AM/Prabhupada 0101 - ጤነኛው ሕይወታችን ዘለዓለማዊውን የደስታ ሕይወትን ማግኘት ማለት ነው፡፡
Press Conference -- April 18, 1974, Hyderabad
እንግዳ 2:የክርሽና ንቃት የመድረሻ አላማው ምንድን ነው?
ፕራብሁፓዳ:የመድረሻ አላማው አይደለም:ለማለትም እምፈልገው:የመድረሻ አላማው:እንደምናውቀው በአለም ላይ: የመንፈስ እና የአለማዊ ንጥረ ነገሮች አሉ: ምድራዊ አለም እንደአለም ሁሉ መንፈሳዊ አለምም አለ: ”ፓራስ ታስማት ቱ ብሃቫህ አንያህ አቭያክታህ አቭያክታት ሳናታናሃ (ብጊ 8.20) መንፈሳዊ አለም: ዘለአለማዊ ነው:ይህ ምድራዊ አለም ደግሞ: ግዜያዊ ነው: እኛ ደግሞ መንፈሳዊ ነፍስ ነን:ዘለአለማዊም ነን: ስለዚህ የእኛ ጥረት ሁሉ ወደ መንፈሳዊ አለም ለመመለስ ነው: በዚህ አለም ላይ ቀርተን:ገላችንን ከመጥፎ መጥፎ ወይንም ወደ ጥሩ አለማዊ ገላ እየለዋወጡ ለመኖር: ምንም ምኞት የለንም: ይህ ነው የእኛ ስራ:ይህ አለም ህመማችን ነው: የእኛ ጤነኛ ህይወት የዘላለማዊ ኑሮን ስንደሰት ነው: “ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሃማ ፓራማም ማማ” (ብጊ 15.6) አያችሁ?ይህ የሰው ህይወታችንንም:ይህን ብቁ የሆነ ደረጃን ለማግኘትን: ጥረት ለማድረግ እንድንጠቀምበት ያስፈልጋል: ለሚለዋወጥ ነገር: ሌላ አለማዊ ገላ ይዘን እንድንወለድም ጥረት ማድረግ አይገባንም:ይህ ነው የህይወታችን አላማ:
እንግዳ 3:ይህ ለመንፈሳዊነት ብቁ መሆን: በአንድ የሰው እድሜ ይቻላልን?
ፕራብሁፓዳ:አዎን እንዲያውም በአንድ አፍታ ወይንም ቅፅበት ይቻላል:ይህም ከተስማማችሁ ነው: ክርሽና እንዲህ ብሏል:“ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ አሃም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሺያዪሽያሚ ማ ሹቻሃ” (ብጊ 18.66) በዚህ አለም ገላችንን የምንቀያይረው:በሀጥያታዊ ተግባራችን ነው: ነገር ግን ለክርሽና ሙሉ ልቦናችንን ከሰጠን እና የክርሽና ንቃትን ከወሰድን:በአንድ አፍታ ወይንም በቅፅበት ወድ መንፈሳዊ መድረክ መስፈር እንችላለን: “ማም ቻዮ ቭያብሂቻሬና ብሃክቲ ዮጌና ሴቫቴ ሳጉናን ሳማቲያይታን ብራህማ ብሁያያ ካልፓቴ” (ብጊ 14.26) ልክ ንጹህ የሆነ ድቮቲ ደረጃ ላይ እንደደረሳችሁ:ይህን የአለማዊ ጉጉቶችን በቀላሉ ለማለፍ ትችላላችሁ: “ብራህማ ብሁያያ ካልፓቴ” በመንፈሳዊ መድረክም ላይ ትሰፍራላችሁ: በዚህም በመንፈሳዊ መድረክ ላይ ህይወታችሁን ብታልፉ:በቀጥታ ወደ መንፈሳዊ አለም ትሄዳላችሁ: