AM/Prabhupada 0009 - ትሁት የአምላክ አገልጋይ የሆነው ሌባ፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

The Thief Who Became A Devotee - Prabhupāda 0009


Lecture on SB 1.2.12 -- Los Angeles, August 15, 1972

ጌታ ክርሽና በብሃገቫድ ጊታ እንዲህ አለ:: [ብ ጊ 7 15] "ናሃምፕራካሻ ሳርቫስያ ዮጋ ማያ ሳማቭርታሃ" "እኔ ለሁሉም ግልጽ አይደለሁም:: "ዮጋ ማያ" ዮጋማያ ትሸፍነናለች:: ታድያ: እንዴት አማላክን ለማየት እንችላለን? ነገር ግን እነዚህ ተንኮለኞች አሉ:: እንደዚህም ይላሉ "አምላክን ልታሳየኝ ትችላለህ? አማላክን አይተኅው ታቃለህ?" አምላክ አሁን እንደ መጫወቻ ሁኖዋል:: "አማላክ ይኅውና:: ይህ የአምላክ ወልድ ነው" የሚል ይበዛል:: [ብ ጊ 7 15] "ና ማም ዱስክሪቲኖ ሙድሃህ ፕራፓድያንቴ ናራድሃማህ" እነዚህም ሀጥያተኞች: ተንኮለኞች: ሞኞች እና ከሰው ሁሉ ዝቅተኞች ናቸው እንዲህም እያሉ ይጠይቃሉ: “አማላክን ልታሰየኝ ትችላለህ?" ምን አይነት የተግባር ሥልጣኔ ቢኖርህ ነው: አማላክን ለይተህ አየተህ ለማወቅ የምትችለው? ለዚህ የሚያስፈልገው የተግባር ሥልጣኔ የሚከተለው ነው:: ይህስ ምንድን ነው? "ታክ ሸራዳድሃና ሙናያሃ" በመጀመሪያ ደረጃ: አንድ ሰው እምነት እንዲኖረው ያስፈልጋል:: እምነትኛ:: "ሽራዳድሃናህ" አማላክንም ለማየት በጣም ጉጉት ያለው ሰው መሆን አለበት:: እንዲሁ: ወደ አንድ ወገን በማዳላት እና: ቁም ነገር በሌለው ቀለድ: "እስቲ አማላክን አሳየኝ" ብሎ መጠየቅ አይገባም:: እንደ ማጂክ! አማላክ እንደ ማጂክ የሚፈጠር ይመስላቸዋል:: አይደለም:: አማላክን የሚሻ ሰው: በጣም ኮስተር ብሎ ለማየት መሻት አለበት:: እንዲህም ይላሉ: "አዎ: ማናልባት ፈጣሪ ካለ" "ስለ አማላክ ሰምተናል" "እና ማየት አለብን" ማለት አለብን:: ከዚህም የተያያዘ አንድ ታሪክ አለ:: ብትሰሙትም ጥሩ ምክር የያዘ ነው:: አንድ ባለ ሙያ የቅዱስ ብሃጋቫድ ጊታ ደጋሚ (አንባቢ) ነበር:: ሲያነብም: ጌታ ክርሽና በጣም በቆንጆ ጌጣ ጌጥ: አሸብርቆ እንደነበረ ያነብ ነበር:: እንደዚህም አሸብርቆ: ለላሞች እረኝነት ወደ ጫካ ይላክ ነበር:: ይህም ስለመሆኑ ሲነበብ አንድ የተረዳ ሌባ ነበረ:: ሌባውም እንዲህ ብሎ አሰበ:: "ለምን ወደ ቭርንዳቫን ሂጄ ይህንን ልጅ አልዘርፈውም?" "ብዙ ጌጣ ጌጥ ይዞ: በጫካ ውስጥ ይገኛል::" "እዚያም ሂጄ: ልጁን ይዤ: ጌማ ጌጡን ሁሉ መውሰድ እችላለሁ::" ፍላጎቱም ይሄ ነበር:: እንድዚሁም ሁኖ ልጁን ለማግኘት የፀና ሃሳብ አደረበት:: በዚህም መንገድ "በአንድ ሌሊት ሚሊዮኔር መሆን እችላለሁ" ብሎ አሰበ:: "ብዙ ጌጣጌጥ ይገኛል" ብሎ አስበ:: በዚህም ተነሳስቶ ጉዞውን ጀመረ:: ዋናው ጽኑ ሃሳቡም "ክርሽናን ማየት አለብኝ" የሚል ነበር:: "ክርሽናን ማየት አለብኝ" የሚለው የጸና ሃሳቡም: ጌታ ክርሽናን ለማየት እንዲበቃ አደረገው:: ጌታ ክርሽናንም ያገኘው ልክ ቅዱስ ብሃገቫት ውስጥ ደጋሚው እንደገለጸው ሁኖ ነው:: ልክ ክርሽናን እንደአየውም "ኦ ክርሽና አንተ በጣም ጥሩ ነህ" አለ:: እና ክርሽናን ማወደስም ጀመረ:: እንዲህም ብሎ አሰበ: "ቀስ በቀስ በማወደስ ጌጣጌጡን ሁሉ እወስዳለሁ" የመጣበትንም አላማ መግለጽ ጀመረ:: "አንተ ሃብታም ትመስላለህ: ትንሽ ጌጣጌጦችህን ልውሰድ?" ብሎ ጠየቀ:: ክርሽናም እንዲህ አለ: "አይሆንም: እናቴ በጣም ትቆጣለች: ስለዚህ አልችልም" ብሎ መለሰ:: ክርሽናም: በልጅነት አንደበት መለሰለት:: በዚህም ሁኔታ ሌባው: ወደ ክርሽና ያለው ጉጉት እያደገ መጣ:: በዚህም ወደ ክርሽና ባለው ቅርበቱ: ልቡ ንጹህ እየሆነ መጣ:: ከዚያም መጨረሻ ላይ: ክርሽና "እሺ መውሰድ ትችላለህ" አለው:: ከዚህም በኋላ: ሌባው ወደ ክርሽና አገልጋይነት ተቀየረ:: ይህም ወደ ክርሸና በመሰረተው ቅርበቱ ነው:: እንደዚህም ሁሉ በተገኘው መንገድ: ወደ ክርሽና ለመቅረብ መንገድ መፍጠር አለብን:: በተገኘው መንገድ:: በእንደዚህም ልባችን ንጹህ ሊሆን ይችላል::