AM/Prabhupada 0162 - የብሀገቨድ ጊታን መልእክት በልቦናችሁ አሳድሩ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

Simply Carry the Message of Bhagavad-gita - Prabhupāda 0162


Press Interview -- October 16, 1976, Chandigarh

በህንድ አገር ውስጥ:ብዙ ስለ ነፍስ ስራ የሚያስተምሩ የቬዲክ መፃህፍቶች አሉ: በሰው ልጅ ትውልድ ደግሞ:ስለ መንፈሳዊ ህይወታችን ፍላጎት ካላደረብን:ልክ ራስን እንደመግደል ይቆጠራል: በህንድ አገርም ተወልደው የነበሩ ታላላቅ አስተማሪዎችም መልእክት ይኅው ነበር: በቅርብ የነበሩ አቻርያዎች (በአርአያ የሚያስተምሩ) ከዚህ ቀደም:ብዙ ታላላቅ አቻርያዎች ነበሩ:እንደ እነ ቭያሳዴቭ እና ሌሎች: ዴቫላ እና ሌላ ብዙ አቻርያዎች: ባለፉት 1500 አመታትም ብዙ አቻርያዎች ነበሩ: እንደነ ራማኑጃ:ማድሃቨ አቻርያ:ቪሽኑስዋሚ: በ500 አመታት ውስጥ ደግሞ:እንደ ጌታ ቼይታንያ ማሃፕራብሁ: እነዚህ ሁሉ ብዙ መንፈሳዊ መጻህፍትን ትተውልን ሂደዋል: በአሁኑ ግዜ ግን ይህ መንፈሳዊ እውቀት ተዘንግቷል: ስለዚህም ጌታ ቼይታንያ ማሃ ፕራብሁ:መልእክቱን ለመላው አለም አስተላልፏል: ሁላችሁም ጉሩ ወይንም መንፈሳዊ መምህር ሁኑ: ታድያ እንዴት ነው ሁሉም መንፈሳዊ መምህር ለመሆን የሚችለው? የመንፈሳዊ አባት መሆን ቀላል ስራ አይደለም: አንድ ሰው የተማረ ወይንም ስለመንፈሳዊ እውቀት ምሁር መሆን አለበት:ሰለ ነፍስ እና ሁሉ የተያያዘውን ነገር መረዳት አለበት ነገርግን ቼይታንያ ማሃፕራብሁ ትንሽ ፎርሙላ ሰጥቶናል: ብሃገቨድ ጊታን በትክክል ከተከተልን:መልእክቱንም ከሰበክን:ያኔ ጉሩ ሆንን ማለት ነው: በቤንጋል ለዚህ የተሰጠው ቃል:“ያሬ ዴክሃ:ታሬ ካሃ: ክርሽና ኡፓዴሽ” (ቼቻ 7 128) ጉሩ መሆን አስቸጋሪ ነው:ነገር ግን የብሃገቨድ ጊታን መልእክት ከሰበካችሁ: እና ያገኛችሁትን ሰው ለማስረዳት ከቻላችሁ: ጉሩ ሆናችሁ ማለት ነው: ስለዚህ ይህ የክርሽና ንቃት ማህበር:የተቋቋመው ለዚሁ አላማ ነው: እኛም ብሃገቨድ ጊታን ሳንቀይር እንደ አለ:እያቀረብን ነው: