AM/Prabhupada 0038 - እውቀት የሚገኘው ከቬዳዎች ስነፅሁፍ ነው፡፡



Lecture on BG 7.1 -- Hong Kong, January 25, 1975

አሁን ክርሽና እዚህ አለ:: አሁን የክርሽና ስእሎች አሉን: የክርሽና ፎቶዎች አሉን: የክርሽና ቤተመቅደሶች አሉን: ስለ ክርሽና ብዙ ነገሮች አሉን: እነዚህም ልብ ወለዶች አይደሉም:: ከሃሳባችን የመነጩም አይደሉም:: እንደ "ማያቫዲ" ፈላስፋዎች "በሃሳብህ እንደልብህ አምላክን መመሰል ትችላለህ" እንደሚሉት አይደለም:: አይደለም:: ፈጣሪ አምላክ በሃሳባችን ገምተን ሊመሰል አይችልም:: ይህ ሌላ ሞኝነት ነው:: እንዴት አድርጋችሁ የአምላክን ምሰል በግምት መመሰል ትችላላችሁ? እንዲህ ከሆነማ: ፈጣሪ አምላክ: በሃሳባችን የተፈጠረ አምላክ ይሆናል: ይህ ምንም ጥሬ ነገር የለውም:: ይህ አምላክ ሊሆን አይችልም:: በሃሳብ ተገምቶ የተፈጠረ አምላክ ሊሆን አይችልም:: ፈጣሪ አማላክ በፊት ለፊታችን ለመቅረብ የሚችል ነው:: ክርሽና በዚህ ምድር ላይ መጥቷል: “ታዳትማናም ስርጃሚ አሃም ሳምብሃቫሚ ዩጌ ዩጌ” ፈጣሪ አምላክን ያዩ ሰዎች: ይኖ ራሉ: ከእነርሱም መረጃ መውሰድ ትችላላችሁ: “ታድቪድሂ ፕራኒፓቴና ፓሪፕራሽኔና ሴቫያ ኡፓዴክሽያንቲ ቴ ግያናም ግያኒናስ ታትቫ ዳርሺና (ብ ጊ 4 34) ”ታትቫ ዳርሺና“ እራስህ ያላየህ ከሆነ: እንዴት ለሌላው መረጃ መስጠት ትችላለህ? እንደዚህም ፈጣሪ አምላክ በምድር ላይ ታይቷል:በታሪክ ብቻ አይደለም የተሰማው: ክርሽና በዚህ ምድር ላይ በነበረ ግዜ: ስለ ”ኩሩክ ሼትራ“ ታላቁ ጦርነት በታሪክ በደንብ ተተንትኖ ተጽፏል: ይህ ብሃጋቫድ ጊታም በዚህን ግዜ እንዴት እንደተነገረ በታሪክ በግልጽ ተተንትኖ ተጽፏል: ይህንን ሁሉ በታሪክ: በብሃጋቫን ሽሪ ክርሽና እና በሻሽትራ ቅዱስ መጽሃፎች መረዳት እንችላለን: ”ሻሽትራ ቻክሹስ“ በቅዱስ መጽሃፎች መረጃዎች ማየት: ልክ እንደ አሁኑ ግዜ: ክርሽና በአካሉ በምድር ላይ አይገኝም: ነገር ግን በእነዚህ በቅዱስ መፃህፍቶች ክርሽና ማን እንደሆነ መረዳት እንችላለን: ስለዚህ ”ሻስትራ ቻክሱሳ ሻስትራ" ወይ በቀጥታ መማር አለብን ወይንም ደግሞ ከሻስትራ ወይንም ቅዱስ መፃህፍቶች መማር አለብን: በግል ከምንማረው ደግሞ ከሻስትራ በቀጥታ የምንማረው የበለጠ ነው: የእኛም መንፈሳዊ እውቀት: የቬዲክ መመሪያዎችን የሚከተሉ ሁሉ: እውቀታቸው ሁሉ የሚመነጨው: ከቬዳ ቅዱስ መፃህፍቶች ነው: የቬዲክ እውቀትን ከሃሳባቸው በግምት አያመርቱትም: አንድ በቬዳ የተረጋገጠ ነገር:ሁል ግዜ እርግጠኛ ሁኖ ይገኛል: ክርሽናን በደንብ ልንረዳው የምንችለው በቬዳዎች ቅዱስ ስነፅሁፎች ነው: “ቬዳሽ ቻ ሳርቬይር አሃም ኤቫ ቬድያህ” (ብጊ15 15) ይህም በብሃጋቫድ ጊታ በደንብ ተገልጿል:ክርሽናን በሃሳባችሁ ልትገምቱት አትችሉም: ተንኮለኞች በሃሳባችን አምላክ ምን እንደሆነ እንገምታለን ቢሉ ይህ ተንኮለኝነት ነው: ክርሽናን ለማየት የምትችሉት የቬዳን ቅዱስ መፃህፍቶች በማንበብ በው: “ቬዳይሽ ቻ ሳርቬር አሃም ኤቫ ቬድያህ” (ብጊ 15 15) ይህ ነው የቬዳዎች አላማ: ስለዚህም “ቬዳንታ” ተብለው ይጠራሉ: የክርሽና እውቀት “ቬዳንታ” ነው: