AM/Prabhupada 0042 - ይህንን የድቁና ስርዓት ኮስተር አድርጋችሁ መቀበል ይኖርባችኋል፡፡



Initiation Lecture Excerpt -- Melbourne, April 23, 1976

በቼይታንያ ቻሪታምሪታ እንደተገለፀው:ቼታንያ ማሃፕራብሁ ሽሪላ ሩፓ ጎስዋሚን ሲያስተምር እንዲህ አለ: “ኤ ሩፔ ብራህማንዳ ብህራሚቴ ኮና ብሃጋቫን ጂቭ ጉሩ ክርሽና ፕራሳዴ ፓይ ብሃክቲ ላታ ቢጅ:(ቼቻ ማድህያ 19 151) በአለም ላይ ያሉ ነፍሳት ሁሉ:ከአንድ ህይወት ወደ ሌላ ህይወት በሞት ግዜ በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ: እንዲሁም ከአንዱ ፕላኔት ወ ደ ሌላው ፕላኔት ሲዘዋወሩ ይገኛሉ: አንዳን ግዜ የወደቀ እና የረከሰ ኑሮ ይኖራሉ:ሌላው ግዜ ደግሞ ከፍ ያለ የምቾት እና የከበረ ኑሮ ይኖራሉ: ይህ እየተካሄደ ነው:ይህም እንዲህ ይባላል:”ሳምሳር ቻክራ ቫርትማኒ“ ትላንትና ማታ ይህን ስናስረዳ ነበር:”ምርትዩ ሳምሳራ ቫርትማኒ“ ይህም ቃል እንዳለ ተጠቅሷል:”ምርትዩ ሳምሳራ ቫርትማኒ“ የአለም ኑሮ የከበደ ነው: መጨረሻም ላይ ሞት አለ: ሁሉም ሞትን በጣም ይፈራል:ምክንያቱም ከሞት በኃላ ምን እንደሚመጣ ማንም አያውቅም: እነዚህ ሞኞች የሆኑት:እንደ እንስሳ ይቆጠራሉ: ልክ እንስሳው ሲታረድ:ሌላው እንስሳ ደግሞ ”እኔ ደህና ነኝ“ ብሎ ያስባል: እንደዚሁም ማንም ትንሽ አእምሮ ያለው ሰው: መሞት እና ሌላ ገላ ለመያዝ አይወድም: ምን አይነትም ገላ:ከሞት በኋላ እንደምናገኝም አናውቅም: እና ይህንን መንፈሳዊ የድቁና በረከት: ከጉሩ እና ከክርሽና የምታገኙትን: እንዲሁ በቀላሉ ወይንም በጥርጣሬ አትውሰዱት: ኮስተር ብላችሁ መውሰድ አለባችሁ:ይህም ለእድገታችሁ:ትልቅ እድል የሚሰጣችሁ ነው: ”ቢጃ“ ማለት ዘር ማለት ነው: የአማላክ የፍቅር አገልግሎት ዘር: ማለት ነው: እንዲሁም ቃል የገባችህትን ሁሉ:ፈጽሙ: ይህም ማሃላ:ለመንፈሳዊ አስተማሪያችሁ:ከእሳት ሴረሞኒ ፊት:ወይንም ከቫኤሽናቫዎች ፊት ለፊት ሊሆን ይቻላል:ከዚህም መሃላ ስታችሁ በፍጹም እንዳትሄዱ: በዚህም መንገድ የመንፈሳዊ አቅዋማችሁ በጣም ያማረ ይሆኖል: ማመንዘር የሌለበት:ስጋ መብላት የሌለበት:ቁማር የሌለበት:የአልክሆል ስክረት የሌለበት: እንዚህን አራት መመሪያ እየተከተላችሁ:የጌታ ክርሽናን ቅዱስ ስም ዘምሩ: አርት የተከለከሉ መመሪያዎች እና አንድ መመሪያ:ይህ ህይወታችሁን በጣም የተሳካ ያደርገዋል: ይህም ቀላል ነው: የሚከብድ መመሪያ አይደለም: ነገር ግን ”ማያ“ ከባድ ናት:ወደ አለማዊ መንገድ ሁልግዜ ትገፋፋናለች: ስለዚህ ”ማያ“ ወደ አለማዊ መንገድ ስትገፋፋን: ሁል ግዜ ፀሎት ማድረግ ያስፈልገናል: ”ጌታዬ ሆይ:እባክህ አድነኝ:ሙሉ ልቦዬን ሰጥቼሃሉ:እባክህ ከክፉ አለማዊ ኑሮ ሰውረኝ“ ብለን መፀለይ አለብን: ክርሽናው ውዲያውኑ ከመውደቅ ይሰውረናል: ይህንንም እድል እንዳያመልጣችሁ: ይህ ነው የእኔ ምክር: የእኔ ጥሩ ምኞት እና ምርቃት ከእናንተ ጋር ነው: ስለዚህ የዚህን የብሃክቲን እድል እንጠቀምበት:”ብሃክቲ ላታ ቢጅ“ ”ማሊሃና ሴይ ቢጃ ካሬ አሮፓና“ ጥሩ ዘር ስናገኝ:መሬት ውስጥ መዝራት አለብን: ምሳሌውም እንዲህ ተሰጥቷል:የአንደኛ ደረጃ ጥሩ የጽጌረዳ ዘር ስታገኙ: ከዚያም መሬት ላይ ተክላችሁ: ትንሽ ውሃ ብታጠጡት: ማደግ ይጀምራል:ይህም ዘር ውሃ በማጠጣት ለማደግ ይችላል: ይህ መንፈሳዊ ውሃ ታድያ ምንድን ነው?”ሽራቫና ኪርታና ጃሌ ካርዬ ሴቻና“ (ቼቻ ማድህያ 19 152) ይህ የመንፈሳዊ ዘርን ውሃ ማጠጣት ማለት:”ብሃክቲ ላታ“ ማለት ”ሽራቫና ኪርታና“ ስለ አምላካችን መስማት እና መዘመር ማለት ነው: ስለዚህም ከሳንያሲ (መሎ ክሴ) እና ከቫይሽናቫዎች:ተደጋግሞ የምትሰሙት ነገር ይሆናል: ነገር ግን ይህንን እድል እንዳያመልጣችሁ ተጠቀሙበት:ያ ነው የእኔ መልእክት:በጣም አመሰግናለሁ: ድቮቲዎች:“ጃያ ፕራብሁፓዳ”