AM/Prabhupada 0057 - ልቦናችንን ማፅዳት፡፡



Lecture on SB 6.1.34-39 -- Surat, December 19, 1970

ሬቫቲናንዳና:ሁልግዜ ማበረታታት ያለብን ሃሬ ክርሽና እንዲዘመር ነው:አይደለምን? ፕራብሁፓዳ:አዎን:የዘመኑ የሃይማኖት መንገድ ይኅው ነው: ሃሬ ክርሽናንም በመዘመር:የአንድ ሰው: የመረዳት ኩሬው በጣም የፀዳ ይሆንለታል: መንፈሳዊ እውቀትም ማግኘት ይችላል: ልባችን ንጹህ ሳይሆን ግን:መንፈሳዊ እውቀት:ለማግኘትም ሆነ ለመረዳት በጣም ያዳግተናል: እነዚህ ሁሉ የማስተካከያ መናኅሪያዎች:ብራህማቻሪያ(ተማሪ):ግርጋሃስታ(ትዳር):ቫናፕራስታ (ጡረታ): እነዚህ ሁሉ ልብን ማጠቢያ: ለማጠብ እድል የሚሰጡ መናኅሪያዎች ናቸው: ብሃክቲም ልብን ለመንፈሳዊነት ጽዳት ማድረጊያ መንገድ ነው:”ቪድሂ ብሃክቲ“ የዴይቲ ስግደትም በማከናወን አንድ ሰው ልቦናውን ማጽዳት ይችላል: ”ታት ፓራትቬ ሳርቮ ፓድሂ“ አንድ ሰው የክርሽና ዘለአለማዊ አገልጋይ መሆኑን እይተረዳ በሄደ ቁጥር:በመንፈሱም ንጹህ እየሆነ ይመጣል: ንጹህ ይሆናል:“ሳርቮፓዲ” ማለትም:ያልታወከ “ሳርቮ ፓድሂ” ይህን “ኡፓዲ” ውን:ወይንም አለማዊ ሹመቱን ያስወግዳል: "እኔ አሜሪካዊ ነኝ“ ”እኔ ህንድ ነኝ“ ”እኔ ይህ ነኝ“ ”እኔ ያ ነኝ“ እንደዚህም ሁሉ:ከዚህ ከአለማዊ የገላ አስተሳሰብ ሁሉ ነፃ ስትሆኑ:ይህ ”ኒርማላም“ ይባላል: ”ኒርማላ“ ወይንም ያልተበከለ መንፈስ ማለት ነው: ነገር ግን ይህ አለማዊ አስተሳሰብ እስከ አለ ድረስ ግን:ይህም:”እኔ ይህ ነኝ“ ”እኔ ያ ነኝ“ እስከ አለ ድረስ: ”ሳ ብሃክታህ ፕራክርታህ ስምርታሃ“ በጎን: ”በደንብ ተቀመጥ:እንደዛ ሳይሆን“ ”ሳ ብሃክታህ ፕራክርታህ ስምርታህ:አርቻያም ኤቫ ሃራዬ“ የደይቲ ስግደት ስነስርአት ላይ እያለን እንኳን: ”አቻርያም ሃራየ ያት ፑጃም ሽራድሃዬሃቴ“ በጥሩ ፍቅር ይሰግድ ይሆናል:ነገር ግን ”ናታድ ብሃክቴሹ ቻንዬሹ“ ለሌሎች ትህትና እና አስተዛዘን ላይኖረው ይችል ይሆናል: ወይንም ደግሞ የጥሩ አምላክ አገልጋይ ባህርይ ምን እንደሆነ ላይረዳ ይችል ይሆናል: እንዲህ ከሆነም ”ሳ ብሃክታህ ፕራክርታህ ስምርታሃ“ እርሱም አለማዊ አገለጋይ ይባላል: ስለዚህ የእኛን ደረጃ ከአለማዊ አገልግሎት ደረጃ ከፍ ማድረግ አለብን: ይህም ከፍ ማለት ያለበት ደረጃ:አንድ ሰው የድቮቲ ወይም የአምላክ አገልጋይ ማንነትን በትክክል እስከሚረዳበት ድረስ ነው: ድቮቲስ ያልሆኑት እነማን ናቸው?አምላክ ማን ነው? ከሃዲዎችስ እነማን ናቸው? እነዚህ ልዩነቶች ሁሉ አሉ: ነገር ግን የ“ፓራማሃምሳ” ደረጃ ሲደረስ ግን:እነዚህ ልዩነቶች አይገኙም: እርሱም ሁሉም ሰዎች:በጌታ ማገልገል ላይ እንዳሉ አድርጎ ያያቸዋል: በማንም ላይ ቅናት የለውም:ማንንም ለያይቶ አያይም: ይህ ግን የተለየ ደረጃ ነው:የ ህንንም ለማስመሰል መሞከር የለብንም: ነገር ግን የ“ፓራማሃምሳ” ደረጃ ትልቁ እና አባይ መንፈሳዊ ብቁነት ደረጃ ነው: እንደ ሰባኪ ወይንም አስተማሪ ግን:ልክ ይህን ልጅ እንደአልኩት “በስነስርአት ተቀመጥ” “ፓራማሃምሳ” ግን እንደዚህ አያይም:እርሱ ምንአልባት ይህ ምንም አይደለም ብሎ ሊያልፈው ይችላል: ማየት ግን አዳግቶት አይደለም:እኛ ግን ይህንን ለማስመሰል አይገባንም: ምክንያቱም እኛ ሰባኪዎች እና አስተማሪዎች ነን:ፓራማሃምሳን ማስመሰል አይገባንም: ትክክለኛ መነሻውን እና ትክክለኛ መግለጫውን መናገር አለብን: ሬቨቲናንዳን:ፕራብሁፓዳ አንተ ከፓራማሃምሳ ደረጃ መሆን አለብህ: ፕራብሁፓዳ:እኔ ከእናንተ በታች ነኝ:ከእናንተ በታች: ሬቨቲናንዳን:ይህ ነው ቁንጅናህ:አንተ ፓራማሃምሳ ደረጃ ነህ:ነገር ግን እኛን እየሰበክህም ትገኛለህ: ፕራብሁፓዳ:አይደለም እኔ ከእናንተ በታች ነኝ:ከፍጥረታትም ሁሉ በታች ነኝ: የመነፈሳዊ አባቴን ትእዛዝ ግን ለመፈፀም ጥረት በማድረግ ላይ እገኛለሁ:ይህ ብቻ ነው: ይህ ነው የሁሉም ሰው ሁሉ ስራ መሆን የሚገባው: ሞክሩ:የከፍተኛው መንፈሳዊ ትእዛዝን ለማስፈፀም ሞክሩ: ይህም ለመበልፀግ አስተማማኙ መነገድ ነው: አንድ ሰው በዝቅተኛ ደረጃ ይገኝ ይሆናል: ነገር ግን:የታዘዘውን ስራ ለማስፈጸም ጥረት የሚያደርግ ከሆነ ግን:እንከን የለሽ ይሆናል: በዝቅተኛ ደረጃ ይገኝ ይሆናል:ነገር ግን:ሃላፊነት የተሰጠውን የሚወጣ ከሆነ ግን:እንከን የጎደለው አይሆንም: ይህ ነው መታወቅ ያለበት: