AM/Prabhupada 0040 - አንድ አብዩ ጌታ እዚህ አለ፡፡



Lecture on BG 16.8 -- Tokyo, January 28, 1975

በዚህ አለም ላይ: በሚሊዮን እና በትሪልዮን የሚቆጠሩ: ነዋሪ ነፍሳቶች አሉ:: ፈጣሪ አምላካችንም በእያንዳንዱ ነፍስ ልብ ውስጥ: ተቀምጦ ይገኛል:: "ሳርቫስያ ቻሃም ህርዲ ሳኒቪስቶ ማታ ስምርቲር ጅያናም አፖሃናምቻ" (ብጊ 15 15) አምላክ እንዲህ እያደረገ እያስተዳደረን ይገኛል:: ታድያ: ፈጣሪ አምላካችን: እንደኛ የሚቆጣጠር ነው: ብለን እራሳችንን ከእርሱ ጋር ማወዳደር: ይህ የእኛ ድንቁርና ነው:: ፈጣሪ አምላክ ሁሉን የሚቆጣጠር ነው:: የአለም ሁሉ ተቆጣጣሪ አለ ማለት ነው:: አምላክም ሊቆጣጠር የሚችለው: ወሰን በሌለው እውቀቱ: ወሰን በሌለው አገልጋዮቹ: እና ወሰን በሌለው ሃይሉ ነው:: እነዚህ በአምላክ ሰብአዊ መንፈስ የማያምኑ: (በህንድ የሚገኙ) የአምላክ ሰብአዊ መንፈስ ምን ያህል ሃይል እንዳለው ማመን በጣም ያዳግታቸዋል:: ስለዚህም የሰብአዊ መንፈስ ከሃዲዎች ሁነው ይገኛሉ:: ይህን ሰብአዊነት ለማስተዋል በጣም ያዳግታቸዋል:: እነዚህ በአምላክ ሰብአዊነት የማያምኑ: ይህንን ማሰብ በጣም ያዳግታቸዋል:: እነሱም የሚያስቡት: "አንድ ሰው እንደ ሰው ከሆነ: እንደኔ ሰው መሆን አለበት" ብለው ያምናሉ:: እኔ ይህን ማድረግ ካልቻልኩኝ: እርሱም እንደዚህ ማድረግ አይችልም: ብለው ያምናሉ:: ስለዚህም: "ሙድሃ" ተብለው ይጠራሉ:: "አቫጃናንቲ ማም ሙድሃህ (ብጊ 9 11) ክርሽና አምላክን ከእነርሱ ጋር ያወዳድሩታል:: እርሱ ሰው እንደመሆኑም ሁሉ: አምላካችን ክርሽናም ፈጣሪ ሰው ነው:: ስለዚህ እውቀት የላቸውም:: የቬዳ ቅዱስ ስነፅሁፎች እንዲህ ብለው ያስረዱናል: "ፈጣሪ አምላክ ሰው ይሁንም እንጂ: ወሰን የሌለው የሰዎች ብዛትን ሲያስተዳድር ይገኛል" ይህን እነዚህ ሰዎች ሊረዱ አይችሉም:: "ኤኮ ባሁናም ቪዳድሃቲ ካማን" ይህ አንዱ ፈጣሪ ሰው: በብዙ ሚልዮን እና ትሪሊዮን የሚቆጠሩትን ሰዎች ሲያስተዳድር ይገኛል:: እኛ እያንዳንዳችን ሰዎች ነን:: እኔ ሰው ነኝ: አንተም ሰው ነህ:: ጉንዳን ሰብአዊ ነው: ድመት ሰብአዊ ናት: ውሻ ሰብአዊ ነው: ተባይ ሰብአዊ ነው: ዛፎች ሰብአዊ ናቸው: ሁሉም ነፍሳት ሰብአዊ ናቸው:: ሌላም ደግሞ ሰብአዊ ፍጡር አለ:: ይህም አምላካችን ፈጣሪ ክርሽና ነው:: ይህ አንድ ሰብአዊ ፍጡር: ወሰን በሌለው ሃይሉ: በሚልዮን እና በትሪልዮን የሚቆጠሩትን ሰዎች ሲያስተዳድር ይገኛል:: ይህም በቬዲክ ቅዱስ ስነፅሁፎች ተገልጿል:: "ኤኮ ባሁናም ቪዳድሃቲ ካማን ኒትዮ ኒትያናም ቼታናስ ቼታናናም (ካትሃ ኡፓኒሻድ 2 2 13) ይህ ነው መግለጫው:: ክርሽናም በብሃጋቫድ ጊታ እንዲህ አለ: "አሃም ሳርጋስያ ፕራብሃቮ ማታህ ሳርቫም ፕራቫርታቴ ኢቲ ማትቫ ብሃጃንቴ ማም (ብ ጊ 10 8) ስለዚህም የክርሽና አገልጋዮች ይህንን በትክክል ሲረዱ "አምላክ አንድ ብቻ መሆኑን ሲረዱ" "አምላክ የሁሉም መሪ እንደሆነ: የሁሉም ተቆጣጣሪ እንደሆነ: የሁሉም አስተዳዳሪ እንደሆነ" ለመረዳት ሲችሉ: በቀላሉ ሙሉ ልቦናቸውን ለመስጠት እና: ትሁት የአማላክ አገልጋር መሆን ይችላሉ::