንዲኖራችሁ ነው:ይህ የቭርንዳቨን አስተሳሰብ ነው: የራሳችሁን ፍላጎት ለሟሟላት ፍላጎት ካላችሁ ግን:ይህ አለማዊ ነው: ይህ ነው የአለማዊ እና የመንፈሳዊ ልዩ ነቱ: