AM/Prabhupada 0139 - ይህም መንፈሳዊ ግኑኝነት ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on SB 3.25.38 -- Bombay, December 7, 1974

ክርሽናን ከወደድን:አለማዊ ነገሮች ሁሉ አያሳስቱንም ማለት ነውን? ወይ እንደ አለቃህ ትወደዋለህ በዚህ አለማዊ ላይ ያለ አለቃ:እስከ አገለገላችሁት ድረስ:ደስተኛ ነው: ሰራተኛውም ደሞዝ እስከተከፈለው ድረስ:ደስተኛ ነው: በመንፈሳዊ አለም ግን:እንደዚህ አይነት ቅንብር የለም: በተለያየ ምክንያት ለማገልገል ካልቻልክ:አለቃህ ደስተኛነቱ አያቆምም አገልጋዩም:አለቃው ባይከፍለው:ቅሬታ የለውም: ይህ አንድነት እና ፍጹም የሆነ ግኑኝነት ነው: ለዚህም ምሳሌ አለን: በዚህ ድርጅታችን ውስጥ:ብዙ ተማሪዎች አሉን: የምንከፍለው ነገር ግን የለንም:እነርሱም የተፈለገውን ስራ ሁሉ ይሰራሉ: ይህ የመንፈሳዊ:ዝምድና ነው: አንዴ:ጃዋሃርላል ኔህሩ ለንደን ተቀምጦ ነበር: አባቱም ሞቲላል ኔህሩ 300 ሩፒ ሰራተኛ እንዲቀጥርበት ሰጥቶት ነበረ: አንድ ግዜም ፓንዲታ ወደ ለንደን ሲመጣ:ሰራተኛ እንደ አልተቀመጠ ተረዳ: ፓንዲታም ሰራተኛው የታለ ብሎ ጠየቀው: እርሱም እንዲህ መለሰ:“ሰራተኛ ምን ያደርግልኛል?ሰራ የለም:ሁሉን እኔ ራሴ እሰራዋለሁ” ብሎ መለሰለት: እርሱም እንዲህ አለው:“አይደለም:እኔ የፈለግሁት የእንግሊዝ ሰው አገልጋይህ እንዲሆን ነው” ስለዚህም መክፈል ጀመረ ማለት ነው:ይህም ምሳሌ ነው: እኔ ግን በመቶ እና በሺህ የሚቆጠሩ አገልጋዮች አሉኝ:ነገር ግን የምከፍለው የለኝም: ይህ የመንፈሳዊ ዝምድና ነው: የሚያገለግሉትም ስለሚከፈላቸው አየደለም:ምን የምከፍለው አለና ነው? እኔ ድሃ ህንዳዊ ነኝ: ምን መክፈል እችላለሁ?ነገር ግን አገልጋዩ በመንፈሳዊ ፍቅር የተነሳ ያገለግላል: እኔም ያለ ደሞዝ አስተምራቸዋለሁ:ይህ መንፈሳዊ ነው: “ፑናሽያ ፑርናም አዳያ (ኢሾ ጥቅሶች) ሁሉም ነገር ሙሉ ነው: ስለዚህም ክርሽናን:እንደ ልጃችሁ:እንደ ጓደኛ:እንደ አፍቃሪ አድርጋችሁ ብትቀበሉት:ልትታለሉ አትችሉም: ክርሽናን ለመቀበል ሞክሩ: ይህንን ሃሰታዊ እና ምትሃታዊ:አገልጋይ:ልጅ:አባት ወይንም ፍቅረኛን ተውት:ልትታለሉ ስለምትችሉ: