AM/Prabhupada 0039 - የአሁኑ ዘመን መሪዎች ልክ እንደ አሻንጉሊት ወይንም ፓፔት ይቆጠራሉ፡፡

From Vanipedia


Modern Leader Is Just Like A Puppet - Prabhupāda 0039


Lecture on SB 1.10.3-4 -- Tehran, March 13, 1975

ልክ እንደ ዩዲስቲር የሆነ እንከን የሌለበት ንጉስ: የአገሩን መሬት እና ባህር ይቅርና: መላ ምድርን ሊገዛ ይችላል:: ይህ እንገን የሌለው ንጉስ ነው:: (ንባብ): "ፕሪሞ ጄኒቸር" የሚባለው የእንግሊዞች ህግ: የቤተሰብ ውርስን: በመጀመሪያ ለተወለደ ልጅ ያመራ ነበር: በጥንት ግዜም ንጉስ ማሃራጃ ዩድሂስቲር: ምድርን እና ባህሮቹን ሲገዛ: ይህን የመሰለ ህግ: ህብረተሰቡ ይከተል ነበር:: ይህም ህግ መላ አለምን ከእነ ባህሯ ይመለከት ነበር:: (ንባብ): "በዚያን ግዜ የሃስቲናፑር ንጉስ: (አሁን የደልሂ ወገን የሆነበት ስፍራ) : ያንን ግዜ ንጉሱ ባህርንም አጠቃሎ: የአለም ገዢ ነበር:: ይህም ግዛት እስከ ማሃራጅ ፓርክሺት: የማሃራጅ ዩዲስቲር የልጅ ልጅ ድረስ ተተላልፎ ነበር:: የንጉስ ማሃራጅ ዩዲስቲር ታናናሽ ወንድሞችም: እንደ ሚኒስቴር ሁነው: የተለያዩ ግዛቶችን ያስተዳድሩ ነበር:: በነዚህም መንፈሳዊ እና ክቡራን በሆኑ የንጉሳውያን ወንድማማቾች መሃከልም ሙሉ በሙሉ የሆነ ትብብር ነበረ:: ንጉስ ማሃራጅ ዩድሂስቲር: ምርጥ ንጉስ እና የጌታ ክርሽና አገልጋይ እና ተወካይ ነበረ:: ንጉስ የፈጣሪ አምላክ ክርሽና ተወካይ መሆን አለበት:: ይህም የአለምን ነገስታት ለማስተዳደር ነው:: ይህም የሚመሳሰለው እንደ ገነት ንጉስ: "ንጉስ ኢንድራ" ነው:: ደሚጎዶች (መላእክት) እነ ኢንድራ: ቻንድራ: ሱርያ: ቫሩና: ቫዩ: የመሳሰሉት:የህዋ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ፕላኔቶች የሚያስተዳድሩ ናቸው: እንደዚሁም ሁሉ ማሃራጅ ዩዲስቲር ከእነርሱ አንዱ ሁኖ ምድርን ያስተዳድር ነበር: ማሃራጅ ዩድሂስቲር እንደ አሁን ግዜ የዲሞክራሲ የፖለቲካ መሪዎች:የመንፈሳዊ ብልጽግና የሚጎለው መሪ አልነበረም: ማጃራጅ ዩድሂስቲር:በተከበረው ቢሽማዴቭ እና ፍጹም በማይወድቀው ጌታም: ትእዛዝ ይተዳደር ነበር: ስለዚህም ፍጹም ሙሉ እውቀት ነበረው: የአሁኑ ግዜ ተመርጦ የሚያገለግል የአገር መሪ:ልክ እንደ ፓፔት ይቆጠራል:ምክንያቱም የንጉሳትን የመሰለ ሃይል የለውም: እንደ ማሃራጅ ዩድሂስቲር ቢገለፅለት እንኳን: በራሱ ፍቃድ: በኮንስቲቲውሽናል ደረጃው ምክንያት ምንም ነገር ለማድረግ አይችልም: በዚህም ምክንያት በአለም ላይ ብዙ የሚቃረኑ እና የሚጣሉ ብዙ ህገ መንግስቶች ይገኛሉ: ይህም ወይ በአይዲዎሎጂ ልዩነት ወይም ደግሞ በግል ስስት የተነሳሳ ፍላጎት ሊሆን ይችላል: ነገር ግን እንደ ንጉስ ማሃራጅ ዩዲስትቲር የመሰለ ንጉስ የራሱ የሆነ አይደኦሎጂ የለውም: ይህም ንጉስ ይከተል የነበረውም:ፍጹም ወዳቂ ያልሆነውን የፈጣሪ አምላክን ትእዛዝ እና የአምላክ ተወካዮችን ትእዛዝ ነበር: እንዲ ሁም የአምላክ ሃይል የተሰጠውን ቢሽማዴቭን ነበር: በሻስትራ ቅዱስ መጻህፍቶች ውስጥ:ታላቅ የፈጣሪ ሃይል ያላቸውን አገልጋዮች እንድንከተል ተደንግጓል: እንዲሁም መከተል ያለብን ፍጹም ወዳቂ ያልሆነውን ፈጣሪ አምላካችንን ሲሆን: ይህም ያለ ምንም የራስ ጥቅም ፍላጎት እና በግል ያልተፈጠረ አይዲዎሎጂ ሳይጨመርበት ነው: በዚህም ስነስርአታዊ አመራት በመከተል: ማሃራጅ ዩድሂስቲር አለምን ከነባህርዋ ሊያስተዳድር በቅቶ ነበር: ምክንያቱም መመሪያዎቹ: ፍጹም እና ወዳቂ ያልነበሩ ነበር:ይህም አመራር በምድር ብቻ ሳይሆን በዩኒቨርስም ውስጥ የሚሰራ ነው: የአንድ አለም አመራር ሊሰራ የሚችለው:ይህን የመሰለ ፍጹም ሊወድቅ የማይችል አመራር ሲኖር ብቻ ነው: ወዳቂ የሆነ የሰው ዘር: ፍጹም የሆነ በአለም ላይ ሁሉም ሊቀበለው የሚችለውን አይዲዎሎጂ ሊፈጥር አይችልም: ፍጹም የሆነ እና ወዳቂ ያልሆነው ፈጣሪ አምላካችን ብቻ ነው:ይህን የመሰለ ፕሮግራም ሊፈጥር የሚችለው: ይህንንም በሁሉም ቦታ ሊቀበሉት የሚችሉ እና:መላ አለም ሊከተለው የሚችለው ይሆናል: ሰብአዊ ስሜት የሌለው መንግስት ሳይሆን: ጥሩ መሪው ሰው ነው ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው: መሪው ንጉስ ፍጹም የፈጣሪን ትእዛዝ የሚከተል ከሆነ:የሚያስተዳድረው መንግስትም በጣም ጥሩ አመራር ይኖረዋል: መሪው ሰው ግን ሞኝ ከሆነ: መንግስቱም የሞኞች ገነት ሁኖ ይቀራል:ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው: በአለም ላይ ብዙ ውድቀት ያላቸውን ንጉሶች እና የመንግስት ሃላፊዎችን በታሪክ አይተናል: ስለዚህም የመንግስት መሪዎች እንደ ማሃራጅ ዩድሂስቲር በደንብ በመንፈሳዊ ትምህርት የዳበሩ እንዲሆን ያስፈልጋል: ሙሉ የፈላጭ ቆራጭ ሃይልም እንዲኖራቸው ያስፈልጋል: የአለም ንጉስ ሊሰራ የሚችለው እንደ ማሃራጅ ዩድሂስቲር የሆነ እንከን የሌለው የአምላክ አገልጋይ መሪ ሲኖር ነው: በዚያን ግዜ መላው አለም በጣም ደስተኛ ነበረ:ምክንያቱም እንደ ማሃራጅ ዩዲስትር የመሰሉ መሪዎች በየክፍለ መንግስቱ ነበሩ: እነዚህ ንጉሳንም የማሃራጅ ዩዲስትርን ፈለግ ተከትለው:ለአለም ጥሩ አርአያ እና ምሳሌ ይፍጠሩ: ሞናርክም እንዴት ጥሩ መንግስት ሊፈጥር እንደሚችልም ይረዱት: ሁሉ ትእዛዞች ሁሉ በሻስትራ ቅዱስ መፃህፍቶች ውስጥ ተደንግገዋል:እንዚህም ነገስታቶች ይህንን መመሪያ ቢከተሉ ትክክለኛ አመራር ይኖራቸዋል: ሃይልም ይኖራቸዋል: በአመራራቸውም እንከን የለሽ ስለሚሆኑ: የጌታ ክርሽና የምድር ተወካዮች ይሆናሉ: ስለዚህም እንዲህ ተብሏል: “ካማም ቫቫርሻ ፓርጃንያሃ” (ሽ ብ 1 10 4) “ፓርጃንሃሃ” ማለት ዝናብ ማለት ነው: ዝናብ ለህይውታችን መሰረታዊ እና በጣም ወሳኝ የሆነ ሃብት ነው: ስለዚህም ክርሽና በብሃገቫድ ጊታ እንዲህ ብሏል:“አናድ ብሃቫንቲ ብሁታኒ ፓርጃናያድ አና ሳምብሃቫ” (ብጊ 3 14) የሰውን ልጅም ሆነ:እንስሳንም ለማስደሰት ከፈለጋችሁ: እንስሳዎችንም ጭምር: እነዚህ የመንግስት መሪዎች አንዳንድ ግዜ የሰውን ልጅ እንዴት እንደሚንከባከቡ ለማሳየት ይሞክራሉ: ነገር ግን የአገሪቱን እንስሳዎች ይዘነጓቸዋል: ለምን? ለምን ይህ እኩልነት ጠፋ? እንስሶችም እዚሁ በአገሪቱ ምድር ላይ ተወልደዋል:እነርሱም እንደኛ ህይወት ያላቸው ነፍሶች ናቸው: ምንም እንኳን እንስሳ ቢሆኑ እና እንደኛ እውቀት ባይኖራቸውም: በእርግጥ የራሳቸው የሆነ እውቀት አላቸው:ምንም እንኳን ይህ እውቀት እንደ የሰው ልጅ እውቀት ባይሆንም: ታድያ እውቀቱ ባይኖራቸው ከብት የማረጃ ቤት ከፍተን እንስሶችን መግደል ይገባናልን?ይህ ፍትህ ያለው አመራር ነው ማለት እንችላለን? ይህ ብቻ ሳይሆን ማንም ሰው እንኳን መንግስትን ለመጠጋት ሲመጣ:ንጉሱ መጠጊያ እንዲሰጣቸው ያስፈልጋል: ለምን ልዩነት ማድረግ ያስፈልጋል? ማንም ለጥገኝተት የሚመጣ ሰው እና “ጌታዬ እኔ በእርስዎ መንግስት ውስጥ መኖር እፈልጋለሁ” የሚል ሰው ጥገኝነት ሊሰጠው ይገባል: ለምን እንዲህስ ይባላል? ”አይፈቀድም:መግባት አትችልም:አንተ አሜሪካዊ ነህ:አንተ ህንድ ነህ:አንተ እንዲህ ነህ“ አይደለም:ብዙ ነገር መውጠንጠን ያስፈልገዋል:የአምላክንም መመሪያ ቢከተሉ ደግሞ: ይህም ማለት የቬዲክ ቅዱስ መመሪያዎችን ቢከተሉ:ንጉሳኑ እንከን የሌላቸው መሪዎች ሊሆኑ ይችሉ ነበር: ተፈጥሮም ይህን ትደግፍ ነበረ:ስለዚህም በማሃራጅ ዩዲስትር መንግስት አመራር ግዜ: ”ካማም ቫቫርሳ ፓርጃንያሃ ሳርቫ ካማ ዱግሃ ማሂ (ሽ ብ 1 10 4 ) “ማሂ” መሬት:ለህይወት የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ ከመሬት ማግኘት እንችላለን: ከሰማይ አይወድቅልንም: እንድ ዝናብ ከሰማይ ሊወድቅ ይችላል: ነገር ግን እንዴት ከመሬት በተለያዩ ሳይንሳዊ ሂደቶች: ይህ እንደሚከሰት አይረዱም: በተለያዩ በተመቻቹ ሁኔታዎች እና በአስትራል ግፊት:ዝናብ ወደ መሬት ይወርዳል: ከዚያም ብዙ ነገሮች ይመረታሉ:ይህም ውድ የሆኑ ድንጋዮች እና ፐርሎች ሳይቀሩ ነው: እነዚህ ሁሉ እንዴት እንደሚመረቱ አይረዱም: እንደዚሁም ሁሉ ንጉሱ የአማላክ በረከት ያለው ከሆነ: ተፈጥሮም ሊተባበረው ይችላል: ነገር ግን ንጉሱ እና መንግስት: በረከት የሌለው አመራር ከያዙ:ተፈጥሮም ሊተባበራቸው አይችልም: