AM/Prabhupada 0419 - ድቁና ማለት የክርሽና ንቃታችሁ 3ኛ ደረጃ ማለት ነው፡፡: Difference between revisions

(Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0419 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1968 Category:AM-Quotes - L...")
 
m (Text replacement - "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->" to "<!-- END NAVIGATION BAR --> <!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->")
 
Line 7: Line 7:
[[Category:AM-Quotes - in USA, Seattle]]
[[Category:AM-Quotes - in USA, Seattle]]
<!-- END CATEGORY LIST -->
<!-- END CATEGORY LIST -->
<!-- BEGIN NAVIGATION BAR -- DO NOT EDIT OR REMOVE -->
{{1080 videos navigation - All Languages|Amharic|AM/Prabhupada 0417 - በዚህ ሕይወት እና በሚቀጥለው ሕይወታችሁ ደስተኞች ሁኑ፡፡|0417|AM/Prabhupada 0421 - የመሀ ማንትራን ስትዘምሩ ማስወገድ የሚኖርባችሁ ሀጥያቶች ከ1 እስከ 5|0421}}
<!-- END NAVIGATION BAR -->
<!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->
<!-- BEGIN ORIGINAL VANIQUOTES PAGE LINK-->
<div class="center">
<div class="center">
Line 19: Line 22:


<!-- BEGIN AUDIO LINK -->
<!-- BEGIN AUDIO LINK -->
<mp3player>http://vaniquotes.org/w/images/681020IN.SEA_clip6.mp3</mp3player>
<mp3player>https://s3.amazonaws.com/vanipedia/clip/681020IN.SEA_clip6.mp3</mp3player>
<!-- END AUDIO LINK -->
<!-- END AUDIO LINK -->



Latest revision as of 06:06, 29 November 2017



Lecture & Initiation -- Seattle, October 20, 1968

ይህ የድቁና ስርዓት ማለት የክርሽና ንቃት የሶስተኛው ደረጃ ማለት ነው፡፡ እነዚህም በድቁና ስርዓት በመሰማራት የሚገኙት ሁሉ የተደነገጉትን የክርሽና ንቃት ሕግጋት እና መመሪያ በትክክል መከተል አለባቸው፡፡ ልክ ከበሽታ ለመዳን እንደሚፈልግ በሽተኛ ሀኪም የሚሰጠውን ትእዛዝ በጥሞና መከታተል አለበት፡፡ ከበሽታውም በቶሎ እንዲድን ሊያደርገው የሚችለው ይኅው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን አራቱን መመሪያዎች በትክክል መከተል ያሰፈልጋችኃል፡፡ 16 ዙርያም የክርሽናን ቅዱስ ስም መዘመር ያስፈልጋችኋል፡፡ ይህንንም ስርዓት በመከተል ቀስ በቀስ በዚህ በመነሳሳት ለክርሽና ንቃት ጣእሙ እና ቅርበቱ እያደገ ይመጣል፡፡ ከዚያም የክርሽና ፍቅር አውቶማቲካሊ ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም ፍቅር በልባችን ውስጥ ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ ይህ ለክርሽና ያለን ፍቅር ከውጪ የሚመጣ አስገድደን የምናመጣው ነገር አይደለም፡፡ ይህም ሁሉ ቦታ እና ከሁሉም ፍጥረታት ጋር ያለ ነው፡፡ አለበለዛም በውስጣቸው ባይኖር ኖሮ እንዴት እነዚህ አሜሪካን ልጆች እና ልጃገረዶች ሊያነቃቁት ቻሉ? ይህም ፍቅር በውስጣችን ያለ ነው፡፡ እኔ በማነቃቃት ብቻ እየረዳሁ እገኛለሁ፡፡ ልክ እንደ ክብሪት፡፡ ክብሪት እሳት አለው፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው መጫር ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ እሳት በውስጡ ያለ ነው፡፡ ሁለቱን እንጨቶች ብቻ በማነካካት እሳት ላይገኝ ይችላል፡፡ ይህም የእሳቱ ኬሚካል ከላይ ባይኖር ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ክርሽና ንቃት በሁሉም ልብ ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡ የሚያስፈልገው ግን በክርሽና ንቃት ማህበር በመሳተፍ ይህንን ፍቅር ማነቃቃት ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ሰለዚህ ይህ አስቸጋሪም ሆነ ተግባራዊ ወይንም የማያጓጓ ያልሆነ አይደለም፡፡ ሁሉም ነገር ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ሰለዚህ ሁሉንም የምንጠይቀው ነገር ቢኖር ይህንን በጣም ምህረታዊ የሆነውን የጌታ ቼታንያን ስጦታ ተቀበሉ፡፡ ይህም የክርሽና ንቃትን እና የሀሬ ክርችናን ቅዱስ ስም የመዘመርን ነው፡፡ በዚህም በጣም ደስተኞች ትሆናላችሁ፡፡ ይህ ነው ፕሮግራማችን፡፡ እናመሰግናለን፡፡