AM/Prabhupada 0050 - የሚቀጥለው ሕይወት ምን እንደሆነ አያውቁትም፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

They do not Know What is Next Life - Prabhupāda 0050


Lecture on BG 16.5 -- Calcutta, February 23, 1972

ተፈጥሮ ራሱ በሽሪ ክርሽና ትእዛዝ ስር ዕድል እየሰጠን ይገኛል፡፡ ይህም ዕድል ከዚህ ከተሳሰረ የመወለድ እና የመሞት ሰንሰለት እንድንላቀቅ ነው፡፡ “ጃንማ ምርትዩ ጃራ ቭያድሂ ዱክሀ ዶሻኑ ዳርሻናም” (ብጊ 13 9) አንድ አዋቂ ሰው የእነዚህ የአራቱን ክሰተቶች መከራ ለይቶ መረዳት ይገባዋል፡፡ እነዚህም መወለድ መሞት እርጅና እና በታመም ናቸው፡፡ የቬዲክም ስረአትም ሁሉ የሚያስተምረን ከእነዚህ ከአራቱ ወጥመዶች እንዴት አድረገን ለመላቀቅ እንደምንችል ነው፡፡ ቢሆንም ግን የተመጣጠነ ኑሮ እንድንኖር ዕድል ተሰጥቶናል፡፡ ይህም ”ይህንን አድርግ፡ ያንን አድርግ“ በመባል ነው፡፡ ይህንንም ስርአት በመከተል በመጨረሻው ደረጃ ከዚህ ወጥመድ ተላቀን ለመውጣት እንበቃለን፡፡ ሰለዚህም አብዩ የመላእክት ጌታ ብሀገቫን እንዲህ ብሏል፡ ”ዳይቪ ሳምፓድ ቪሞክሳያ (ብጊ 16 5) እዚህ እንደተጠቀሰውም ዳይቪ ሳምፓት የተባለውን ባህርይ ካዳበራችሁ “አሂምሳ ሳትቫ ሳምሹድሂህ አሂምሳ” እንደነዚህ ብዙ ነገሮችን ካደረጋችሁ “ቪሞክሳያ” የተባለውን ታገኛላችሁ፡፡ በአሁኑ ግዜ ያለው ዘመን “ቪሞክሻ” ምን እንደሆነ እውቀቱ የላቸውም፡፡ የእውቀት ዓይናቸው የተሰወረ ነው፡፡ “ቪሞ ክሳያ” የተባለ ደረጃ እንደ አለ የተረዱ አይደሉም፡፡ ከዚህ ሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት እንደአለ ምንም እውቀቱ የላቸውም፡፡ በዚህ እውቀት የተመሰረተም የትምህርት ድርጅቶች አይታዩም፡፡ ይህንንም በመላ ዓለም ተዘዋውሬ አይቸዋለሁ፡፡ ስለ ነፍሳችን ከሞት በኋላ ሕይወት የሚያስተምር አንድ የትምህርት ድርጅት እንኳን አይታይም፡፡ በዚህ ሂደት እንዴት አንድሰው የተሻለ ኑሮ ለማግኘት ይችላል? እምነት የሚባል ነገር ያላቸውም፡፡ ለእምነት የሚያመች እውቀትም የላቸውም። ይህን “አሱሪ ሳምፓት” ይባላል፡፡ ይህም በሚቀጥለው ተገልጿል፡፡ “ፕራቪቲም ቻ ኒቭርቲም ቻ ጃና ና ቪዱር አሱራሀ” ፕራቭርቲም - ፕራቭርቲም ማለት መሳብ ወይንም በጣም በቅረብ ማለት ነው፡፡ ታድያ ወደ ምን ዓይነት እንቅስቃሴ ወይንም ስራ ነው መሳብ የሚገባን? ከምን ዓይነት ስራስ ነው መራቅ የሚገባን? አሱራ ወይንም ሴይጣናዊ አንደበት ያላቸው ሁሉ ይህንን ሊረዱ አይችሉም፡፡ “ፕርቭርቲም ቻ ኒቭርቲም ቻ” “ፕራቭርቲም ቻ ኒቭርቲም ቻ ጃና ና ቪዱር አሱራ ና ሶቻም ናፒ ቻቻሮ ና ሳትያም ቴሹ ቪድያቴ” (ብጊ 16 7) እነዚህ አሱራዎች (ሰይጣናዊ) ናቸው፡፡ ሕይወታቸው ወደ የትኛው በጎ መንገድ መመራት እንደሚገባው እውቀቱ የላቸውም፡፡ ይህም “ፕራቭርቲ” ይባላል፡፡ ከምን ዓይንት ክፉ ኑሮ መቆጠብ እንዳለባቸውም (ንቭርቲ) እውቀቱ ያላቸውም፡፡ ፕርቭርቲስ ቱ ጂቫትማና - ይህም ሌላ ነው፡፡ ”ብሁናም ኒቭርቲስ ቱ መሀ ፕሀላም“ ጠቅላላ የቬዲክ ስነፅሁፍም ሁሉ የሚሰጠው መመሪያ ይኅው ነው፡፡ “ፕርቭርቲ እና ኒቭርቲ” በዚህም መመሪያ ቀስ በቀስ ልምዱ እየተገኘ ይመጣል፡፡ “ሎኬ ቭያቫያሚሳ ማድያ ሴቫ ኒትያ ሱጃንቶሀ“ እያንዳንዱ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በተፈጥሮ ለቭያቫያ ወይንም ለወሲብ ምኞት ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለማድያ ሴቫሀ ወይንም ለመጠጣት እና ለመስከር በተጨማሪም ስጋ ለመብላት ምኞት አለው፡፡ በተፈጥሮ እነዚህ አዝማምያዎች አሉ፡፡ አሱራዎች ይህንን አዝማሚያ ለማጥፋት ምኞቱም የላቸውም፡፡ እንዲያውም ምኞታቸው ከመጠን በላይ ለመጨመር ነው፡፡ ይህ አሱራ ሕይወት ነው፡፡ አንድ በሽታ ሊኖረኝ ይችላል፡፡ ከዚህም በሽታ ለመዳን ከፈለኩኝ ዶክተሩ መድሀኒት ሊያዝልኝ እና ትእዛዝ ሊሰጠኝ ይችላል፡፡ ”ይህንን እንዳትወስድ“ የስኳር በሽታ ያለው ሰው ስኳርን እንዳይወስድ ተከልክሏል፡፡ ”ሰኳር እንዳትወስድ ስታርችም እንዳትወስድ“ ኒቭርቲ - እንደዚሁም ሁሉ የቬዲክ ስነፅሁፎች ይህንን የመሰለ መመሪያ ሲሰጡን ይገኛሉ፡፡ ሻስትራ ወይንም እነዚህ የቬዲክ ቅዱስ መጻህፍቶች ምን በቀበል እንደ አለብን እና ምን መግደፍ እንዳለብን በግልፅ ተንትነው ይገልፁልናል፡፡ ልክ በእኛ መንፈሳዊ ሕብረተሰብ ውስጥ እንደምናየው የትኛው አስፈላጊ ኒቭርቲ እና የትኛውን ፕራቭርቲ መቀበል እንደአለብን በደንብ ተረድተን እንገኛለን፡፡ ይህም ፕርቭርቲ ሰለሚባለው ለተማሪዎቻችን እንዲህ ብለን ትምህርቱን ሰጥተናቸዋለን፡፡ “አግባብ የሌለው ግብረ ስጋ ግኑኝነት ከማድረግ እና ስጋን ከመብላት መቆጠብ እንዳለብን“ ”አሚሳ ሴቫ ኒትያ ሱጃንቶሀ“ የሻስትራም ቅዱስ መፃህፍትም ከእነዚህ እንድንርቅ ገልፀውልናል፡፡ ”ኒቭርቲስ ቱ መሀፕሀላም“ ከእነዚህም ከመቆጠብ ሕይወታችን የተሳካ ሊኖን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዝግጁ ላንሆን እንችላለን፡፡ እነዚህንም ፕራቭርቲዎች የመቀበል ፍላጎት ከሌለን እና ኒቭርቲዎችን ለመራቅ ፍላጎቱ ከሌለን ሰይጣናዊ አንደበት እንደያዝን በረዳት ይገባናል፡፡ ክርሽናም እንዲህ ይላል ”ፕራቭርቲም ቻ ኒቭርቲም ቻ ጃና ና ቪዱር አሱራሀ (ብጊ 16 7) አንዳንዶችም ሊረዱት አይችሉም፡፡ “ምንድን ነው የምትለው?" ብለው ይጠይቃሉ፡፡ እንዲያውም ትላልቅ መነኩሴዎች ሁሉ ”ይህ ምን ጥፋት አለው?" ብለው ይናገራሉ፡፡ የፈለከውን መብላት ትችላለህ። ምን ችግር አለው? የፈለከውን ማድረግ ትችላለህ፡፡ እነዚህ ወስላታ መነኩሴ ነኝ ባዮችም እንዲህ ይላሉ፡፡ “አንተ ብቻ ትንሽ ገንዘብ ስጠኝ እና እኔ ልዩ የሆነ የፀሎት ጥቅስ እሰጥሀለሁ፡፡” እንዲህ ዓይነት ማታለል እየተካሄደ ነው፡፡