AM/Prabhupada 0054 - ሁሉም ለክርሽና ችግር በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
"ማያቫዲዎች" ለማረጋገጥ የሚፈልጉት ቢኖር፤ ከሁሉም በላይ ፍፁም የሆነው እውነት "ኒራካራ" ወይንም ሰብአዊ ያልሆነ የአምላክ ሀይል ነው በማለት ነው፡፡ ክርሽና እንዲህ በማለት አእምሮ ሰጥቶናል፡፡ "ይህንን ንድፈ ሀሳብ አቅርብ" "ይህንን ሙግት ወይንም ያንን ሙግት አቅርብ" እንዲህም ዓይነት ሀሳብ በመስጠት ሽሪ ክርሽና በአእምሮዋችን እንድንመራ ያደርገናል፡፡ እንዴት አብዩ ጌታ ስራውን እንደሚሰራም የአንድ የቤንጋሊ አባባል አለ፡፡ ይህም አንዱ ሰው በቤቱ ውስጥ በመሆን እንዲህ ዓይነት ፀሎት በማድረግ ላይ ይገኝ ይሆናል፡፡ "ጌታዬ ሆይ በዛሬ ሌሊት ውስጥ መኖርያ ቤቴ በሌቦች ሳይዘረፍ አይቀርም፡፡ ስለዚህ እባክህ ከዚህ ዘረፋ አድነኝ፡፡" እንደዚህም በማለት አንድ ሰው ፀሎቱን ያቀርብ ይሆናል፡፡ በሌላ ቦታ ደግሞ ሌባው እንዲህ በማለት ይፀልይ ይሆናል፡፡ "ጌታዬ ሆይ በዚህ ሌሊት እዚያ ቤት ውስጥ ሰብሬ በመግባት ለመዝረፍ እፈልጋለሁ፡፡" "ስለዚህ እባክህ የምዘርፈውን ነገር እንዳገኝ እርዳኝ፡፡" ታድያ በዚህ ግዜ ክርሽና ማድረግ ያለበት ምንድን ነው? (ሳቅ) ክርሽና በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ ይገኛል፡፡ የሁላችንንም ፀሎት መስማት እና ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ይህም የሌቦቹንም ፀሎት፣ የቤቱን ጌታ ፀሎት እና ሌሎች የተለያዩ ፀሎቶችን መስማት ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ቢሆንም ግን ክርሽና ሁሉን አስተካክሎ ለማቅረብ የማያዳግተው ነው፡፡ ይህም የሽሪ ክርሽና ዓብዩ አእምሮ ስራ ነው፡፡ ሽሪ ክርሽና ለሁሉም ነፃነትን ሰጥቷል፡፡ ለሁሉም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ አቅርቧል፡፡ ይህም ሁሉ ሆኖ ሁልግዜ ለጥቅማችን ስናስቸግረው እንገኛለን፡፡ ስለዚህም ክርሽና ለትሁት አገልጋዮቹ እንዲህ ብሎ መክሯቸዋል፡፡ “ምንም ዓይነት የግልህን ፕላን አታድርግ፡፡“ አንተ ተንኮለኛ ለእኔ ብዙ ችግር አታምጣብኝ፡፡ (ሳቅ)ሙሉ ልቦናህን ግን ለእኔ ማቅረብ ይኖርብሀል፡፡ እኔ ባቀርለብኩልህ ፕላን ስር የምትተዳደር ከሆነም ሁሌ ደስተኛ ልትሆን ትችላለህ፡፡ አንተ የራስህን ፕላን ሁሌ እየነደፍክ ነው፡፡ በዚህም ደስተኛ ሆነህ አትታይም፡፡ እኔም በዚህ ደስተኛ አይደለሁም፡፡ (ሳቅ) በቀን በቀን ብዙ የተለያዩ ፕላኖች ወደ እኔ እየመጡ ነው፡፡ ለእነዚህም ሁሉ መልስ መስጠት ይጠበቅብኛል፡፡ ይህም ሁሉ እየሆነ ሽሪ ክርሽና ምህረት የተሞላበት ነው፡፡ ”ዬ ያትሀ ማም ፕራፓድያንቴ ታምስ ..." (ብጊ፡ 4.11)
