AM/Prabhupada 0067 - ጎስዋሚዎቹ ይተኙ የነበረው ለሁለት ሰዓት ብቻ ነበረ፡፡
Lecture on SB 1.16.26-30 -- Hawaii, January 23, 1974
ምንም ቢመጣ እንኳን የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ ወደ ፊት መገስገሱን አያቆምም፡፡ ይህም ንቃት የሚስፋፋው በሽሪ ቼይታንያ መሀፕራብሁ ታላቅ ሩህሩህነት አማካኝነት ነው፡፡ ይህም ንቃት የሚስፋፋው፤ በዚህ ከካሊ ዩጋ ዘመን በድህነት ለተጠቃው ለመላው የሰው ልጅ ጥቅም ነው፡፡ ያለ ሽሪ ቼይታንያ ሩህሩህነት ግን፤ የክርሽናን ንቃትን ለማዳበር ቀላል ስራ ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ ቀላል ስራ አይደለም፡፡ ስለዚህ በሽሪ ቼታንያ ሩህሩህነት አማካኝነት የክርሽና ንቃታቸውን ያገኙ ሁሉ፤ ይህንኑ ንቃት በመቀጠል ለማዳበር እድሉ እንዳያመልጣቸው ይገባል፡፡ ይህንን እድል ማባከን ራስን እንደማጥፋት ይቆጠራል፡፡ ከመንፈሳዊው መድረክም ውጪ አትውደቁ፡፡ ይህም በቀላሉ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ የሀሬ ክርሽናንም ቅዱስ ስም ሁሌ ዘምሩ፡፡ ሁሌ ብቻ ሳይሆን ቼታንያ መሀፕራብሁ እንደመከረን ለ24 ሰዓት ቢሆንም ይመረጣል፡፡ “ኪርታንያ ሳዳ ሀሪህ” (ቼቻ፡ አዲ Adi 17.31) ሁልግዜ ቅዱስ ስምን ዘምሩ፡፡ መመሪያችንም ይኅው ነው፡፡ ቢሆንም ግን ይህንን ለማድረግ በጣም የሚያዳግተን ሆኖ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም በካሊ ዘመን ግፊት በብዙ ዓለማዊ ነገሮች ተዋክበን እንገኛለን፡፡ ስለዚህ ቢያንስ ቢያንስ አስራ ስድስት ዙር ድረስ ቅዱስ ስምን በመቁጠሪያ ላይ መዘመር ይገባናል፡፡ ይህንንም እንዳያመልጣችሁ፡፡ እንዳያመልጣችሁ፡፡ ይህንንስ አስራ ስድስት ዙር ቅዱስ ስም ለመዘመር ምን ያስቸግራል? ቢበዛ ወደ ሁለት ሰዓት የሚፈጅ ነው፡፡ ሀያ አራት ሰዓት በእጃችሁ ያለ ነው፡፡ መተኛት ትፈልጋላችሁ? እሺ ተኙ እንበል፡፡ ለአስር ሰዓት ትተኙ ይሆናል፡፡ ይህ ግን አስፈላጊ ወይንም የሚመከር አይደለም፡፡ ከስድስት ሰዓት በላይም መተኛት አያስፈልግነም፡፡ ነገር ግን ዓለማውያን ለብዙ ሰዓት መተኛት ይፈልጋሉ፡፡ ይህም ቢቻል ለ24 ሰዓት ነው፡፡ በካሊ ዩጋ ዘመን ውስጥ ያለው የሰው ልጅ ፍላጎት ይኅው ነው፡፡ መሆን ግን የለበትም፡፡ ምክንያቱም ውድ ግዜያችሁን ሁሉ በከንቱ ስለምታሳልፉት ነው፡፡ መብላት፣ መተኛት፣ በወሲብ መገናኘትን እና እራስን ሁሌ በመከላከል ያለንን ግዜ ከማባከን መቀነስ ይገባናል፡፡ እነዚህም ሙሉ በሙሉ ለመቅረት ከቻሉ ትክክለኛ ደረጃ ላይ ደረስን ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሁሉ ለቁሳዊው ገላ ብቻ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ስለሆኑ ነው፡፡ መብላት፣ መተኛት፣ መከላከል እና ወሲብ ለቁሳዊ ገላ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ ቢሆንም ግን እኛ ይህ ቁሳዊ ገላ አይደለንም፡፡ “ዴሂኖ ስሚን ያትሀ ዴሄ ኮማራም ....." (ብጊ፡ 2.13) ይህንንም ዓይነት ንቃት ለማግኘት ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ በክርሽና ንቃትም እየዳበርን በመምጣት ላይ እያለን ምን ዓይነት ሀላፊነት እንዳለን በደንብ መረዳት ይገባናል፡፡ ከስድስት ሰዓትም በላይ መተኛት አያስፈልግም፡፡ እንቅልፍንም ለመቆጣጠር ካልቻሉ ቢበዛ ስምንት ሰዓት መሆን አለበት፡፡ አስር፣ ወይንም አስራ ሁለት፣ ወይንም አስራ አምስት ሰዓት መሆን የለበትም፡፡ ይህ ከሆነማ የኑሮ ጥቅሙ ምንድነው? አንዱ አገልጋይ ሌላ በንቃቱ የገሰገሰ ተብሎ የሚታወቀውን አገልጋይ ለማየት ቤቱ ሂዶ ነበር፡፡ በዚህም ግዜ ይህ አገልጋይ እስከ ጥዋቱ ሶስት ሰዓት (9 AM) ድረስ ተኝቶ አገኘው፡፡ ታድያ ይህ ዓይነቱ አገልጋይ በንቃቱ የገሰገሰ ነው ይባላል? ይህስ ምን ዓይነት አገልጋይ ነው? ትሁት አገልጋይ ከጥዋቱ በ10 ሰዓት (4 AM) ላይ መነሳት ይኖርበታል፡፡ በ11 ሰዓት (5 AM) ገላውን ታጥቦ እና ሌሎች ዝግጅቶቹንም አድርጐ መፈፀም ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ቅዱስ ስምን ለመዘመር መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ ለ24 ሰዓት ይህን የመሰለ መንፈስ እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ ጥሩ አይደለም፡፡ ጎስቫሚዎቹ የሚተኙት ሰዓት ለሁለት ሰዓት ብቻ ነበር፡፡ እኔም ማታ ማታ መፅሀፍ ስፅፍ እገኛለሁ፡፡ የምተኛውም ከሶስት ሰዓት በላይ አይሆንም፡፡ ቢሆንም ግን አንዳንድ ግዜ ትንሽ እርፍት እወስዳለሁ፡፡ ጎስቫሚዎቹንም ለማስመሰል ጥረት አላደርግም፡፡ ይህም የማይቻል ነገር ይሆናል፡፡ ቢሆንም ግን በተቻለን መጠን ሁላችንም ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ ላይ መገኘት አይገባንም፡፡ እንቅልፍ መቀነስ ማለት ደግሞ ምግብን መቀነስ ማለት ነው፡፡ ምግብ ከቀነስን እንቅልፋችንንም ለማሳጠር እንችላለን፡፡ መብላት እና መተኛት የተያያዙ ናቸው፡፡ ከበላን በኋላ እንቅልፍ ይጫጫነናል፡፡ ስለዚህ ብዙ የምንበላ ከሆነ ብዙ መተኛትን ያመጣል፡፡ አነስ ያለ ምግብ የምንበላ ከሆነ አነስ ያለ እንቅልፍ ያስፈልገናል፡፡ ስለዚህ ከመብላት፣ መተኛት እና ከወሲብ መራቅ ይገባናል፡፡ ይህም ጥሩ ልምድ ነው፡፡ የወሲብ ግኑኝነት በተቻለ መጠን መቀነስ ይኖርበታል፡፡ ስለዚህ እውቅና የሌለው ወሲብ ውስጥ መሰማራት የተከለከለ ነው፡፡ ይህም አንዱ መመሪያችን ነው፡፡ ፈፅሞ ይቅር ለማለት ግን አንችልም፡፡ ”ይህንንም ማንም ለማድረግ የሚያዳግተው ነው፡፡“ ማንም ሰው ቢሆን ያዳግተዋል፡፡ ስለዚህ የወሲብ ፍላጎትን ለማርካት የትዳር ኑሮ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ በዚህም ትዳር ላይ የተወሰነ ፍቃድ አለ፡፡ የተሰጠውም ፍቃድ እንዲህ በማለት ነው፡፡ ”አሁን የተወሰነ ፍቃድ አለህ፡፡ ቢሆንም ግን እውቅና የሌለው እና ከትዳር ውጪ የወሲብ ግኑኝነት አይፈቀድም፡፡“ ያለበለዛ መንፈሳዊ ንቃትን ማዳበር አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ስለዚህ እነዚህ መብላት፣ መተኛት፣ ወሲብ እና መከላከልን መቆጣጠር ይገባናል፡፡ ለምሳሌ መከላከልን እንመልከት፡፡ በተለያየ መንገድ እራሳችንን ለመከላከል ለምሳሌ በጦርነት ግዜ ብዙ ሀይል እናፈሳለን፡፡ የቁሳዊው ዓለም ጥቃትም እራሳችንን እንድንከባከብ ታስገድደናለች፡፡ አገራችሁ በመከላከያ እርምጃዎች የገፋች ናት፡፡ ቢሆንም ግን ለምሳሌ ነዳጅ ቢጠፋ አገሪቷን ለመከላከል ያዳግታል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በአጭር ግዜ ውስጥ አስፈላጊ ነገሮችን በድንገት ልናጣ እንችላለን፡፡ ስለዚህም ለእነዚህ መከላከያዎች በክርሽና መተማመን ያስፈልገናል፡፡ ”አቫሽያ ራክሲቤ ክርሽና“ ይህም ማለት ሙሉ ልቦናችንን መስጠት ማለት ነው፡፡ ሙሉ ልቦና መስጠት ማለትን ሽሪ ክርሽና ገልፆታል፡፡ ”ሙሉ ልቦናህን ለእኔ ስጥ፡፡“ ሳርቫ ድሀርማ ፓሪትያጅያ (ብጊ፡ 18.66)፡፡ በዚህም ሙሉ እምነት እንዲኖረን ያስፈልገናል፡፡ ”ክርሽና ሙሉ ልቦናችንን እንድንሰጠው ጠይቆናል፡፡“ ”ስለዚህም ሙሉ ልቦናችን እንስጠው፡፡ ይህንንም በማድረግ ከአደጋ ሊያድነን ይችላል፡፡“ ይህም ማለት ሙሉ ልቦናችንን መስጠት ይባላል፡፡