AM/Prabhupada 0087 - የቁሳዊው ዓለማት ህግጋት፡፡



Sri Isopanisad Invocation Lecture -- Los Angeles, April 28, 1970

አዎ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ ለመኖር ያላቸው ግዜ የተወሰነ እና ጊዝያዊ ናቸው፡፡ በዚህም በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ስድስት ዓይነት ለውጦች ይታያሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ መወለድ ከዚያም ማደግ ከዚያም ቀጥሎ የተወሰነ ጊዜ መቆየት ይመጣል፡፡ ከዚያም መውለድ ከዚያም ማርጀት ከዚያም መጥፋት ይመጣል፡፡ ይህ የቁሳዊው ዓለም የተፈጥሮ ሕግጋት ነው፡፡ አበባ ልክ እንደ እንጭጭ አበባ ሆኖ ይፈጠራል፡፡ ከዚያም ያድጋል ከዚያም ለሁለት ወይንም ለሶስት ቀን ይቆያል፡፡ ከዚያም ዘርን ያፈራል ከዚያም ቀስ በቀስ መድረቅ ይጀምር እና ከግዜ በኋላ ይጠፋል፡፡ (በጎን በኩል) እንዲህ አድርገህ ተቀመጥ። ይህም "ሳድ ቪካራ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስድስት ዓይነት ለውጦች፡፡ ይህንንም ዓይነት የተፈጥሮ ሕግ በምንም ዓይነት የቁሳዊ ዓለም ሳይንስ ልትቀይሩት አትችሉም፡፡ አይቻልም፡፡ እንዲህ ማሰብ ድንቁርና ነው፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ለማዳን ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜም "በሳይንስ እድገት በአንድ ወቅት ላይ የሰው ልጅ የማይሞት ሊሆን ይችላል፡፡" ብለው በሞኝነት ያስባሉ፡፡ ራሽያኖች እንዲህ ሲሉ ይገኛሉ፡፡ ይህም ድንቁርና ነው፡፡ "አቪድያ" የቁሳዊ ዓለምን የተፈጥሮ ሕግ ልታቆሙት አትችሉም፡፡ ስለዚህ በብሀገቨድጊታ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "ዳይቪሂ ኢሻ ጉናማዪ ማማ ማያ ዱራትያያ" (BG 7.14) የቁሳዊው ዓለም የተፈጥሮ ሂደት በሶስት ዓይነት የተከፈለ ነው፡፡ "ሳትቫ ጉን፣ ራጃ ጉን፣ ታሞ ጉን" እነዚህም ትሪ ጉና ተብለው ይታወቃሉ፡፡ የጉና ሌላው ትርጉሙ ደግሞ "ገመድ" ማለት ነው፡፡ ገመድንም እንዳያችሁት በሶስት ገመዶች ተጠምሮ የተጠላለፈ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቀጠን ያለ ገመድ ይኖራል፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ሶስት ዓይነት ገመዶች ይጠላለፋሉ፡፡ ከዚያም በኋላ ሶስት ገመዶች ስለሚጨመሩ ገመዱ በጣም ጠንካራ ይሆናል፡፡ እንደዚህም ሁሉ እነዚህ ሶስት ዓይነት ሳትቫ፣ ራጃ እና ታሞ ጉና ተብለው የሚታወቁት ባሕሪዎች በአንደበታችን ውስጥ ተቀላቅለው ይገኛሉ፡፡ ከዚያም አንድ የተወሰነ ውጤት ያመጣሉ፡፡ ከዚያም በተጨማሪ ይቀላቀላሉ፡፡ ይህም በተደጋጋሚ ይቀጥላል፡፡ በዚህም መንገድ 81 ግዜ ተቀላቅለው ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ጉና ማዪ ተብላ የምትታወቀው ማያ ወይንም መልአክ በዚህ ዓይነት ባህሪዎች ጥፍር አድርጋ አስራን ትገኛለች፡፡ ስለዚህ በዚህ ከተጠፈርንበት ቁሳዊ ዓለም ለመውጣት በጣም አዳጋች ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ይህም እስርስር የሚያደርግ ይባላል፡፡ ስለዚህ "አፓቫርጋ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ስርዓት ማለት ከዚህ ከፓቫርጋ ስርዓት ነፃ የሚያደርገን ማለት ነው፡፡ ትላንትና ይህ "ፓቫርጋ" የሚለው ቃል ምን እንደሆነ ለጋርጋሙኒ ሳስረዳው ነበረ፡፡ ይህ "ፓቫርጋ" ከሚለው ቃል "ፓ" የሚለው ቃል የሳንስክሪት አልፋቤቶች መስመር የመጀመሪያው ቃል ነው፡፡ የዴቫናጋሪንም ቋንቋ ያጠናችሁም ሁሉ ይህንን ልትረዱት ትችላላችሁ፡፡ በዴቫናጋሪ ቋንቋ የተለያዩ አልፋቤቶች አሉ፡፡ እነዚህም ለምሳሌ በአንዱ መስመር እንደሚከተለው እናገኛለን፡፡ "ካ፡ ክሀ፡ ጋ፡ ግሀ፡ ና፡ ቻ፡ ችሀ፡ ጃ፡ ጅሀ፡ ና" በዚህም መንገድ አምስት ጥንድ ቃላቶች በአንድ መስመር ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚያም አምስተኛው መስመር ላይ "ፓ፡ ፕሀ፡ ባ፡ ብሀ፡ ማ" የሚባሉት ቃላቶች ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ከዚህ "ፓቫርጋ" ከሚለው ቃል "ፓ" የሚለው የመጀመሪያው ቃል ነው፡፡ "ፓ" ማለት ፓርቫ ወይንም መሸነፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ እያንዳንዱ ሰው ለመኖር በታላቅ ትግል ላይ ይገኛል፡፡ በመጨረሻ ግን ሁሉም ተሸናፊ ይሆናል፡፡ "ፓቫርጋ" ከሚለው በመጀመሪያው የሚገኘው ቃል ወይንም "ፓ" የሚለው ቃል ፓርቫ ማለት ነው፡፡ ከዚያም "ፕሀ" ማለት ደግሞ "አረፋ" ማውጣት ማለት ነው፡፡ ይህም ልክ እንደ ፈረስ ይመሰላል፡፡ ይህም ፈረስ ከመጠን በላይ ሲሰራ ማለት ነው፡፡ ይህም ፈረስ ከመጠን በላይ ሲሰራ ከአፉ አረፋ ይወጣዋል፡፡ እኛም እንደዚሁ ከመጠን በላይ ሲደክመን ወይንም ከብዙ ስራ በኋላ ምላሳችን መድረቅ ይጀምርና ከአፋችን አረፋ መውጣት ይጀምራል፡፡ እንደዚህም ሁሉ በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ ሁሉም ሰው ከመጠን በላይ ሲሰራ ይገኛል፡፡ በመጨረሻ ግን ሁሉም ተሸናፊ ነው፡፡ "ፓ፡ ፕሀ፡ ባ" ከሚለው መስመር አልፋቤቶች "ባ" የሚለው ቃል ትርጉሙ "መታሰር" ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ "ፓ" ይገኛል፡፡ ከዚያም "ፕሀ" ይገኛል ከዚያም "ባ" የሚለው ቃል መታሰር ማለት ነው፡፡ ከዚያም "ባ፡ ብሀ" የሚሉት ቃላቶች ይገኛሉ፡፡ "ብሀ" ማለት ደግሞ "መመታት" እና በፍራቻ ስር መሆን ማለት ነው፡፡ ከዚያም "ማ" ማለት ደግሞ "ምርትዩ" ወይንም ሞት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ የክርሽና ንቃት ስርዓት "አፓቫርጋ" ይባላል፡፡ "አፓ" ማለት "ምንም" ማለት ነው፡፡ "ፓቫርጋ" ማለት የዚህ የቁሳዊ ዓለም ምልክቶች ናቸው፡፡ ይህ "አፓ" የሚለውን ቃል ከፊቱ ስትጨምሩ ደግሞ "አፓቫርጋ" ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ዜሮ ሆነ ወይንም "ወደመ" ማለት ነው፡፡