AM/Prabhupada 0008 - ክርሽና እንደገለፀው “እኔ የሁሉም አባት ነኝ፡፡”

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

Kṛṣṇa Claims That "I Am Everyone's Father" - Prabhupāda 0008


Janmastami Lord Sri Krsna's Appearance Day Lecture -- London, August 21, 1973

በህንድ አገር ውስጥ: ብዙ ታላላቅ ሰዎች: መንፈሳዊ ሰዎች: ቀሳውስቶች: እና መሪ መምህራኖች: እነዚህ ሁሉ: ብዙ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለትምህርት ቆንጆ አድርገው እና ሙሉ በሙሉ አዳብረው አዘጋጅተውልናል:: እኛ ግን ይህንን እድል እየተጠቀምንበት አንገኝም:: እነዚህም ቅዱስ ስነፅሁፎች እና መመሪያዎች: ለህንዶች: ለሂንዱ: ወይንም ለብራህመና (ቄሶች) ብቻ የተዘጋጁ አይደሉም:: እነዚህም ለሁሉም አለም ሰው የትዘጋጁ ናቸው:: ጌታ ክርሽናም እንዲህ ይላል [ብ ጊ 14 4 ] "ሳርቫ ዮኒሹ ኮንቴያ ሳምብሃቫንቲ ሙርታያህ ያህ ታሻም ማሃድ ብራህማ ዮኒር አሃምቢጃ ፕራዳ ፒታ" ጌታ ክርሽና እንዲህ ብሏል "እኔ የሁሉም አባት ነኝ" እንደ አባትነቱም ሁላችንን በደስታ እና በሰላም እንድንሆን ጥልቅ ምኞቱ ነው:: ልክ አባት ልጁን ደስተኛ እንዲሆንለት እንደሚፈልግ ሁሉ:: እንደዚሁም ሁሉ ጌታ ክርሽና ሁላችንም ደስተኛ እንድንሆንለት ይፈልጋል:: በዚህም ምክንያት አንድ አንድ ግዜ ወደ እኛ ዘንድ ወደ ምድር ይመጣል:: [ብ ጊ 4 7 ] "ያዳ ያዳ ሂ ድሃርማስያ ግላኒር ብሃቨቲ" ጌታ ክርሽናም የሚመጣበት ምክንያቱም ይህ ነው:: (ለማስደሰት) እና የጌታ ክርሽና አገልጋዮች ሁሉ: የጌታ ክርሽና ሚሽን ውስጥ መሳተፍ አለባቸው:: በሚሽኑ ውስጥ መሳተፍ አለባቸው:: ይህም የጌታ ቼታንያ ሚሽን ነው:: "አማራ አግናያ ጉሩ ሃና ታራ ዔ ዴሻ ያሬ ዴክሃ ታሬ ካሃ ክርሽና ኡፓዴሽ" [ ቼ ቻ 7 128] "ክርሽና ኡፓዴሽ" በብሃገቫድ ጊታ የተገለፀውን የጌታ ክርሽናን ለማስተማር ሞክሩ:: የሁሉም ህንዶች ሃላፊነት ይህ ነው:: ጌታ ቼይታንያ ማሃፕራብሁም እንዲህ አለ:: "ብሃራታ ብሁሚቴ ማኑሽያ ጃንማ ሃይላ ያራ ጃንማ ሳርትሃካ ካሪ ፓራ ኡፓካር" [ ቼ ቻ አዲ 9 41] እና የህንዶች ሃላፊነት "ፓራ ኡፓካር ነው" ህንዶች ሌላውን ለመበዝበዝ አይደለም የተፈጠሩት:: ይህ የህንዶች ስራ መሆን አይገባውም:: የህንዶች ታሪክ መያያዝ ያለበት ከ "ፓራ ኡፓካር" ጋራ ነው:: ከጥንት ግዜ ጀምሮ: ከመላው አለም: ቡዙ ሰው ወደ ህንድ አገር ለመንፈሳዊ ትምህርት ሲመጣ ይታያል:: ጌታ እየሱስ ክርስቶስም ወደ ህንድ አገር መጥቶ ነበር:: ከቻያናም ሆነ ከሌላ አገር ብዙ ሰው ይመጣ ነበር:: እኛ ግን ያለንን መንፈሳዊ ሃብት ረስተን እንገኛለን:: ይህም ምን ያህል ስለሰው ልጅ ስቃይ ግድ እንደሌለን ያሳያል:: ይህም ትልቅ የጌታ ክርሽና ንቃት እንስቃሴ በመላው አለም ላይ በመስፋፋት ላይ ይገኛል:: ነገር ግን የእኛ ህንድ ህብረተሰብ እና መንግስታችን ግድ ያላቸው አይመስልም:: ይህንን ከልብ የተቀበሉት አይመስልም:: ይህ የእኛ እድለቢስነት ነው:: ይህ የጌታ ቼታንያ ሚሽን ነው:: እርሱም እንዲህ ይላል: ህዶች ሁሉ "ብሃረታ ብሁሚቴ ማኑሻ ጃንማ" በህንድ ሰው ሁኖ የተፈጠረ ሁሉ: ይህንን የቬዲክ ስነጽሁፎ ች ሁሉ በመጠቀም: ህይወቱን የተሟላ ማድረግ ይገባዋል:: ትምህርቱንም በመላው አለም ማከፋፈል ይገባዋል:: ይህም "ፓራ ኡፓካር" ይባላል:: ህንድ ይሄን ማድረግ ትችላለች:: የአለም ህዝብ ይሄንም እያመሰገነ ነው:: ይህም ምን ያህል ታላቅ ትምህርት እንደሆነም: አውሮፓውያኖች: አሜሪካኖች: ሁሉ አመስግነው እየተቀበሉት ነው:: እኔም በቀን በቀን: ተማሪዎች ምን ያህል እንደተገለገሉበት: የሚገልፅ ደብዳቤ እየደረሰኝ ነው:: ይህም እርግጠንኛ ነው:: ይህም ለሞተ ሰው ህይወት እንደተሰጠው ተደረገ ማለት ነው:: እድዚሁም በማለት: ሁላችሁን ህንዶች እና በተለይም የክቡር እንግዳችንን: በትህትና እጠይቃለሁ:: ከዚህ እንቅስቃሴያችን ጋራ በመተባበር: የራሳችሁን እና የሌላውን ህይወት የተሳካ እንዲሆን አድርጉ:: ይህም የጌታ ክርሽና ሚሽን ነው:: የጌታ ክርሽና በአለም ላይ መምጣት ነው:: በጣም አመሰግናለሁ::