AM/Prabhupada 0081 - በፀሀይ ፕላኔት ውስጥ የሚገኙት ነዋሪዎች ገላቸውእሳት የተሞላበት ነው፡፡



Lecture on BG 2.13 -- New York, March 11, 1966

እዚህ እንዲህ ተብሎ ተገልጿል፡፡ "ድሂራ፣ ድሂራ" "ዴሂኖ ስሚን ያትሀ ዴሄ ኮማራም ዮቫናም ጃራ" "ታትሀ ዴሀንታራ ፕራፕቲር ድሂራስ ታትራ ና ሙህያቲ" (ብጊ፡ 2.13) "ዴሂናህ" ዴሂናህ ማለት "ይህንን ቁሳዊ ወይንም ስጋዊ ገላ የወሰደ" ማለት ነው፡፡ "አስሚን" አስሚን ማለት ደግሞ "በዚህ ዓለም" ወይም “በዚህ ሕይወት” ማለት ነው፡፡ “ያትሀ” ማለት “እንደ” ሲሆን “ዴሂ” ማለት ደግሞ “በስጋዊ ገላ ውስጥ” ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም “ዴሂናህ” ማለት “ስጋዊ ገላ የወሰደ ሰው” ማለት ነው፡፡ “ዴሂ” ማለት ደግሞ “በስጋዊ ገላው ውስጥ” ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እኔ በስጋዊ ገላዬ ውስጥ ተቀምጫለሁ፡፡ ስጋዊ ገላዬ እራሱ ግን አይደለሁም፡፡ ይህም የሚመሰለው ልክ በሸሚዛችን እና በኮታችን ውስጥ ሆነን እንደተቀመጥነው ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ እኔም በስጋዊ ገላዬ ውስጥ ቁጭ ብዬ እገኛለሁ፡፡ ይህም ቁሳዊው ወይንም ስጋዊ እና ረቂቅ በሆነው ገላዬ ውስጥ ነው፡፡ (ረቂቅ ገላ ሀሳብን እና አእምሮን ያጠቃልላል፡፡) ይህ ቁሳዊ ወይንም ስጋዊ ገላችን የተገነባው ከአፈር፣ ከውሀ፣ ከእሳት፣ ከአየር እና ከኢተር ነው፡፡ መላ ቁሳዊ ገላችን የተገነባው በእነዚህ ነው፡፡ በምድር ላይ ወይንም በዚህ ፕላኔታችን ላይ አፈር በርከት ብሎ ይገኛል፡፡ በየትም ቦታ ላይ የሚገኘው ቁሳዊ ገላ ሁሉ የተገነባው ከእነዚህ በአምስት ከተጠቀሱት ነገሮች ነው፡፡ መሰረታዊ ንጥረ ነገሮቹ እነዚህ አምስቱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ይህንን ሕንፃ እንውሰደው፡፡ ይህ የምናየው መላው ሕንፃ የተገነባው በአፈር፣ ውሀ እና በእሳት ነው፡፡ ለምሳሌ አፈርን ወስዳችሁ እንደ ጡብ በመስራት እና በእሳት ውስጥ በመክተት የምትገነቡበትን ሸክላ ታዘጋጃላችሁ፡፡ ይህም የተሰራው አፈርን በውሀ በመበጥበጥ፣ ጡብ የመሰለን ቅርጽ በመስጠት እና ይህንን ጡብ ወደ እሳት ውስጥ በመክተት ነው፡፡ ከዚያም በእሳቱ አማካኝነት ጠንካራ ሲሆን ሕንፃውን ለመስራት ሸክላውን በመጠቀም መገንባት እንጀምራለን፡፡ ስለዚህ በቀላሉ እንደምናየው ይህ ሁሉ የአፈር፣ የውሀ እና የእሳት ቅንብር ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ስጋዊ ገላችንም የተገነባው በአፈር፣ በውሀ፣ በእሳት፣ በአየር እና በኢተር ነው፡፡ አየርም እንዲሁ በገላችን ውስጥ ሁልግዜ እንደተላለፈ ነው፡፡ እንደምታውቁትም አየር በገላችን ውስጥ ሁልግዜ ያለ ነው፡፡ ይህ በውጭ የምናየው ቆዳችን ከአፈር የተገነባ ሲሆን በሆዳችን የሚገኝ ደግሞ እሳት አለ፡፡ ያለ ሙቀት ምግባችንን በሆዳችን ውስጥ ለመፍጨት አንችልም፡፡ አያችሁ? ይህም በሆዳችን የሚገኘው እሳት ሲቀዘቅዝ ምግብ የመፍጨት አቅማችን ይቀንሳል ወይንም ይበላሻል፡፡ እንደዚህም ብዙ ምሳሌ መስጠት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ በዚህ ምድር ላይ ይህንን ስጋዊ ገላ ይዘናል፡፡ አፈርም በርከት ብሎ የሚገኝበት ነው፡፡ እንደዚህም ሁሉ በሌሎች ፕላኔቶች ላይ ውሀ በበርካታነት የሚገኝባቸው ፕላኔቶች ይገኛሉ፡፡ በሌሎች ፕላኔቶች ደግሞ እሳት በርከት ብሎ የሚገኝባቸው ፕላኔቶች ይገኛሉ፡፡ለምሳሌ በፀሀይ ውስጥ እንደምናየው ነው፡፡ በፀሀይ ውስጥም ነዋሪ ነፍሳት ይገኛሉ፡፡ ገላቸውም በእሳት የተገነባ ነው፡፡ በእሳትም ውስጥ ለመኖር የሚያስችላቸው ተፈጥሮ አላቸው፡፡ በእሳት ውስጥ ሆነው ለመኖር ይችላሉ፡፡ እነዚህም ሁሉ በቫሩና ሎካ ወይንም በቪነስ ውስጥም የሚገኙ ነፍሳት ለኑሮ አመቺ የሆነ የተለያየ ገላ ይዘው ይገኛሉ፡፡ ይህም የሚመሰለው እዚህ ምድር ላይም በውሀ ውስጥ እንደሚኖሩት ፍጥረታት ነው፡፡ በውሀ ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት የተለየ ዓይነት ገላ ይዘው ይገኛሉ፡፡ ለብዙ ዓመታት ከውሀ ውስጥ ሳይወጡ የሚኖሩ ፍጥረታት አሉ፡፡ በውሀ ውስጥም በመሆን ተመችቷቸው ለመላ ሕይወታቸው የሚኖሩ አሉ፡፡ እነዚህንም ፍጥረታት ከውሀ ወደውጪ ብታወጧቸው ለመሞት ይበቃሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የሰው ልጅም በምድር ላይ ተመችቶት ሲኖር ይታያል፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅን በውሀ ውስጥ ብትከቱት ለሞት ይበቃል፡፡ ምክንያቱም በተፈጥሮ የተሰጠን ስጋዊ ገላ በምድር እንጂ በውሀ ውስጥ ለመኖር አመቺነት ስለሌለው ነው፡፡ ሌላ ምስሌ ለመስጠት እንደ አሞራ ከባድ የሆነች ወፍ ለመብረር ትችላለች፡፡ ይህችም በዓብዩ አምላክ ለመብረት እንድትችል የተፈጠረች ስለሆነች ነው፡፡ ቢሆንም ግን የሰው ልጅ የፈጠረው የሚበር አይሮፕላን ወደ መሬት በብልሽት ምክንያት ሲከሰከስ እናየዋለን፡፡ ይህም ሰው ሰራሽ በራሪ ነገር በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ በተፈጥሮ የምናየው ዓይነት ቅንብር ይህን ይመስላል፡፡ እያንዳዱ ነዋሪ ፍጥረት ባካባቢው ለመኖር የሚያስችለውን አመቺ ቁሳዊ ገላ ይዞ ይገኛል፡፡ “ዴሂኖ ስሚን ያትሀ ዴሄ” (ብጊ፡ 2.13)የዚህስ ገላ የተፈጥሮ ሂደት እንዴት ነው? በዚህም የብሀገቨድ ጊታ ጥቅስ ውስጥ ይኅው ነጥብ ተገልፆልናል፡፡ ይህ ገላችን የሚቀያየረው እንዴት እንደሆነ ተገልፆልናል፡፡ ይህስ እንዴት ነው? በዚህ የዓለማዊ አስተሳሰብ ስለተበከልንም ይህንን ለመረዳት ያዳግተን ይሆናል፡፡ ይህም ነፍሳችን ወይም እኛ ማለት ስጋዊ ገላችን ነው ብለን ስለምናስብ ነው፡፡ የመንፈሳዊ ትምህርት የመጀመሪያው ኤ ቢ ሲ ዲ እውቀት ይህ ቁሳዊ ወይም ስጋዊ ገላችን እኛ እንዳልሆንን በትክክል መገንዘቡ ነው፡፡ አንድ ሰው ይህንን በትክክል ያልተረዳ ከሆነ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ፈፅሞ ሊዳብር ወይም ሊበለፅግ አይችልም፡፡ ግንዛቤው ትክክል የሚሆነው “እኔ ይህ ቁሳዊ ገላ አይደለሁም፡፡” ብሎ በትክክል ሲረዳ ነው፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያው የብሀገቨድ ጊታ ትምህርት የሚወሰደው ይህንን በትክክል በመገንዘብ ነው፡፡ እዚህም እንደተገለፀው “ዴሂኖ ስሚን” ሲባል "ዴሂ“ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ነፍስን ነው፡፡ ነፍስ ”ዴሂ“ ስንል ነፍስን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህንን ስጋዊ ገላ የተቀበለው ነፍስ ”ዴሂ“ ይባላል፡፡ ”አስሚን“ የሚለው ቃል ደግሞ ”ይገኛል“ ማለት ነው፡፡ ነፍስ በውስጥ ሳትቀያየር ትገኛለች ስጋዊ ገላው ግን በየግዜው ሲቀያየር ይገኛል፡፡