AM/Prabhupada 0086 - ለምንድነው የተለያዩ ነገሮች የሚታዩት

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

ለምንድነው የተለያዩ ነገሮች የሚታዩት
- Prabhupāda 0086


Sri Isopanisad, Mantra 9-10 -- Los Angeles, May 14, 1970

በምድር ላይ የተለየ ደረጃ ያላቸው ሰዎች የምናየው ለምንድን ነው? የሁሉም ስጋዊ ገላ ሀሞት፣ ንፍጥ እና አየር የሞላበት ገላ ሆኖ እያለ ለምን የሁሉም ሰው ደረጃ የተመሳሰለ አልሆነም? ይህም የመንፈሳዊ እውቀታቸውን ስለማያዳብሩ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ያልተመሳሰለ ደረጃ ያላቸው ሰዎች በመሀላችን ለምን እናያለን? አንድ ሰው በሚሊዮን የሚቀጠር ሀብት ሲኖረው እናያለን፡፡ ሌላው ሰው ደግሞ ከትውልዱ ጀምሮ በቀን ሁለት ግዜ እንኳን የሚበላው ሲያጣ እናያለን፡፡ ይህም ምንም እንኳን የዕለት እንጀራውን ለማግኘት በጣም የሚታገል ቢሆንም ነው፡፡ ታድያ ይህንን ልዩነት የምናየው ለምንድን ነው፡፡ አንዱ ሰው በጣም ምቾት የተሞላበት ህይወት ሲያገኝ ሌላው ለምን ስቃይ የተሞላበት ኑሮ ውስጥ ይገኛል? ስለዚህ ካርማ ተብሎ የሚታወቀው የተፈጥሮ ሕግ ስላለ ነው፡፡ ይህም ሕግ የሚሰራው ለእያንዳንዱ ግለሰብ ነው፡፡ እውቀት ማለትም ይህንን መገንዘብ ነው፡፡ ሽሪ ኢሾፓኒሻድ የተባለውም መፅሀፍ ስለዚህ ገልፆልናል፡፡ “አንያድ ኤቫሁር ቪድያያ አንያድ አሁር አቪድያያ” በድንቁርና ውስጥ ያሉት ሰዎች ሁሉ የሚያዳብሩት እውቀት የተለየ እርምጃ ውስጥ ሊከታቸው የሚችለውን ነው፡፡ ሌሎች በትክክለኛ እውቀት ላይ የተሰማሩት ደግሞ የሚያዳብሩት እውቀት የተለየ ዓይነት ነው፡፡ ተራ የሆኑት ሰዎች እኛ የምንሰራው ነገር ሁሉ አያስደስታቸውም፡፡ ይህም የክርሽና ንቃትን ማዳበሩን ነው፡፡ በዚህም ስራችን በመደነቅ ሲያዩን ይገኛሉ፡፡ ጋርጋ ሙኒ ትላንትና ማታ ሲነግረኝ ሰዎች እንዲህ እያሉ ይጠይቁናል ብሎ ነበር፡፡ “ይህንን ያህል ገንዘብ የምታገኙት ከየት እያመጣችሁት ነው?" ”እንደምናየው ብዙ መኪና እና ትላልቅ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃዎችም እየገዛችሁ ነው፡፡“ "ከዚህም በተረፈ ሀምሳ ስልሳ የሚሆኑ ሰዎች በቀን እያስተዳደራችሁ ነው፡፡ ይሄ ሁሉ ከየት የሚመጣ ገንዘብ ነው?" (ሳቅ) እንደዚህም በመሰለ ሁኔታ ሰዎች እየተገረሙ ነው፡፡ እኛም ደግሞ እነዚህ ተንኮለኞች ለምን እንደተገረሙ በማየት እኛም እየተገረምን ነው፡፡ ሆድን ለሞሙላት ብቻ ከመጠን ባለፈ ሁኔታ ሲሰሩ ይታያሉ፡፡ ስለዚህ ብሀገቨድ ጊታ እንዲህ ገልፆልናል፡፡ “ያ ኒሻ ሳርቫ ብሁታናም ታስያም ጃግራቲ ሳምያሚ” እንደምናየውም እነዚህ ሰዎች ተኝተው ይገኛሉ፡፡ የሚመለከቱንም እኛ ግዜያችን እያባካንን እያለን እንደሆነ በማድረግ ነው፡፡ ይህም የተቃረነ አስተያየት ነው፡፡ ለምን? ምክንያቱም የእነሱ የስራ መስመር የተለየ ሲሆን የኛም የስራ መስመር የተለየ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ታድያ አሁን የትኛው የስራ መስመር ትክክለኛ የሆነ መወሰን ይኖርበታል፡፡ እነዚህም ርእሶች ሁሉ በቬዲክ መፃህፍት ውስጥ ጥሩ በሆነ መንገድ ተገልፀውልን ይገኛል፡፡ ይህንንም ኢሾፓኒሻድን የመሰለ ሌላ ጋርጋ ኡፓኒሻድ የሚባል መፅሀፍ አለ፡፡ በዚህም በጋርጋ ኡፓኒሻድ ውስጥ ስለ ምሁራን ባል እና ሚስት ውይይት ተገልፆልናል፡፡ ባልየውም ሚስቱን እንዲህ በማለት ሲያስተምራት ይገኛል፡፡ “ኤታድ ቪዲትቫ ያህ ፕራያቲ ሳ ኤቫ ብራህማና ጋርጊ” “ኤታድ አቪዲትቫ ያሀ ፕራያቲ ሳ ኤቫ ክርፓና” የትክክለኛው ባህል እውቀት ይህንን የመሰለ ነው፡፡ “እያንዳንዱ ሰው ይወለዳል ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ለመሞት ይበቃል” ስለዚህም የተለየ አመለካከት ሊኖር አይችልም፡፡ እኛም ሁላችንም ሟቾች ነን እነርሱም ሁሉ ሟቾች ናቸው፡፡ እንደዚህም ይሉ ይሆናል “ስለ መወለድ፣ መታመም፣ ማርጀት እና መሞትን ታሰላስሉ ይሆናል፡፡” ታድያ እናንተ ገና ለገና የክርሽናን መንፈሳዊ ንቃት በማዳበር ላይ ስለምትገኙ እነዚህ አራት ክስተቶች እናንተን ሊያጠቋችሁ አይችልም ማለት ነውን? ከነዚህስ አራት መሰረታዊ የተፈጥሮ ጫናዎች ነፃ ናቸሁ ማለት ነውን? አይደለም፡፡ ይህም ሊሆን አይችልም፡፡ እውነታው ግን ጋርጋ ኡፓኒሻድ እንደገለፀው ነው፡፡ “ኤታድ ቪዲትቫ ያህ ፕራያቲ“ አንድ ሰው የራሱን ማንነት በትክክል ተረድቶ ይህንን ገላ በሞት ግዜ የሚለቅ ከሆነ ”ሳ ኤቫ ብራህማና ማለትም እርሱ ብራህማና ነው፡፡ ብራህማና .......በዚህም ምክንያት ይህንን ቅዱስ የሆነውን ክር አቅርበንላችኋል፡፡ የሕይወት ሚስጥሯ ምን እንደሆነ ሁሌ ለማወቅ ጥረት አድርጉ፡፡ ይህም የብራህማና ሕይወት ነው፡፡ “ቪጃናትሀ” ይህንንም ቪጃናታሀ የሚለውን ቃል አንብበነዋል፡፡ ሁሉንም ነገር በትክክል የተረዳ ከሆነ እና ሁሉንም ነገር ልክ እንደፍጥረታቸው የተረዳ ከሆነ እርሱም ብራህናማ ይባላል፡፡