AM/Prabhupada 0101 - ጤነኛው ሕይወታችን ዘለዓለማዊውን የደስታ ሕይወትን ማግኘት ማለት ነው፡፡

Revision as of 09:23, 23 April 2015 by YamunaVani (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0101 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1974 Category:AM-Quotes - C...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid source, must be from amazon or causelessmery.com

Press Conference -- April 18, 1974, Hyderabad

እንግዳ 1:የክርሽና ንቃት የመድረሻ አላማው ምንድን ነው? ፕራብሁፓዳ:የመድረሻ አላማው አይደለም:ለማለትም እምፈልገው:የመድረሻ አላማው:እንደምናውቀው በአለም ላይ: የመንፈስ እና የአለማዊ ንጥረ ነገሮች አሉ: ምድራዊ አለም እንደአለም ሁሉ መንፈሳዊ አለምም አለ: ”ፓራስ ታስማት ቱ ብሃቫህ አንያህ አቭያክታህ አቭያክታት ሳናታናሃ (ብጊ 8.20) መንፈሳዊ አለም: ዘለአለማዊ ነው:ይህ ምድራዊ አለም ደግሞ: ግዜያዊ ነው: እኛ ደግሞ መንፈሳዊ ነፍስ ነን:ዘለአለማዊም ነን: ስለዚህ የእኛ ጥረት ሁሉ ወደ መንፈሳዊ አለም ለመመለስ ነው: በዚህ አለም ላይ ቀርተን:ገላችንን ከመጥፎ መጥፎ ወይንም ወደ ጥሩ አለማዊ ገላ እየለዋወጡ ለመኖር: ምንም ምኞት የለንም: ይህ ነው የእኛ ስራ:ይህ አለም ህመማችን ነው: የእኛ ጤነኛ ህይወት የዘላለማዊ ኑሮን ስንደሰት ነው: “ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሃማ ፓራማም ማማ” (ብጊ15 6) አያችሁ?ይህ የሰው ህይወታችንንም:ይህን ብቁ የሆነ ደረጃን ለማግኘትን: ጥረት ለማድረግ እንድንጠቀምበት ያስፈልጋል: ለሚለዋወጥ ነገር: ሌላ አለማዊ ገላ ይዘን እንድንወለድም ጥረት ማድረግ አይገባንም:ይህ ነው የህይወታችን አላማ: እንግዳ 3:ይህ ለመንፈሳዊነት ብቁ መሆን: በአንድ የሰው እድሜ ይቻላልን? ፕራብሁፓዳ:አዎን እንዲያውም በአንድ አፍታ ወይንም ቅፅበት ይቻላል:ይህም ከተስማማችሁ ነው: ክርሽና እንዲህ ብሏል:“ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ አሃም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሺያዪሽያሚ ማ ሹቻሃ” (ብጊ18 66) በዚህ አለም ገላችንን የምንቀያይረው:በሀጥያታዊ ተግባራችን ነው: ነገር ግን ለክርሽና ሙሉ ልቦናችንን ከሰጠን እና የክርሽና ንቃትን ከወሰድን:በአንድ አፍታ ወይንም በቅፅበት ወድ መንፈሳዊ መድረክ መስፈር እንችላለን: “ማም ቻዮ ቭያብሂቻሬና ብሃክቲ ዮጌና ሴቫቴ ሳጉናን ሳማቲያይታን ብራህማ ብሁያያ ካልፓቴ” (ብጊ14 26) ልክ ንጹህ የሆነ ድቮቲ ደረጃ ላይ እንደደረሳችሁ:ይህን የአለማዊ ጉጉቶችን በቀላሉ ለማለፍ ትችላላችሁ: “ብራህማ ብሁያያ ካልፓቴ” በመንፈሳዊ መድረክም ላይ ትሰፍራላችሁ: በዚህም በመንፈሳዊ መድረክ ላይ ህይወታችሁን ብታልፉ:በቀጥታ ወደ መንፈሳዊ አለም ትሄዳላችሁ: