AM/Prabhupada 0678 - በክርሽና ንቃት በማዳበር ላይ የሚገኝ ሁሉ በዮጋ ትኩረት የተሰማራ ነው፡፡

Revision as of 07:17, 23 June 2015 by Visnu Murti (talk | contribs) (Created page with "<!-- BEGIN CATEGORY LIST --> Category:1080 Amharic Pages with Videos Category:Prabhupada 0678 - in all Languages Category:AM-Quotes - 1969 Category:AM-Quotes - L...")
(diff) ← Older revision | Latest revision (diff) | Newer revision → (diff)


Invalid URL, must be MP3

Lecture on BG 6.25-29 -- Los Angeles, February 18, 1969

ቪሽኑጃን፡ ጥቅስ 27 ”መላ ሀሳቡ በእኔ ላይ የሚያተኩረው ዮጊ ከፍተኛውን ደስታ ሊያገኝ ይችላል፡፡“ ”ከብራህማን (ከአብዩ) ጋር ባለው ግኑኝነት ነፃነቱን አግኝቷል፡፡ በሀሳቡም ሰላምተኛ ነው፡፡“ ረጋ ካላለም መንፈስ ነፃ ወጥቷል፡፡ ከሀጥያትም ነፃ ነው፡፡ (ብጊ፡ 6.27)

ጥቅስ 28 ”በራስን በማወቅ ደረጃም ተረጋግቶ እና ከቁሳዊ ዓለም መበከልም ነፃ በመውጣት“ ”ይኅው ዮጊ ከፍተኛውን የትክክለኛ የደስታ ደረጃ አግኝቶ እና ከአብዩ ጌታ ጋር ቀርቦ ይታያል፡፡“ (ብጊ፡ 6.28)

ፕራብሁፓድ፡ ይህ ነው ትክክለኛ ደረጃ ላይ መሆን ማለት፡፡ ”ሀሳቡ ሁሉ በእኔ ላይ ያተኮረ፡፡“ እኔ ማለት ክርሽና ማለት ነው፡፡ ክርሽና እየተናገረ ነው፡፡ እኔ እንዲህ ብዬ የምጠይቅህ ከሆነ ”የሚጠጣ ውሀ ስጠኝ“ ውሀውን ለሌላ ሰው ለመስጠት አይገባህም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የብሀገቨድ ጊታ የተነገረው በክርሽና ነው፡፡ እርሱም ”እኔ“ ብሎ ይናገራል፡፡ ”እኔ“ ማለት ክርሽና ማለት ነው፡፡ ይህ ግልፅ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን ብዙ ሰለ ብሀገቨድ ጊታ ገለፃ የሚሰጡ አሉ፡፡ እነዚህም ክርሽና ከሚናገረው ውጪ እየወጡ ይገኛሉ፡፡ ለምን እንደሆነ ላውቀው አልችልም፡፡ ይህ ግን ይህ አታላይ ይዘት እንዳለው ግልጽ ነው፡፡ ሰለዚህ “እኔ” ሲባል ክርሽና ማለት ነው፡፡ እንደዚህም የክርሽና ንቃት ያለው ሰው በዮጋ ተመስጦ የሚገኝ ነው፡፡ ቀጥል