AM/Prabhupada 0051 - የደነዘዘ ጭንቅላት ከዚህ ገላ ባሻገር ምን እንዳለ ለመረዳት አይችልም፡፡



Interview with Newsweek -- July 14, 1976, New York

ጋዜጠኛ፡ የክርሽና ንቃተ ማህበር በአንድ ወቅት ለመላ የዓለም ህዝብ የሚስፋፋበት ግዜ ይመጣል ብለው ያስባሉ?

ፕራብሁፓድ፡ ይህ የሚቻል አይደለም፡፡ ይህ ንቃት በመንፈሳዊ አእምሮ ለዳበሩ አዋቂዎች ሊቀሰም የሚችለ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ በመንፈስ የዳበሩ የአዋቂነት ማእረግ ላላቸው ሰዎች ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ ታድያ ከእነዚህ በአዋቂነት ደረጃ ከሚገኙት ውስጥ?

ፕራብሁፓድ፡ አንድ ሰው በመንፈሱ የዳበረ እና በአዋቂነት ማእረግ ላይ የሚገኝ ካልሆነ ይህንን የክርሽናን ንቃት ሊረዳው አይችልም፡፡ መላ የዓለም ህዝብም በአዋቂነት ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው ብለንም አንገምትም፡፡ “ክርሽና ዬ ብሀጃ ሴ ባዳ ቻቱራ” አንድ ሰው በአዋቂነት ማእረግ ላይ የሚገኝ ካልሆነ የክርሽናን ንቃት ለመረዳት ያዳግተዋል፡፡ ምክንያቱም ይህ የክርሽና ንቃት ከዓለማዊው ኑሮ ባሻገር የተለየ ርእስን ይዞ የሚገኝ በመሆኑ ነው፡፡ እንደሚታየው ብዙሀኑ የዓለም ሰዎች መላ ሕይወታቸውን የሚያጠፉት ኑሮዋቸውን ለገላቸው ጥቅም ብቻ በሚያውል ሕይወት የተመረኮዘ በማድረግ ነው፡፡ (ለነፍስ ሳይሆን) ይህንንም በመሰለ የደነዘዘ አእምሮ በመያዝ ከገላ ጥቅም ውጪ ምን ዓይነት ጥቅም እንዳለ ለመረዳት የሚያዳግታቸው ናቸው፡፡ ስለዚህ መላ የዓለም ህዝብ የክርሽናን ንቃት በትክክል ሊረዳው ይችላል ብሎ ማመን የሚያዳግት ነው፡፡ ይህ የሚቻል አይደለም፡፡

ጋዜጠኛ፡ ስለ ጄኔቲክ ሳይንስ (ዘር የመቀያየር ሳይንስ)በቅርብ ግዜ ብዙ ውይይት ሲካሄድ ነበረ፡፡ ይህም የጄኔቲክ ሳይንስን እንዴት ለማሻሻል እንደሚቻል ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ጄኔቲክ ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው?

ጋዜጠኛ፡ የጄኔቲክ ሳይንስን ማሻሻል ማለት ምንድነው? ባሊ

ማርዳን፡ ይህም ትላንትና ስለ ጄነቲክ ሳይንስ ስንወያይ እንደነበረው ነው፡፡ ይህንንም የጄኔቲክ ሳይንስ ለማሻሻል የገላችን እና የሀሳባችን መሰረታዊ ባህርዮች ምን እንደሆኑ ጥረት በማድረግ እና በመረዳት ቀስ በቀስ ነገሮችን ለመለዋወጥ ይፈልጋሉ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ሰለዚህ ርእስ መጽሀፍ አለን፡፡ ያ መጽሀፍ የታለ?

ራሜሽቫራ፡ ይህም በስዋሩብ ዳሞዳር መፅሀት ውስጥ ተጠቅሷል፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አዎን፡፡ አምጣው፡፡

ራሜሽቫራ፡ ታድያ ጥያቄህ ምንድነው?

ጋዜጠኛ፡ የኔ ጥያቄ እንዲህ ነው፡፡ ቀደም ብለው የቴክኖሎጂ እቃዎችን ስለመጠቀም ጠቅሰው ነበረ፡፡ በዚህም አኳያ በአንዳንድ ሕብረተሰብ ውስጥ የሚታዩ ነገሮች አሉ፡፡

ፕራብሁፓድ፡ መጽሀፉን ለማግኘት አልቻላችሁምን? የለም?

ጋዜጠኛ፡ ጥያቄዬን ልጠይቅ፡፡ የሰው ልጅ የቴክኖሎጂን ጥቅም በመመርኮዝ ሕብረተሰቡን የሚያለማ ከሆነስ? ይህንንም በመከተል አብዛኛው የሰው ልጅ ሕብረተሰብ አእምሮው የዳበረ ነው፡፡ ታድያ አዋቂ ሰው ስንል ምን ማለታችን ነው?

ፕራብሁፓድ፡ አዋቂ ሰው ሊባል የሚችለው አንድ ሰው ነፍስ ወይንም ሰውየው በዚህ ቁሳዊ ገላ ውስጥ የሚገኝ እንደሆነ እንጂ ገላው ራሱ ነፍስ ወይንም ሰውየው እንዳልሆነ በትክክል ሲረዳ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ ብንጠቅስ አንድ ሰው ሸሚዝ ለብሷል እንበል፡፡ ነገር ግን ሰውየው ሸሚዝ ነው ልንል አንችልም፡፡ ይህንንም ማንም ሰው በቀላሉ ለመረዳት አያዳግተውም፡፡ ሰውየውም በሸሚዙ ውስጥ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አንድ ሰው ቁሳዊው ገላ እንዳልሆነ እና በቁሳዊው ገላ ውስጥ የሚገኝ ነፍስ መሆኑን በትክክል ሲረዳ አዋቂ ነው፡፡ ይህንንም ለመረዳት የሚያዳግት መሆን የለበትም፡፡ ይህንንም ለመረዳት በሞት ግዜ ያለው ልዩነቱ ምንድን ነው? በሞት ግዜ የሕይወትን ሀይል ስትሰጥ የነበረችው ነፍስ ገላውን ለቃ በመሄዷ ነው፡፡ በዚህም ግዜ ቁሳዊው ገላ ሞተ እንላለን፡፡

ጋዜጠኛ፡ ቢሆንም ግን በመንፈሳዊ እውቀት ያልዳበሩ ብዙ አዋቂ ሰዎች በምድር ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ገላ እራሳቸው እንዳልሆኑ ሊሰማቸውም የሚችሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህም ገላ የሞተ እንደሆነ እና ከገላ ባሻገር ሌላ ነገር እንዳለ የሚሰማቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ታድያ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች በመንፈሳዊ ንቃት የዳበሩ ለመሆን ለምን አይበቁም፡፡

ፕራብሁፓድ፡ አንድ ሰው ቁሳዊ ገላው እንዳንልሆነ በቀላሉ ለመረዳት የማይችል ከሆነ ከእንስሳ ያልተሻለ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ የመንፈሳዊ ንቃት የመጀመርያው እና መሰረታዊው እውቀት ይህ ነው፡፡ አንድ ሰው የለበሰው ቁሳዊ ገላዬ ነኝ ብሎ የሚያስብ ከሆነ በእንስሳነት ደረጃ ላይ ተመድቦ የሚገኝ ሰው ነው፡፡

ራሜሽቫራ፡ ጥያቄዋ እንዲህ ነው... ለምሳሌ አንድ ሰው ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ የተረዳ ነው እንበል፡፡ ይህም ሰው በቁሳዊ ነገሮችም እውቀት አእምሮው የዳበረ ነው እንበል፡፡ ታድያ ይህ ሰው ለምን የክርሽና ንቃትን ለመረዳት አይችልም?

ፕራብሁፓድ፡ የቁሳዊው ዓለም እውቀት አእምሮው በመንፈስ የዳበረን አዋቂነትን ሊሰጠን አይችልም፡፡ የቁሳዊ ዓለም እውቀት የተሞረኮዘው “እኔ ይህ ቁሳዊ ገላ ነኝ” በሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህም “እኔ አሜሪካዊ ነኝ፡፡ እኔ ሕንድ ነኝ፡፡ እኔ ቀበሮ ነኝ፡፡ እኔ ውሻ ነኝ፡፡ እኔ ሰው ነኝ፡፡” በሚል አስተሳሰብ የተመረኮዘ ነው፡፡ ይህ የቁሳዊ ዓለም ንቃት ነው፡፡ የመንፈሳዊው ንቃት ግን ከዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ባሻገር ነው፡፡ ይህም ”እኔ ይህ ቁሳዊው ገላ አይደለሁም“ በሚል እውቀት ነው፡፡ ይህንንም ዓይነት ንቃት ያለው ሰው አዋቂ ነው ተብሎ ሊታወቅ ይችላል፡፡ አለበለዘ ግን አዋቂ ሰው ሊባል አይችልም፡፡

ጋዜጠኛ፡ ታድያ እንዲህ ማለታችን ...

ፕራብሁፓድ፡ እነዚህም ዓለማዊ ሰዎች “ሙድሀ” ወይንም እንደ “አህያ” ይመሰላሉ፡፡ እንደዚህም ሁሉ አንድ ሰው ራሱን ገላዬ ነኝ ብሎ ማሰብ አይገባውም፡፡

ጋዜጠኛ፡ ከዚህ በኋላስ ያለው ንቃት ምን ይሆናል?

ፕራብሁፓድ፡ ለምሳሌ ውሻን እንውሰድ፡፡ ውሻ እኔ ገላዬ ነኝ ብሎ ነው የሚያስበው፡፡ የሰውም ልጅ እንደዚሁ የመሰለ አስተሳሰብ ካለው ከውሻው ምንም የተሻለ አስተሳሰብ የለውም ማለት ነው፡፡

ጋዜጠኛ፡ ታድያ ከዚህስ ንቃት በኋላ ምን ዓይነት ንቃት እንዲኖር ያስፈልጋል? ባሊ

ማድዳን፡ ይህ ቁሳዊ ገላ እራሳችን እንዳልሆንን ከተረዳንስ በኋላ ምን ዓይነት ንቃት እንዲኖረን ያስፈልገናል?

ፕራብሁፓድ፡ ይህ የአዋቂዎች ጥያቄ ነው፡፡ ቁሳዊ ገላችን እንዳልሆንን ከተገነዘብንም በኋላ እንዲህ ብለን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ “በአሁኑ ወቅት በቁሳዊ ዓለም መንፈስ በተሞላበት ኑሮ ላይ እገኛለሁ፡፡” “ታድያ ከዚህ ባሻገር ማድረግ የሚገባኝ ምን ዓይነት ስራ ነው?" ይህ ዓይነቱ ጥያቄ የሰናተን ጎስዋሚ ዓይነቱ ጥያቄ ነው፡፡ እርሱም እንዲህ ብሎ ጠይቋል፡፡ ”ከዚህ ከዓለማዊው ስራዬ ነፃ አውጥተህኛል፡፡ ታድያ ከዚህ ባሻገር ስራዬ ምን መሆን ይገባዋል?" "የአሁኑ ሀላፊነቴ ምን መሆን እንደሚገባው መረዳት እፈልጋለሁ፡፡“ ይህም ጥያቄ በአእምሮዋችን ውስጥ መቀረፅ ሲጀምር አንድ ሰው ወደ መንፈሳዊው አባት መቅረብ ይገባዋል፡፡ ይህም ምን ማድረግ እንደሚገባው ለመረዳት እና ሀላፊነቱን ለማወቅ እንዲችል ነው፡፡ ”እኔ ይህ ቁሳዊ ገላ ካልሆንኩ መስራት የሚገባኝ ምን ዓይነት ስራ ነው?" በአሁኑ ሰዓት ከቀን እስከ ማታ ድረስ የገላችንን ጥቅም ስናሳድድ እንገኛለን፡፡ ይህም ስንመገብ፣ ስንተኛ፣ በወሲብ ስንሰማራ፣ ራሳችንን ከጠላት ስንከላከል ወዘተ፡፡ እነዚህ ሁሉ ከቁሳዊ ገላችን ጋር ብቻ የተያያዙ ናቸው፡፡ ታድያ እኔ ይህ ቁሳዊ ገላ አይደለሁም የሚለው ንቃታችን ሲዳብር ማድረግ የሚገባን ነገር ምንድን ነው? ይህ አዋቂነት ይባላል፡፡ ራሜሽቫራ፡ ቀደም ብሎ እንደተጠቀሰው “ይህ ገላ እራሳችን እንዳልሆንን ከተገነዘብን በኋላ ማድረግ የሚገባን ምንድን ነው?"

