AM/Prabhupada 0095 - ስራችን ሁሉ ትሁት ልቦናችንን መስጠትን መሆን ይገባዋል፡፡



Lecture on BG 4.7 -- Bombay, March 27, 1974

ለዚህ ዓለም ተማርከናል፡፡ ለአብዩ ሽሪ ክርሽና ፈጣሪ አምላክ ግን ተማርከን ሙሉ ልቦናችንን አልሰጠንም፡፡ ይህ ነው በሽታችን፡፡ ይህ ነው በሽታችን፡፡ የክርሽና ንቃተ ማህበርም የተቋቋመው ይህንኑን በሽታ ለማጥፋት ነው፡፡ በሽታውን ለማዳን ነው፡፡ ክርሽናም ለዚሁ ዓላማ ምድር ላይ ይመጣል፡፡ እንዲህም ብሏል፡፡ "ያዳ ያዳ ሂ ድሀርማስያ" (ብጊ፡ 4 7) "ድሀርማስያ ግላኒህ" ማለት በሀይማኖት የተበረዘ ነገር ሲኖር ማለት ነው፡፡ የሀይማኖት ዓላማ የተበረዘ ሲሆን፡ ክርሽና እንዲህ ይላል፡ "ታዳትማናም ሽሪጃሚ አሀም" ሌላው ደግሞ፡ "አብህዩታናም አድሀርማስያ" እነዚህ ሁለቱም ተጠቅሰዋል፡፡ ሰዎች ለአብዩ ሽሪ ክርሽና ተማርከው ልቦናቸውን ካልሰጡ፡ የራሳቸው የሆነውን "ክርሽናዎች" ይፈጥራሉ፡፡ በምድር ላይ ብዙ ተንኰለኞች ይገኛሉ፡፡ ለእነዚህም ተንኮለኞች ልቦናችንን መስጠት፡ "አድሀርማስያ" ይባላል፡፡ ድሀርማ ማለት ለአብዩ የመላእክት ጌታ ሽሪ ክርሽና ሙሉ ልቦናችንን መስጠት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ሙሉ ልቦና ለክርሽና ከመስጠት ይልቅ፡ ልቦናችን ለድመቶች፡ ለውሾች፡ ወይንም ለተለያዩ ነገሮች ስንሰጥ እንገኛለን፡፡ ይህም "አድሀርማ" ይባላል፡፡ ክርሽና የሚመጣው፡ የሂንዱ ሀይማኖት ወይንም የእስልምና ሀይማኖት ወይንም የክርስትናን ሀይማኖት ለማቋቋም አይደለም፡፡ የመጣበትም ዓላማ ትክክለኛውን ሀይማኖት ለመመስረት ነው፡፡ ትክክለኛውም ሀይማኖት፡ ተማርከን ሙሉ ልቦናችንን ለትክክለኛው አብዩ ሰው መስጠት ማለት ነው፡፡ ሁሌ ስንማረክ እንገኛለን፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነም አስተያየት አለው፡፡ ለዚህም አስተያየት ተማርኰ ይገኛል፡፡ ይህም ለፖሎቲካ፡ ለህብረተሰብ፡ ለኢኮኖሚ፡ ለሀይማኖት ወይንም ለማናቸው ሀሳብ ሊሆን ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ አስተያየት አለው፡፡ የዚህም አስተያየት መሪም እዚያው ይገኛል፡፡ ታድያ የእኛ ስራ ሁሌ ለዚህ ለመረጥነው አስተያተት መማረክ ነው፡፡ ይህም የመማረክ ባህሪይ ያለ ነው፡፡ ነገር ግን የት መማረክ እንደሚገባን እውቀቱ የለንም፡፡ ይህ ነው ችግሩ፡፡ ይህም የምንማረክለት ወይም ልቦናችን የምንሰጥበት ስህተተኛ ቦታ በመሆኑም፡ መላ ዓለም በብጥብጥ ላይ ሁኖ ይገኛል፡፡ ተማርከን ልቦናችንንም የምንሰጥበት ቦታ ሁሉ ሲቀያየርም እናየዋለን፡፡ "ከአሁን በኋላ የኮንግሬስ ፓርቲ አንፈልግም፡፡ አሁን የምንፈልገው የኮምዩኒስት ፓርቲ ነው፡፡" ስንል እንገኛለን፡፡ እንደገናም፡ "ኮምኒስት ፓርቲ አንፈልግም፡፡ ይህን ፓርቲ እንመርጣለን" ስንል እንገኛለን፡፡ ታድያ ፓርቲውን ሁሌ መቀያየር ምን ፋይዳ አለው? ይህን ፓርቲ፡ ያንን ፓርቲ እንላለን እንጂ፡ ለአብዩ የመላእክት ጌታ ልቦናችንን ስንሰጥ አንታይም፡፡ ሙሉ ልቦናችንንም ለአብዩ ሽሪ ክርሽና እስከምንሰጥ ድረስ፡ በዓለም ላይ ምንም አይነት ሰላም ሊኖረን አይችልም፡፡ ይህ ነው መልእክቱ፡፡ ከመጥበሻው ወደ እሳቱ መዝለል ምንም ሊያድነን የሚችል ነገር የለም፡፡ ሰለዚህም አብዩ ክርሽና በብሀገቨድ ጊታ የመጨረሻው ትእዛዝ እንዲህ ይል ነበር፡፡ ”ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ አሀም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሻዪሽያሚ“ (ብጊ፡ 18 66) የሀይማኖት የመበረዝ ትርጉም፡ በሽሪማድ ብሀገቨታም ተገልጾልናል፡፡ ”ሳ ቫይ ፑምሳም ፓሮ ድሃርሞህ“ አንደኛ ደረጃ ወይንም የላቀው ድሀርማ፡፡ ፓራህ ማለት የላቀው ማለት ነው፡፡ ወይንም መንፈሳዊ፡ ”ሳ ቮይ ፑምሳም ፓሮ ድሃርሞ ያቶ ብሀክቲር አድሆክሳጄ" (ሽብ፡1 2 6) ለአድሆክሳጃ (መንፈሳዊ) ሙሉ ልቦናችንን ስንሰጥም፡ አድሆክሳጃ ማለት የላቀ መንፈስ ወይንም ክርሽና ማለት ነው፡፡ የክርሽና ሌላው ስሙ “አድሆክሳጃ” ነው፡፡ “አሆይቱኪ አፕርቲሃታ” “አሆይቱኪ” ማለት ያለ ምንም ምክንያት ወይንም መነሻ ማለት ነው፡፡ “ክርሽና እንዲህ ነው በዚህም ምክንያት ሙሉ ልቦናዬን እሰጣለሁ” በማለት አይደለም፡፡ ልቦናችንን መስጠት ያለብንም ያለ ምንም ድርድር ሳይሆን ነው፡፡ “አሆይቱኪ አፕራቲሀታ” ሙሉ ልቦናችንን ስነሰጥም የሚያደናቅፍ ነገር አይኖርም፡፡ ሙሉ ለሙሉ ልቦናችንን ለክርሽና ስንሰጥም፡ ፈተና ወይንም እንቅፋት ሊኖረን አይችልም፡፡ በማናቸውም ደረጃ ላይ ብንሆንም ልናደርገው የምንችለው ነገር ነው፡፡ “አሆይቱኪ አፕራቲሃታ ያያትማ ሱፕራሲዳቲ“ በዚህም መንገድ፡ "አትማ” ወይም ነፍሳችን፡ ሀሳባችን፡ ገላችን ሁሉ የረካ ይሆናል፡፡ ይህ ነው ስርዓቱ፡፡