ከሽሪ ክርሽና ትሁት አገልጋዮች በቀር ሁሉም ሰው ለክርሽና ብዙ ችግር እያቀረበ ነው፡፡ ችግር፣ ችግር፣ ችግር.... ስለዚህም እነዚህ አስቸጋሪዎች “ዱስክርቲና” ተብለው ይታወቃሉ፡፡ “ዱስክርቲና” ማለትም ወንጀለኛ ወይንም ሕግ ሰባሪ ማለት ነው፡፡ ምንም ዓይነት የግል ፕላን አታድርጉ፡፡ ሁሌ የክርሽናን ፕላን ብቻ ተቀበሉ፡፡ የግል ፕላናችሁ ግን ለክርሽና አላስፈላጊ ችግር ያቀርባል፡፡ ስለዚህ ትሁት የሽሪ ክርሽና አገልጋይ ለግሉ ጥቅም ብሎ ለምንም ዓይነት ቁሳዊ ነገር ፀሎት አያደርግም፡፡ ይህም የንፁህ አገልጋይ ባህርይ ነው፡፡ ለዚህም ለቀን እንጀራው እና ለግል ጥቅሙ በፀሎት ክርሽናን ለችግር አያጋልጠውም፡፡ የዕለት እንጀራውንም ባያገኝ ፆሙን ይውላል እንጂ ክርሽናን በፀሎት ለግል ጥቅሙ አይጠይቀውም፡፡ “ክርሽና እርቦኛልና እባክህ የምመገበውን አቅርብልኝ፡፡” ክርሽና ሰለ ትሁት አገልጋዮቹ ሁኔታ በደንብ የሚረዳ ነው፡፡ ስለዚህ የትሁት አገልጋዮቹ መመሪያ የግል ፕላናቸውን ለክርሽና ማቅረብ አይሆንም፡፡ ሽሪ ክርሽና ፕላኑን ያቅርብ፡፡ የእኛ ፋንታ ደግሞ የክርሽናን ፕላን በመከተል መኖር ብቻ ነው፡፡
ታድያ ይህ የእኛ ፕላን ምን መሆን አለበት? ስለዚህም ፕላን ክርሽና እንዲህ ብሎ ደንግጎልናል፡፡ “ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም” (ብጊ፡ 18.66)፡፡ “ማን ማና ብሀቫ ማድ ብሀክቶ ማድ ያጂ” ስለዚህ የእኛም ፕላን እንደዚሁ መሆን አለበት፡፡ ውይይታችንም ሁሉ ትኩረት የሚያደረገው ለክርሽና ነው፡፡ “የክርሽና ንቃታችሁን አዳብሩ” በማለት ነው፡፡ እንዴት የክርሽና ንቃታችንንም በማዳበር ላይ እንዳለን በምሳሌነትም ማስተማር ይገባናል፡፡ እንዴት ለክርሽና እንደምንሰግድለት፤ እንዴት ወደየመንገዱ ክርሽናን ለማገልገል እንደምንወጣ፤ እንዴት የክርሽናን ቅዱስ ስም ወይንም መንፈሳዊ ስሙን ለመዘመር በየመንገዱ እንደምንወጣ፤ እንዴት የክርሽናን ቅዱስ ምግብ ወይንም “ፕራሳድ” በነፃ እንደምናድል በተግባር ማሳየት ይኖርብናል፡፡ በተቻለ መጠን ሀላፊነታችን ሁሉ እንዴት የክርሽናን ንቃት ለሁሉም ሰው እንደምናስተምር መሆን ይገባዋል፡፡ ይኅው ነው፡፡ ይህንንም ሁሉ በተግባር ለማዋል እቅድ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ይህም እቅድ የክርሽና እቅድ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም እቅድ በክርሽና የተደገፈ መሆን አለበት፡፡ ለግል ጥቅም የሚሆን እቅዳችሁን ማውጠንጠን አትጀምሩ፡፡ ስለዚህ በትክክል ለመመራት እንድትችሉም ትሁት የክርሽና አገልጋይ ወይንም ተወካይ የሆነ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡ ይህም የመንፈሳዊው አባታችሁ ነው፡፡ ይህንንም ክቡር ዓላማ ለመፈፀም አብይ እቅድ አለ፡፡ ስለዚህ የመሃጃኖችን ወይንም የታላላቅ መንፈሳውያንን ፈለግ መከተል ይገባናል፡፡ እዚህም እንደተገለፀው “ድቫዳሻይቴ ቭጃኒሞ ድሀርማም ብሀገቨታም ብሀታህ” እንደገለፀውም “እኛ የተወልከነው ”መሃጃኖች“ ወይንም የሽሪ ክርሽና ተወካዮች፤ ብሀገቨት ድሀርማ ወይንም የክርሽና ድሀርማ ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡” ድቫዳሻ፡ ድቫዳሻ ማለት አስራ ሁለት ስሞች ማለት ነው፡፡ እነዚህም አስራ ሁለት መሀጃኖች ወይንም ታላላቅ መንፈሳዊ መምህራን በስቫያምብሁር ናራዳህ ሻምቡህ ውስጥ ተገልፀዋል፡፡ (ሽብ፡ 6.3.20) ቀደም ብዬም ገልጬዋለሁ፡፡ ያመራጅም እንዲህ ብሏል “እነዚህም አስራ ሁለት የክርሽና ተወካዮች ብቻ፤ የብሀገቨድ ድሃርማ ምን እንደሆነ ጥርት ባለ መንገድ የሚያውቁ ናቸው፡፡” “ድቫዳሽያቴ ቪጃኒማህ” ቪጃኒማህ ማለት “እናውቃለን” ማለት ነው፡፡ ”ድሃርማም ብሀገቫታም ብሀታህ ጉህያም ቪሹድሀም ዱርቦድሃም ያም ግያትቫምርታም አሽኑቴ“ “እናውቃለን” ስለዚህ በምክር የቀረበልንም ይኅው ነው፡፡ “ማሃጃኖ ዬና ጋታህ ሳ ፓንትሃህ” (ቼቻ፡ ማድህያ 17.186) ሽሪ ክርሽናንም በትክክል ለመረዳት እና የመንፈሳዊ ሕይወታችንን ስኬታማ ለማድረግ ከተፈለገ እነዚህ መሀጃኖች የሰጡትን መመሪያ ሁሉ በጥሞና በመከታተል ነው፡፡
በዚህም መንገድ እኛም የምንከተለው ይህንኑ የብራህማ ሳምፕረዳያን ወይንም የብራህማን ይድቁና ስርዓት ነው፡፡ እርሱም የመጀመሪያው “ስቫያምብሁ” ነው፡፡ የድቁና ስርዓቱም ከብራህማ ጀምሮ፣ ወደ ናራዳ፣ ከናራዳ ወደ ቭያሳዴቫ ሲቀጥል ይገኛል፡፡ በዚህም ቀጥሎ በማድሀቫ አቻርያ እና በሺሪ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ በዚህም መንገድ የታላላቅ መንፈሳውያኖቹን ፈለግ ስለምንከተል የሽሪ ብሀክቲሲድሀንታን ሳራስቫቲ ጐስዋሚ ፕራብሁፓድ የትውልድ ቀን በዛሬው ቀን ስናከብር እንገኛለን፡፡ ይህንንም ታላቅ በዓል በተከበረ ሁኔታ ማክበር ይጠበቅብናል፡፡ በብሀክቲሲድሀንታ ሳራስቫቲም የመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ እንድንሰማራ በዚህ ቀን ላይ ፀሎት ማድረግ ይገባናል፡፡ በትሁት አገልጋይህም በመመራት ላይ ስለምንገኝ፤ መንፈሳዊ ሀይሉን ስጠን፣ በትክክል ለማገልገልም አእምሮውንም ስጠን፡፡ እንዲህ በማለትም በዚህ መንፈሳዊ ቀን ግዜ መፀለይ ይገባናል፡፡ በዚህ ምሽት የነፃ “ፕራሳዳም” (መንፈሳዊ ምግብ) ማደል ይኖርብናል፡፡