ፕራብሁፓድ፡ "ከዚህ ንቃት በኋላ ምን ማድረግ እንደሚገባን መጠየቅ ይገባናል፡፡” “ለዚህም መልሱን ለማግኘት አንድ ሰው መንፈሳዊ አባትን ወይንም ራሱን በትክክል የተገነዘበ ሰውን ለእውቀት መቅረብ ይገባዋል፡፡

ጋዜጠኛ፡ መንፈሳዊ አባት በመፅሀፍ ተመስሎ ማለት ነው? ባሊ

ማርዳን፡ ወይንም መንፈሳዊ አባት እራሱ፡፡ ፑስታ

ክርሽና፡ ሽሪላ ፕራብሁፓድ ቀደም ብለው እንደጠቀሱት በቁሳዊው ዓለም በተመረኮዘው አስተሳሰባችን ብዙ ዓይነት ሀላፊነት ይዘን እንገኛለን፡፡ በገቢ በስራ ላይ ተሰማርተናል፣ በወሲብ እንሰማራለን፣ ምግብ ስንበላ እንገኛለን፣ እንተኛለን፣ እራሳችንን ስንከላከል እንገኛለን ወዘተ፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ከቁሳዊ ገላችን ጋር በቀጥታ የተያያዙ ናቸው፡፡ ታድያ እኛ ይህ ቁሳዊ ገላ አይደለንም ብለን ስንገነዘብ ስራችን ምን መሆን ይገባዋል? ይህንንም የመሰለ ንቃት ላይ ስንደርስ የሚቀጥለውን ሀላፊነታችንን ለመረዳት ከመንፈሳዊ አባት መመሪያዎችን መውሰድ ይገባናል፡፡ ይህንንም ፈለግ በመከተል እርምጃ መውሰድ የሚገባን ትክክለኛው ሀላፊነታችንን ምን እንደሆነ በማወቅ ነው፡፡ ይህም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ፕራብሁፓድ፡ ለመብላት፣ ለመተኛት፣ ለወሲብ እና እራሳችንን ለመከላከል እንኳን ከመምህር እውቀት መውሰድ ያስፈልገናል። ለምሳሌ ጥሩ ምግብ ለመብላት ምን ዓይነት ምግብ መመገብ እንደሚገባን ከምግብ አዋቂዎች እውቀት መውሰድ ይገባናል፡፡ ለምሳሌ ምን ዓይነት ቫይታሚን መውሰድ እንደሚገባን፡፡ ይህ ራሱ ትምህርት ያስፈልገዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ መተኛት ራሱ ትምህርት ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ በቁሳዊ ገላ የተመሰረተው ሕይወት ራሱ ከሌላ ሰው እውቀት መውሰድን ይፈልጋል፡፡ ታድያ ከዚህ ከቁሳዊ ገላ ከተመሰረተ ሕይወት በላይ የአንድ ሰው እውቀት ሲዳብር ወይንም “እኔ ይህ ገላ አይደለሁም፡፡ እኔ በገላ ውስጥ የምትገኘው ነፍስ ነኝ፡፡” የሚለውን እውቀት ሲያገኝ በዚህን ግዜ የመንፈሳዊ እውቀትን ከመምህር ለመውሰድ መዘጋጀት አለበት፡፡