AM/Prabhupada 0068 - ሁሉም ሰው መስራት ይገባዋል፡፡



Lecture on SB 6.1.45 -- Laguna Beach, July 26, 1975

ኒታይ፡ “በዚህ በሕይወታችን ውስጥ የምናደርጋቸው የተለያዪ ስራዎች ሁሉ፤ ምንም እንኳን መንፈሳዊ ወይንም ዓለማዊ እንቅስቃሴዎች ቢሆኑም እንኳን፤ ከሞት በኋላ በሚቀጥለው ሕይወታችን፤ ባደረግነው የስራ አኳያ እንደ ዓይነቱ በተመጣጠነ ደረጃ፤ የስራችን የካርማ ውጤቱ እንድነደሰት ወይንም እንድንሰቃይ ያደረገናል፡፡”

ፕራብሁፓድ፡ “ዬና ያቫን ያትሀድሀርሞ ድሃርሞ ቬሀ ሳሚሂታሀ ሳ ኤቫ ታት ፋላም ብሁንክቴ ታትሀ ታቫድ አሙትራ ቫይ” (ሽብ፡ 6.1.45)

ቀድሞ በቀረበው ጥቅስ ላይ “ዴሀቫን ና ሂ አካርማ ክርት” የሚለውን ተወያይተንበታል፡፡ ይህንን ቁሳዊ ገላ ያገኘ ሰው ሁሉ ለመኖር የግድ ስራ መስራት አለበት፡፡ ሁሉም ሰው መስራት ግዳጁ ነው፡፡ የመንፈሳዊ ገላ ይዘንም ቢሆን ስራ መስራት ያለ ነው፡፡ ይህን የቁሳዊ ገላ ይዘንም ቢሆን መስራት አለብን፡፡ ምክንያቱም የስራ መነሻዋ ነፍስ ናት፡፡ ነፍስ ዘለዓለማዊ እና ሕያው ናት፡፡ በስራ እንቅስቃሴም ሁሌ የምትገኝ ናት፡፡ ቁሳዊ ገላ እስካለን ድረስ እንቅስቃሴ የሚቀጥል ነው፡፡ ስራ ሁልግዜ አለ፡፡ የሰው ልጅ ያለ ስራ መቀመጥ አይችልም፡፡ በብሀገቨድ ጊታም እንደተጠቀሰው “ለአንድ አፍታ እንኳን አንድ ሰው ያለ ስራ መቀመጥ አይችልም፡፡” ይህም ስራ የነዋሪ ሕያው ሰው ምልክት ነው፡፡ ይህም ስራ የሚካሄደው ከአገኘነው የቁሳዊ ገላ አንፃር ነው፡፡ ውሻ ሲሮጥ ይታያል፡፡ የሰውም ልጅ ሲሮጥ ይታያል፡፡ የሰው ልጅ በመኪና መሮጥ ስለቻለ ግን ከእንስሳ በላይ በጣም የሰለጠነ መስሎት ይታየዋል፡፡ ሁለቱም በመሮጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቢሆንም ግን የሰው ልጅ የተለየ ዓይነት ቁሳዊ ገላ ይዞ ይገኛል፡፡ በዚህም የሰው ልጅ አእምሮ መኪና ወይንም ብስክሌት በመገንባት እና በእነዚህም የመሮጥ ሀይልን በመፍጠር ሲጠቀምባቸው ይታያል፡፡ የሚያስበውም “እኔ ከውሾች በላይ የመሮጥ አቅም ስላለኝ ከውሾቹ በላይ የሰለጠንኩ ሆኜ እገኛለሁ፡፡” በማለት ነው፡፡ ይህም የግዜው ዓለማዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ያልተረዳውም ነገር አለ፡፡ ይህም በተለያየ ፍጥነት የመሮጥ ፋይዳው ምን እንደሆነ ባለመረዳቱ ነው፡፡ ይህም በ50 ማይል ፍጥነት፣ በ5 ማይል ፍጥነት ወይንም በ5000 ማይል ፍጥነት ቢሮጥም እንኳን ፋይዳው ምንድነው? የምናየው ጠፈር በስፋቱ ወሰን የለሽ ነው፡፡ ምንም ዓይነት አዲስ ፍጥነት ብንጨምር እንኳን ሁልግዜ በቂ ሆኖ አናገኘውም፡፡ ሁሌ ፍጥነቱን በቂ ሆኖ አናገኘውም፡፡ ይህ የሕይወታችን ዓላም መሆን አይገባውም፡፡ “ከውሻው በላይ የመሮጥ ሀይል ፈጥሬያለሁ ስለዚህ እኔ ከውሻው በላይ የሰለጠንኩ ነኝ፡፡” የሚል አስተሳሰብ ይዘናል፡፡ “ፓንሀስ ቱ ኮቲ ሻታ ቫትሳራ ሳምፕራጋምዮ ቫዮር አትሀፒ ማናሶ ሙኒ ፑንጋቫናም” ”ሶ ፒ አስቲ ያት ፕራፓዳ ሲምኒ አቪቺንትያ ታትቬ ጎቪንዳም አዲ ፑሩሻም ታም አሀም ብሀጃሚ“ (ብሰ፡ 5 34) ይህስ ፍጥነት ለምንድን ነው? ይህም ፍጥነት የሚያስፈልገን ወደ አንድ መድረሻ ለመድረስ ስለምንፈልግ ነው፡፡ ወደ እዚህ መድረሻም ፍጥነት ያስፈልጋል፡፡ ትክክለኛው መድረሻ ደግሞ “ጎቪንዳ ወይንም ቪሽኑ ነው፡፡” ስለዚህም ይህ ጥቅስ ቀርቦልናል፡፡ “ናቴ ቪድሁህ ሳቫርትሀ ጋቲም ሄ ቪሽኑ” ዓለማውያን በተለያየ ፍጥነት ለመሮጥ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ትክክለኛው የፍጥነቱ መድረሻ ምን መሆን እንዳለበት የተረዱበት ደረጃ ላይ አልደረሱም፡፡ በሕንድ አገር አንድ የታወቀ ”ራቢንድራናት ታጎሬ“ ተብሎ የሚታወቅ ባለቅኔ ነበረ፡፡ በለንደን ውስጥም እያለ አንድ መስተአምር ወይንም አርቲክል ፅፎ ነበር፡፡ ይህንንም አንብቤው ነበር፡፡ በእነዚህም በምእራባውያን አገሮች ውስጥ ብዙ መኪናዎች ይታያሉ፡፡ እነዚህም መኪናዎች በከፍተኛ ፍጥነት ሲሯሯጡ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም አይቶ ባለቅኔው ራቪንድራናት ታጎሬ እንዲህ ብሎ ነበረ፡፡ “እነዚህ እንግሊዞች ያላቸው አገር ትንሽ ደሴት ናት፡፡ በዚህም በከፍተኛ ፍጥነት በተሽከርካሪ የሚሄዱ ከሆነ ወደ ባህር ውስጥ ወድቀው እንዳይጠፉ፡፡” ብሎ ፅፎ ነበር፡፡ እንዲህም በማለት በተዘዋዋሪ ጠቅሶ ነበር፡፡ በዚህ ዓይነት ፍጥነት የሚሮጡትስ ለምንድን ነው? እንደዚህም ሁሉ እኛም ወደ ሲኦል ለመሄድ በመሯሯጥ ላይ እንገኛለን፡፡ ይህ ነው አሁን ያለንበት ደረጃ፡፡ ምክንያቱም ትክክለኛው መድረሻችን ምን እንደሆነ የተረዳንበት ደረጃ ስላልደረስን ነው፡፡ መድረሻዬ ምን እንደሆነ ሳላውቅ መኪናዬን በሙሉ ፍጥነት የምነዳው ከሆነ ውጤቱስ ምን ሊሆን ይችላል? ውጤቱም ትልቅ አደጋ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ ለምን እንደምንሮጥ ማወቅ አለብን፡፡ ይህም የሚመሰለው ልክ እንደ ወንዝ በጎርፍ እየፈሰሰ በመሄድ መድረሻው ግን ወደ ባህር እንደሚሆነው ነው፡፡ ወንዙም ወደ ባህሩ ገብቶ በሚቀላቀልበት ግዜ ሌላ የሚሄድበት መድረሻ የለውም፡፡ ስለዚህ መድረሻችን ምን እንደሆነ ሁሌ በመገንዘብ የሕይወታችንን መንገድ መቀየስ ያስፈልገናል፡፡ መድረሻችንም ቪሽኑ ወይንም ዓብዩ ጌታ ብቻ መሆን አለበት፡፡ እኛ የዓብዩ ጌታ ቁራሽ አካል እና ወገን ነን፡፡ በተወሰነም ምክንያት ወደ እዚህ ቁሳዊ ዓለም ለመውደቅ በቅተናል፡፡ ስለዚህ የሕይወታችን መድረሻ እና ዓላማ ወደ ዓብዩ ጌታ መንፈሳዊው ዓለም ወይንም መንግስተ ሰማያት መመለስ መሆን አለበት፡፡ መድረሻችንም ይህ ነው፡፡ ሌላ መድረሻም ሊኖረን አይገባም፡፡ ስለዚህ ይህ የክርሽና ንቃተ ማህበር እና እንቅስቃሴ የሚያስተምረን እንዴት ሕይወታችንን ለዚሁ ዓላማ ማስተካከል እንደምንችል ለማስተማር ነው፡፡ ታድያ የሕይወታችን ግብ ምንድነው? ይህም ወደ ዋነኛው ቤታችን ወደ መንፈሳዊው ዓለም መመለስ ነው፡፡ በአሁኑ ደረጃ ግን ወደ ተቃረነ መንገድ እንሄድ ይሆናል፡፡ ይህም ወደ ሲኦል መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም መድረሻችን አይደለም፡፡ መሄድ ያለብን ግን ወደ መንፈሳዊው ዓለም ዋነኛው ቤታችን ነው፡፡ የእኛም ቅስቀሳ ይኅው ነው፡፡