AM/Prabhupada 0417 - በዚህ ሕይወት እና በሚቀጥለው ሕይወታችሁ ደስተኞች ሁኑ፡፡

From Vanipedia


በዚህ ሕይወት እና በሚቀጥለው ሕይወታችሁ ደስተኞች ሁኑ፡፡
- Prabhupāda 0417


Lecture & Initiation -- Seattle, October 20, 1968

ሰለዚህ በዚህ በክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ በዚህም ሕይወታችሁ ሆነ በሚመጣው ደስተኛ ሁኑ፡፡ ለክርሽና ያላችሁን የፍቅር አገልግሎት በመስጠት ይህንን ሕይወታችሁን ብታሳልፉ ሕይወታችሁ መቶ በመቶ ተሳካ ማለት ነው፡፡ ይህ ካልተቻለ ግን ምንም ዓይነት ፐርሰንቴጅ ያህል እንኳን ብትሳተፉ ይህ መንፈሳዊ እርምጃ ሁሌ ከእናንተው ጋር ይሆናል፡፡ ሊጠፋም አይችልም፡፡ ይህም በብሀገቨድ ጊታ ውስጥ ተረጋግጧል። ሱቺናም ሽሪማታም ጌሄ ዮጋ ብህራስቶ ሳንጃያቴ (ብጊ፡ 6.41) ይህንን የዮጋ ስርዓት መቶ በመቶ ያላከናወነ ሰው ከሞት በኋላ ሕይወቱ በንፁህ ቤተሰብ ወይንም ሀብት ካለው ቤተሰብ በመወለድ መንፈሳዊ እርምጃውን እንዲቀጥል ዕድል ይሰጠዋል፡፡ ሁለት ዕድል ይሰጣል፡፡ ይህም ወይ በመንፈሳዊ ንፁህ ቤተሰብ ወይንም ደግሞ ሀብት ባለው ቤተሰብ ለመወለድ ዕድል ይሰጣል፡፡ በዚህም መንገድ ቢያንስ ቢያንስ ሰው ሆኖ የመፈጠር ዕድሉ የተረጋገጠ ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን የክርሽና ንቃት የማትከታተሉ ከሆነ የወደፊት ትውልዳችሁ ምን እንደሆነ ሊታወቅ አይችልም፡፡ ወደ 8,400,000 የሚሆኑ የተለያዩ ዓይነት ፍጥረታት በዚህ ትእይንተ ዓለም ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም አንዱ ሆነን ልንወለድ እንችላለን፡፡ እንደ ዛፍም ሆነን የምንወለድ ከሆነ .....ልክ በሳን ፍራንሲስኮ እንደአየሁት አንዱ ዛፍ ለ7000 ዓመት ቆሞ የቆየ ነው ይባላል፡፡ ለ7,000 ዓመታት በባህር ዳር ቆመው ይታያሉ፡፡ ”ልክ ልጆች በትምህርት ቤት ሲያጠፉ አግዳሚ ወንበር ላይ ቁም ተብለው በአስተማሪው እንደሚቀጡ“ እነዚህም ዛፎች በተፈጥሮ ሕግጋት ቁም ተብለው ተቀጥተው ይታያሉ፡፡ እንደዚህም ሁሉ ዛፍ የመሆን ውሻ የመሆን ድመት የመሆን እንዲሁም አይጥ ሆኖ የመወለዱም ዕድል አለ፡፡ ብዙ የተለያዩ ሕይወቶች ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ ይህንን ሰው ሆኖ የመወለድን ዕድል እንዳያመልጣችሁ ጥረት ማድረግ አለባችሁ፡፡ የክርሽናን ፍቅራችሁን አጠናክራችሁ በዚህ እና በሚመጣው ሕይወታችሁ ደስተኛ ሁኑ፡፡