AM/Prabhupada 0053 - በመጀመሪያ ደረጃ መስማት አለብን፡፡



Lecture on SB 2.1.5 -- Delhi, November 8, 1973

እኛም "ፕራክርቲ" ተብለን እንታወቃለን፡፡ እኛ ራሳችን የዓብዩ ጌታ ሀይል ነን፡፡ ቁሳዊ ነገሮችን ለመጠቀም ጥረት የምናደረገው ቁሳዊ ነገሮች ዋጋ ወይንም ጥቅም ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡ ለጥቅማችን የማይውሉ ከሆነ ግን ምንም ዋጋ አይኖራቸውም፡፡ ስለዚህ የእኛ ጥረት ምን መሆን እንደሚገባው እዚህ ተገልጿል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በቁሳዊ ዓለም ውስጥ ተጠምደን እንገኛለን፡፡ ስራችን በቁሳዊው ዓለም ለመኖር አይደለም፡፡ መሆን ያለበት ስራችን ከዚህ ዓለም እንዴት ለመውጣት እንደምንችል ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ይህ ነው ትክክለኛው ስራችን፡፡ ይህንንም ስራ ከፈለጋችሁ መድሀኒቱ እዚህ ይገኛል፡፡ ይህስ ምንድነው? "ሽሮታቭያህ ኪርቲታቭያሽ ቻ“ በማዳመጥ ካልተሰማራችሁ እንዴት አድርጋችሁ ደረጃችሁን ለመረዳት ትችላላችሁ? ዓብዩ ጌታን ወይንም ሽሪ ክርሽናን ስትረዱ ወይንም የዓብዩ ጌታ ወገን እና ቁራሽ መሆናችሁን ስትረዱ በዚህ ወቅት ላይ የራሳችሁን ትክክለኛ ደረጃ ምን እንደሆነ ለመረዳት ትችላላችሁ፡፡ ”እኛ የዓብዩ ጌታ ወገን እና የቁራሽ አካል ነን፡፡“ ክርሽና ዓብዩ ጌታ ነው፡፡ ”ሳድ አይሽቫራያ ፑርናም“ በሀብቱም ፍፁም ሙሉ የሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ አእምሮው የተቀወሰ ልጅ በመንገድ ላይ ይንከራተት ይሆናል፡፡ ቢሆንም ግን ረጋ ባለ መንፈስ ሲያስተውል እንዲህ ብሎ ራሱን ይጠይቃል፡፡ ”አባቴ ሀብት ያለው እና ብዙ ሀይል ያለው ነው፡፡“ ”ታድያ እኔ ለምንድነው በየመንገዱ እንደ እብድ የምንከራተተው?“ ”ምግብ የለኝም፣ መጠለያ የለኝም፣ ከደጅ ደጁም እየተንከረታተትኩ ስለምንም እገኛለሁ፡፡“ እንዲህም በማሰብ ራሱን ማወቅ ይጀምራል፡፡ ይህም "ብራህማ ብሁታ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም “እኔ ይህ ቁሳዊ ገላ አይደለሁም፡፡ እኔ የዓብዩ ጌታ ቁራሽ አካል የሆንኩኝ ነፍስ ነኝ፡፡” ይህ ነው ትክክለኛው ንቃት፡፡ ለመቀስቀስ የምንሻውም ይህንኑ ዓይነት ንቃት ነው፡፡ ታላቁ ለሰው ልጅ ልናደረገው የምንችለው በጎ አድራጎትም ይኅው ነው፡፡ ይህም የጠፋውን ንቃታችንን ለመመለስ ነው፡፡ ይህ ንቃት የጎደለውም ሰው በሞኝነቱ “እኔ ይህ ቁሳዊ አካል ነኝ” በማለት ስለሚያስብ ነው፡፡ “በዚህ ዓለም ውስጥም ሁሉን ነገር ለማመቻቸት መጣር አለብኝ” ብሎ ያስባል፡፡ ትክክለኛው እውቀት “ብራህማ ብሁታ አሀም ብራህማስሚ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ አሀም ብራህማስሚ ማለት “እኔ የዓብዩ ጌታ ወይንም የዓብዩ ብራህማን ወገን እና ቁራሽ አካል ነኝ፡፡” ማለት ነው፡፡ ”ወገን እና ቁራሽ አካል“ ይህም ልክ እንደ ወርቅ ቁራሽ ንጥረ ነገር ማለት ነው፡፡ የወርቅ ቁራሽ ንጥረ ነገር እራሱ ምንም እንኳን ትንሽ ቢሆንም ቁራሹ አካል ራሱ ወርቅ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የውቅያኖስ ጠብታ ውሀ እንደውቅያኖሱ የጨውነት ባህርይ አለው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም የአብዩ ጌታ ወገን እና ቁራሽ አካል እንደመሆናችን በዓይነታችን አንድ ነን፡፡ በዓይነት አንድ ነን፡፡ ፍቅር ሁሌ የምንሻው ለምንድን ነው፡፡ ምክንያቱም በክርሽና እና በእኛ መሀከል ፍቅር ስላለ ነው፡፡ እዚህ ቤተመቅደስ ውስጥም ለራድሀ ክርሽና ስንሰግድ እንገኛለን፡፡ ይህም በመጀመሪያ ደረጃ በመሀከላችን ፍቅር ስላለ ነው፡፡ የዓብዩ ጌታ ወገን እና ቁራሽ አካል እንደመሆናችንም ሁሌ ፍቅርን ስንሻ እንገኛለን፡፡ አንድ ሰው ሌላ ሴትን ለመውደድ ይሻል፡፡ አንድ ሴትም ሌላ ወንድ ለመውደድ ስትሻ ትገኛለች፡፡ ይህም ሰው ሰራሽ ባህርይ አይደለም፡፡ ነገር ግን በመንፈሳዊ ዓለም የሚገኘው ፍቅር በዚህ ቁሳዊ ዓለም ባህርይ ተሸፍኖ እና የተገላቢጦሽ ሆኖ ነው፡፡ ከዚህም ከቁሳዊ ዓለም ሽፋን ነፃ ስንሆን ባህርያችን ”አናንዳማዮ ብህያሳት“ (ቬዳንታ ሱትራ፡ 1፡1፡12) ደስተኛ እንሆናለን፡፡ ይህም ልክ ክርሽና ሁሌ እንደሚደንሰው ነው፡፡ ክርሽና ሌላ ነገር ሲያደርግ አይታይም፡፡ የክርሽናን ስእል እንዳያችሁት ካልያ ከተባለው የእባብ ዘር ጋር ሲጣላ ይታያል፡፡ በጭንቅላቱ ላይ ቆሞም ይደንስ ነበረ፡፡ ይህንንም የእባብ ዘር ሲፈራው አይታይም፡፡ ነገር ግን ሲደነስ ይታይ ነበረ፡፡ ከጎፒዎቹ ጋር በራስ ሊላ ዳንስ ውስጥ ሲደንስ እንደነበረም ከዚሁም የእባብ ዘር ካሊያ ጋር ሲደንስ ይታይ ነበረ፡፡ ምክንይቱም እርሱ ሁል ግዜ ”አናንዳማዮ ብህያሳት“ ነው፡፡ ”አንዳንዳማያ“ ማለት ሁልግዜ ጆሊ እና ደስተኛ ማለት ነው፡፡ ክርሽናን ማየት ትችላላችሁ፡፡ ክርሽና ....ለምሳሌ በኩሩክሼትራ የጦር ሜዳ ላይ ጦርነቱ ሲካሄድ ነበረ፡፡ ክርሽና ጆሊ እና ደስተኛ ነበረ፡፡ አርጁና ግን በትካዜ ላይ ነበረ፡፡ ይህም አርጁና ነዋሪ ነፍስ በመሆኑ ነው፡፡ ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ግን ምንም ትካዜ ላይ አልነበረም፡፡ ክርሽና ጆሊ እና ደስተኛ ነው፡፡ የዓብዩ ጌታ ባህርይ እንዲህ ነው፡፡ “አናንዳማዮ ብህያሳት” ይህ ነው ሱትራው፡፡ (ድምደማው) በብራህማ ሰሚታ ውስጥ ዓብዩ ጌታ እንዲህ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ “አናንዳማያ” ሁልግዜ ጆሊ እና ሁልግዜ ደስተኛ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኛም ወደ መንፈሳዊው ዓለም ስንሄድ እንደ እርሱ ደስተኛ እንሆናለን፡፡ ችግራችንም እንዴት አድረገን ወደዛ መሄድ እንደምንችል ነው፡፡ የመጀመሪያው ሀላፊነታችን ማዳመጥ ነው፡፡ “ሽሮታቭያ” ዓብዩ ጌታ ማን እንደሆነ ለማወቅ አዳምጡ፡፡ የሚኖርበትም ቤተ መንግስት ምን እንደሆነ ለማወቅ አዳምጡ፡፡ ምን እንደሚያደርግ እና እንዴት ደስተኛ እንደሆነ ሁሌ ማዳመጥ አለብን፡፡ “ሽራቫናም” በማዳመጥም እምነታችን እያጠነከረ ሲመጣ “ዓብዩ ጌታ የሚያስደስት ነው፡፡” የሚል ስሜት ሊሰማን ይችላል፡፡ ከዚህም በኋላ ስለዚህ ስሜታችን እና ስለ ዓብዩ ጌታ ለመለው ዓለም ለማወጅ ታላቅ ጥረት ለማድረግ እንወስናለን፡፡ ይህም “ኪርታናም” ይባላል፡፡