AM/Prabhupada 0058 - መንፈሳዊ ገላ ማለት ዘለዓለማዊ ሕይወት ማለት ነው፡፡
Lecture on BG 2.14 -- Mexico, February 14, 1975
በመሰረቱ:መንፈሳዊ ገላ ማለት:የዘለአለም ኑሮ:ደስታ እና እውቀት ያለው ማለት ነው: ነገር ግን ይህ አሁን የያዝነው ገላ:አለማዊ ገላ: ዘለአለማዊ አይደለም:ደስተኛም አይደለም:እውቀት የተሞላበትም አይደለም: እያንዳንዳችን ይህ ገላ:ጊዝያዊ እና ወዳቂ እንደሚሆን እናውቃለን: ድንቁርናም የሞላበት ነው: ከዚህም ግድግዳ በስተጀርባ:ምን እንዳለ እንኳን ማወቅ አንችልም: የተለያዩ የስሜታዊ መረጃዎች አሉን: ነገር ግን የተወሰነ እውቀት ብቻ ነው የሚሰጡን:ፍጹም አይደሉም: አንዳንድ ግዜም በትእቢት:ለመቀናቀን እንሞክራለን:“አምላክን ልታሳየኝ ትችላለህ?“ ነገር ግን ልክ መብራት እንደጠፋች: የማየት ሃይላችን እንኳን እንደሚጠፋ እንዘነጋለን: ስለዚህ መላ ገላችን እንከን እና ድንቁርና የሞላበት ነው: መንፈሳዊ ገላ ማለት ግን:እውቀት የሞላበት እና ከገላችን የተቃረነ ነው: ይህንን መንፈሳዊ ገላችንን:በሚቀጥለው ህይወታችን ማግኘት እንችላለን:አሁን ደግሞ ይህንን መንፈሳዊ ገላ እንዴት እንደምናገኝ ጥረት ማድረግ አለብን: በነገራችን ላይ:ወደ ከፍተኛም አለማዊ ፕላኔቶችም ሂደን ገላ ለማግኘትም መዘጋጀት እንችላለን: ወይንም እንደ ውሻ እና እንደ ድመቶች ለመወለድም መዘጋጀት እንችላለን: ወይንም ዘለአለማዊ:ደስታኛ እና እውቀት ያለው:መንፈሳዊ ገላም ለመያዝ መዘጋጀት እንችላለን: ስለዚህም አዋቂ ሰው:በዚህ ህይወት ላይ የሚዘጋጀው:ለወደፊት ደስታኛ:እውቀት ያለውን እና ዘለአለማዊ መነፈሳዊ ገላን ለማግኘት ነው: ይህም በብሃገቨድ ጊታ ተገልጿል:”ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሃርማ ፓራማም ማማ:(ብጊ 15 6) የተገለፀውም:“የመንፈሳዊው አለም:ፕላኔት ወይንም ሰማይ:አንድ ግዜ ለመመለስ ከቻላችሁ:ተመልሳችሁ ወደ እዚህ ጊዜያዊ እና ወዳቂ አለም አትመለሱም” በዚህ አለማዊ ህዋ ግን:ወደ ከፍተኛው ወደ ገነት ፕላኔት እንኳን ብትሄዱ:“ብራህማ ሎካ” እንደገና ተመልሳችሁ ወደ እዚህ አለም መውደቃችሁ አይቀርም: ጥረታችሁን ግን:ወደ መጣንበት ቤታችን ወደ መንፈሳዊው አለም ለመመለስ ከሆነ እና ከተመለሳችሁ: ወደ እዚህ አለም ይህንን አለማዊ ገላ ይዛችሁ አትወለዱም: