AM/Prabhupada 0163 - ሀይማኖት ማለት በአብዩ ጌታ የተሰጠ ሕግጋት እና መመሪያ ማለት ነው፡፡

The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.


Lecture on BG 4.3 -- Bombay, March 23, 1974

የህይወታችን አላማ:ወደ መጣንበት ቤት ወደ አምላካችን ቤት መመለስ ነው: አሁን በእዚህ በአለማዊ ወሳኝ ምድር ላይ ወድቀናል: እየተሰቃየን ነው:ነገርግን አናውቀውም: ሞኞች ነን:ልክ እንደ እንስሳ: የህይወታችንም አላማ ምን እንደሆነ አናውቀውም: የህይወታችን አላማ:በብሃገቨድ ጊታም ተጠቅሷል:“ጃንማ ምርትዩ ጃራ ቭያድሂ ዱክሃ ዶሳኑዳርሻናም” (ብጊ 13 9) ይህንንም ስንረዳ:“ይህ የተደጋገመ መወለድ:መሞት:ማርጀት:መታመም:ይህንን ሁሉ አልፈልግም” ስንል: ማንም ለመሞት አይፈልግም ነገር ግን:ሞት መምጣቱ ግድ ነው: እንዲህም አያስብም:“ይህ የእኔ ችግር ነው:መሞት አልፈልግም:ሞት ግን በእርግጥ ይመጣል” ይህ ነው ችግሩ:ማንም ሰው እነዚህን ችግሮች ለመፍታት አይጠነቀቅም: የተሰማሩትም በግዜያዊ ችግሮች ላይ ብቻ ሁኖ ይገኛል:እነዚህ ጊዝያዊ ችግሮች ግን ችግሮቻችን አይደሉም: ትክክለኛው ችግር ግን እንዴት ሞትን እንደምናቆም ነው:እንዴት መወለድን እንደምናቆም:እንዴት እርጅናን እንደምናቆም:እንዲሁም እንዴት በሽታን እንደምናቆም ነው:ይህ ነው ትክክለኛው ችግራችን: ይህ ሊሰራ የሚችለው ደግሞ ከዚህ አለማዊ ኑሮ ነፃ ስንሆን ነው:ይህ ነው ችግራችን: ስለዚህ ክርሽና እዚህ እንደገና ይመጣል: “ያዳ ያዳ ሂ ድሃርማስያ ግላኒር ብሃቨቲ ብሃረታ” (ብጊ 4 7) ድሃርማስያ ግላኒር ግላኒር ማለት ሲበላሽ ወይንም መንገድ ሲስት ማለት ነው:ሰዎች በሃይማኖት ስም የራሳቸውን ሃሳብ እየፈጠሩ ይገኛሉ: ”ይህ የእኛ ሃይማኖት ነው“ “ይህ የሂንዱ ሃይማኖት ነው” “ይህ የእስላም ሃይማኖት ነው” “ይህ የቡድሃ ሃይማኖት ነው” “ይህ የሲክ ሃይማኖት ነው” እንደዚህም እያደረጉ ብዙ ሃይማኖቶች ፈጥረዋል: ነገር ግን ትክክለኛ ሃይማኖት ”ድሃርማ ሳክሳድ ብሃጋቨት ፕራኒታም“ (ሽብ 6 3 19) ሃይማኖት ማለት በአማላክ የተሰጠ መመሪያ እና ህግ ማለት ነው:ይህ ሃይማኖት ነው: ቀላሉም የሃይማኖት ትርጉም:”ድሃርማ ቱ ሳክሳድ ብሃገቫት ፕራኒታም“ (ሽብ 6 3 19). ልክ ህግ በመንግስት እንደሚደነገገው: ህግን እራሳችሁ መፍጠር አትችሉም:ከዚህ በፊት እንደገለፅኩት: ህግ በመንግስት እንደሚፈጠረው:ሃይማኖት ደግሞ በአምላክ ይፈጠራል: የአምላክን ሃይማኖት ከተቀበላችሁ:ይህ ሃይማኖት ማለት ነው: የአምላክ ሃይማኖት ምንድን ነው? እዚህ ጋ ቁም:ሌሎች እያዩ ነው: የአምላክ ሃይማኖት:ይህንን በብሃገቨድ ጊታ ታገኙታላችሁ: ”ሳርቫ ድሃርማ ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ“ (ብጊ 18 66) ይህ የአምላክ ሃይማኖት ነው: ሌሎቹን ሰሜት የማይሰጡ ሃይማኖቶች ተውት: ክርሽና እንዲህ ብሏል “የእኔ ድቮቲ ሁኑ:ሙሉ ልቦናችሁን ስጡኝ” ይህ ሃይማኖት ነው: