AM/Prabhupada 0043 - ብሀገቨድ ጊታ መሰረታዊ መመሪያችን ነው፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0042
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0044 Go-next.png

Bhagavad-gītā is the Basic Principle - Prabhupāda 0043


Lecture on BG 7.1 -- Sydney, February 16, 1973

Prabhupāda:

“ዮጋም ዩንጃን ማድ አሽራያሃ አሳምሻያም ሳማግራም ማም ያትሃ ግናስያሲ ታክ ችርኑ” (ብጊ 7 1) ይህ ጥቅስ የመጣው ከብሃገቨድ ጊታ ነው: የሚያስተምረንም እንዴት የክርሽናን ንቃት ወይንም የፈጣሪ አማላክን ንቃት እንዴት እንደምናዳብር ነው: “ብሃገቫድ ጊታ” ብዙዎቻችሁ ስለዚህ ቅዱስ መጽሃፍ ስም ሰምታችኋል: በአለም ላይ በጣም ከፍ ባል ቁጥር ህዝብ የሚነበብ መጽሃፍ ነው: በአለም ላይ በእየአንዳንዱ አገር የተለያዩ:የታተሙ የብሃገቫድ ጊታ መጻህፍቶች ይገኛሉ: ይህም ብሃገቨድ ጊታ:የእኛ የክርሽና ንቃተ ማህበር ዋናው መመሪያ መጽሃፍ ነው: የክርሽና ንቃት ብለን የምናስፋፋው ሁሉ:የዚሁን የብሃገቨድ ጊታን መልእክት ብቻ ነው: እራሳችን የፈለሰፍነው ነገር የለም: ይህ የክርሽና ንቃት:ምድር ከተፈጠረች ግዜ ጀምሮ የነበረ ነው: ቢያንስ እንኳን ለአለፉት 5000 ዐመታት:ክርሽና መጥቶ ከነበረበት ግዜ ጀምሮ ማለት ይቻላል: ክርሽና እራሱ ይህንን የክርሽና ንቃት በምድር ላይ መርቶ አስተምሮናል: ትቶልን የሄደውም ትምህርት እና መንፈሳዊ ትእዛዛት:ይኅው በዚህ በብሃጋቨድ ጊታ ተመዝግቧል: ቢሆን ግን:ይብ ብሃገቨድ ጊታ: በአዋቂ ነኝ ባዮች እና በስዋሚ (መነኩሴ)ነኝ ባዮች:በተለያየ መንገድ አለአግባብ ተተርጉሞ ይገኛል: እንዚህም በፈጣሪ ሰብአዊነት የማያምኑ እና በፈጣሪ የማያምኑ ሰዎች ተርጉመውት ነው: ብሃገቨድ ጊታንም የተረጎሙት:የራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ነው: በ1966 አሜሪካ ውስጥ እያለሁ:አንድ አሜሪካዊ ሴትዮ ጠይቃኝ ነበር: ይህም የጠየቀችኝ:የየትኛውን የብሃገቨድ ጊታ መጽሃፍ ህትመት ለማንበብ እንድመራት ነበር: እውነቱን ለመናገር ግን: የትኛውንም ህትመት እንድታነብ ለመምራት አልቻልኩም: ይህም ይትርጉሙ አቀራረብ የአማራቸውን የግል አሰተያየት ሞልተውበት ስለነበረ ነው: ይህም ብሃጋቫድ ጊታ ልክ በክርሽና እንደተዘመረው ወይንም እንደተናገረው የሚተረጉምን መጽሃፍ እንዳሳትም ገፋፋኝ: ይህ አሁን የምታዩትም ህትመት:”ብሃገቨድ ጊታ እንደ ተዘመረው“ በማክሚላን ካምፓኒ በአለም ታላቁ መጽሃፍ አታሚ ታትሞ ይገኛል: እንደዚህም እያደረግን በጥሩ ሁኔታ እየተራመድን እንገኛለን: በመጀመሪያ ያተምነውም የትንሿ መጽሃፍ የ “ብሃገቫድ ጊታ እንደ ተዘመረው”መጽሃፍ የታተመው በ1968 (አአ)አመተ ምህረት ነው: በከፍተኛ ደረጃም ይሸጥ ነበር: የማክሚላን ካምፓኒም የንግድ ማናጀሮችም ለእኛ ሪፖርት አደርገው ነበር: የእኛ መጽሃፎች ብዙ እየተሸጡ የሌሎች መጽሃፎችም ሽያጭ እየቀነሰ መሆኑን ተናግረዋል: ከዚያም በ1972 የሙሉ በሙሉ የ“ብሃገቨድ ጊታ እንደ ተዘመረው” መጽሃፍን ተርጉመን አሳተምን: ማክሚላን ካምፓኒም 50000 መጽሃፍቶችን በቅድሚያ አሳትሞ አቀረበ: ይህም በ3 ወር ውስጥ ተሽጦ አልቆ እንደገና ለማሳተም መሯሯጥ ጀመርን: