AM/Prabhupada 0073 - ቫይኩንትሀ ማለት ጭንቀት የሌለበት ቦታ ማለት ነው፡፡



Lecture on BG 10.2-3 -- New York, January 1, 1967

ይህንን የመንፈሳዊ አገልግሎት ማድረግ የሚገባችሁ፡ እዚህ ብቻ አይደለም፡፡ ይህንን መንፈሳዊ ስልት፡ በቤታችሁም መማር እና ማከናወንም ትችላላችሁ፡፡ የተለያዩም ጥሩ ጥሩ ነገሮችም በቤታችሁ ማዘጋጀት ትችላላችሁ፡፡ ይህንንም ለክርሽና ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡ ይህ አስቸጋሪ አይደለም፡፡ እኛም በቀን በቀን ጥሩ ጥሩ ነገር ለክርሽና እያዘጋጀን በማቀረብ፡ የውዳሴ (ማንትራ)ቃላቶችን እንዘምራለን፡፡ “ናሞ ብራህማንያ ዴቫያ ጎ ብራህማና ሂታyያቻ ጃጋድ ሂታያ ክርሽናያ ጎቪንዳያ ናሞ ናማሃ” ይኅው ነው፡፡ ይህ አስቸጋሪ አይደለም፡፡ ማንኛችንም ብንሆን፡ ምግብ አዘጋጅተን ለክርሽና ማቅረብ እንችላለን፡፡ ከዚያም ከቤተሰብ ጋር ወይንም ከጓደኞቻችን ጋራ ተቀምጠን መቅረብ እንችላለን፡፡ በክርሽናም ስዕል ፊት ለፊት ተቀምጠን መዘመር እንችላለን፡፡ “ሀሬ ክርሽና ሀሬ ክርሽና፡ ክርሽና ክርሽና፡ ሀሬ ሀሬ፡ ሀሬ ራማ፡ ሀሬ ራማ፡ ራማ ራማ፡ ሀሬ ሀሬ“ እንደዚህም በማድረግ ንጹህ የሆነ ኑሮ መኖር እንችላለን፡፡ ውጤቱንም ማየት ትችላላችሁ፡፡ እያንዳንዱ ቤት እና እያንዳንዱ ሰው፡ ይህንን መመሪያ ተከትሎ ክርሽናን ለመረዳት ቢሞክር፡ መላው ዓለም ”ቫይኩንታ“ ይሆን ነበረ፡፡ ቫይኩንታ ማለት ጭንቀት የሌለበት ማለት ነው፡፡ “ቫይኩንታ” ቫይ ማለት ”ያለ ምንም“ ሲሆን “ኩንታ” ማለት ደግሞ ጭንቀት ማለት ነው፡፡ ይህ ዓለም ብዙ ጭንቀት የሞላበት ነው፡፡ “ሳዳ ሳሙድቪግና ድሂያም አሳድ ግራሃት” (ሽብ፡ 7.5.5) ይህም ምክንያቱ፡ ይህንን ግዜያዊ ምድራዊ አካልን ወይንም ዓለማዊ ኑሮ ስለያዝን ነው፡፡ ስለዚህም ሁልግዜ፡ በጭንቀት ተመስጠን እንገኛለን፡፡ የዚህም ተቃራኒ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ይገኛል፡፡ እዚህም ያሉት ፕላኔቶች “ቫይኩንታ” ብለው ይታወቃሉ፡፡ ቫይኩንታ ማለት ጭንቀት የሌለው ማለት ነው፡፡ ሁሌ ፍላጎታችንም ከጭንቀት ነፃ ለመሆን ነው፡፡ ሁላችንም ከጭንቀት ነፃ ለመሆን ብዙ ጥረት እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ከዚህ ጭንቀት እንዴት ነፃ ለመሆን እንደምንችል አልተረዳንም፡፡ በአልኮል እና በሚያሰክር መጠጥ፡ ከጭንቀት ነፃ ለመሆን አንችልም፡፡ ይህም ድራግ ወይንም መጠት መውሰድ እንድንረሳ ብቻ ነው የሚያደርገን፡፡ አንዳንድ ግዜ በዚሁ መንገድ ሁሉን እንረሳለን፡ ነገር ግን ልቦናችንን ማወቅ ስንጀምር ግን፡ ጭንቀቱ እንዳልሄደ ለመረዳት እንበቃለን፡፡ ስለዚህ እራስን ማስከር ሊረዳን አይችልም፡፡ ከጭንቀት ነፃ ለመሆን ከፈለጋችሁ ግን፡ እንደዚሁም ዘለዓለማዊ የደስታ እና የእውቀት ኑሮ ለመኖር ከፈለጋችሁም፡ ይህንን የመንፈሳዊ ፈለግ መከተል አለባችሁ፡፡ እንደዚሁም ክርሽናን ለመረዳት ትችላላችሁ፡፡ በእነዚህም ቅዱስ መጻህፍት ሁሉ በመደንብ ተገልጿል፡ “ናሜ ቪድሁህ ሱራ ጋናህ” (ብጊ፡ 10.2) ክርሽናን በቀላሉ ማንም ሰው ሊረዳው አይችልም፡፡ ነገር ግን መንገዱም ተገልጿል፡፡ “ሴቮን ሙክሄ ሂጂቫዶ ስቫያም ዔቫ ስፑራቲ አዳሃ” (ብሰ 1 2 234) ይህ ነው መነገዱ፡፡ (ክርሽናን በፍቅር ማገልገል) ስለዚህም መንገድ በ “ሽሪማድ ብሃገቨታም” ቅዱስ መጽሃፍ ውስጥ፡በተለያየ መንገድ በደንብ ተገልጿል፡፡ በአንዱም ወገን እንዲህ ተብሎ ተገልtጿል፡ “ግያኔ ፕራያሳም ኡዳፓስያ ናማንታ ኤቫ” “ጂቫንቲ ሳን ሙክሃሪታም ብሃቫዲያ ቫርታም ስትሃኔ ስትሂታሃ ስሩቲ ጋቲም ታኑ ቫን ማኖብሂር” “ዬፕራያሾ ጂታ ጂቶ ፒ አሲ ታይስ ትሪ ሎክያም” (ሽብ፡ 10.14.3) ይህም በጣም ደስ የሚይሰኝ ቃል ነው፡፡ እንዲህም ተብሏል፡፡ “አጂታ” ክርሽናን ማንም ሊያውቀው አይችልም፡፡ የአማላክ ሌላው ስሙ “አጂታ” ነው፡፡ አጂታ ማለትም ማነም ቢሆን ሊረታው አይችልም ማለት ነው፡፡ ማንም ቢሆን በቀላሉ ሊቀርበው አይችልም፡፡ ይሁን እንጂ፡ የማይረታው አምላክ ይረታል፡፡ “አጂታ ጂቶ ፒ አሲ” አምላክ ጌታ በቀላሉ ሊታወቅ ባይችልም፡ በቀላሉ ሊረታ ባይችልም፡ ይሁን እንጂ፡ ሊረታ ይችላልህ፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? “ስታሃኔ ስቲታሃ” (ይህም በፍቅር በማገልገል ብቻ ነው፡፡)