AM/Prabhupada 0096 - ማጥናት የሚገባን ብሀገቨታ ከሆነው ሰው ነው፡፡
Lecture on BG 13.4 -- Miami, February 27, 1975
እንዲህ እያልኩም አስባለሁ:”እኔ አሜሪካን:ህንዳዊ:ህንድ: እስላም:ንኝ" እላለሁ:በልቤ ውስጥም ቡዙ አለማዊ ቆሻሻ ነገሮች አሉ: ልቦሃችንን ማፅዳት አለብን:”ህርዲ አንታሃ ስትሃህ አብሃድራኒ“ ቆሻሻ ነገሮች ሁሉ በልቦናዬ ይገኛሉ:ይህንንም ልቦና ካጸዳነው:ከዚህ ሁሉ አለማዊ ሹመቶች ነፃ እንሆናለን: ”ናስታ ፕራዬሹ አብሃድሬሹ ኒትያም ብሃጋቫታ ሴቫያ“ (ሽብ1 2 18) ናስታ ፕራዬሹ:እነዚህ ቆሻሻ ነገሮች ከልቦናችን ሊጠፉ የሚችሉት:በየግዜው ሽሪማድ ብሃገቨታም እና ብሃገቨድ ጊታ በመስማት ነው: ”ኒትያም ብሃገቨት“ ብሃገቨት ማለትም:የመፅሀፍ ብሃገቨት እና የሰው ብሃገቨት ማለት ነው: የሰው ብሃገቨት መንፈሳዊ አባት ማለት ነው: ወይንም ሌላ በክብሩ ከፍ ያለ መንፈሳዊ:እርሱም ብሃጋቫታ ይባላል:ማሃ ብሃገቨት ወይንም ብሃገቨት: ስለዚህም ”ብሃጋቫታ ሴቫያ“ ማለት:ብሃገቨድ ጊታ እና ብሃገቨታምን ማንበን ብቻ ሳይሆን: ከሰው ብሃጋቫትም ትምህርት መውሰድ አለብን:ይህ ያስፈልጋል: ቼይታንያ ማሃፕራብሁም እንዲህ መክሮናል:”ባሃጋቫታ ፓራ ጊያ ብሃጋቫታ ስትሃኔ“ ስለ ብሃጋቫታ መማር ከፈለጋችሁ:ወደ ብሃጋቫታ ወደ ሆነ ሰው መሄድ አለባችሁ:እርሱም በመንፈሳዊነት ንቁ የሆነ ነው: ባለ ሙያ ነኝ ባይ ሰው ጋ ግን አይሆንም:እርሱም ስለማይረዳችሁ ነው: ባለሙያ ነኝ ባዮች ግን:”ቤተ መቅደስ ሂጄ:ወይንም ወደ ቤተ ክርስቲያን:ከዚያም ከሲኦል መንገድ ላያድኑን ይችላሉ“ ማድረግ ያለብንም: በመንፈሳዊነት ንቁ ከሆነ ከብሃገቫታ ሰው ጋር መቅረብ እና ትምህርትን መውሰድ ነው: ይህንንም የብሃገቫታ ትምህርት ከእርሱ መስማት አለብን: እርሱም የክርሽና ተወካይ ነው:ክርሽና እንዲህ አለ:”ታት ሳማሴና ሜ ስርኑ” ሜ ስርኑ “ወይ ከእኔ ስሙ ወይም ደግሞ ከእኔ ተወካይ:በዚህም ጥቅም ልታገኙ ትችላላችሁ” እነዚህም ቅርንጫፎች የተቋቋሙት:ለሰው ልጆች ከስቃይ እንዲወጡ እድል ለመስጠት ነው: ለዚህ ህይወታችን ብቻ ሳይሆን:ለወደፊቱም ህይወታችን ነው: “ኤይ ሩፔ ብራህማንዳ ብህራሚቴ ኮና ብሃግያቫን ጂቭ ጉሩ ክርሽና ክርፓያ ፓይ ብሃክቲ ላታ ቢጅ” (ቼቻ 19 151) ስለዚህም ይህ የእኛ ሃላፊነት ነው:ይህንን ሃላፊነት ከክርሽና ወስደናል: ክርሽና እራሱ ለማስተማር ይመጣል:ሽሪማድ ብሃገቨታምን ትቶልን እንደሄደ ሁሉ: ከዚያም ድቮቲዎቹን ለህዝብ እንዲሰብኩ እና እንዲያስተምሩ ወክሏቸው ይሄዳል: ይህን ነው እኛም ለማድረግ ጥረት ላይ ያለነው:የፈለሰፍነው ነገር የለም:ወይንም የራሳችን የሆነ ነገር የለም: እቃዎች እና ንብረቶች ይኖራሉ:ነገር ግን እንደ ተወካይ ማከፋፈያ ጣቢያችን ነው: ምንም ችግርም የለንም: ብሃገቫድ ጊታንም እንደአለ ብናቀርብ እና የክርሽናን ትእዛዞች ብናስተምር የእኛም ተግባር ተከናወነ ማለት ነው: አዲስ የምንፈጥረውም ነገር አይኖርም:ለመፍጠርም ሃይል የለንም: በአለም ላይ ብዙ አዲስ ሃሳብ የሚፈጥሩ አሉ:አዲስ ፊሎሶፊ:እና የማይረባ ባሳብ የሚያቀርቡ አሉ: ይህ ምንም አይረዳም:ትክክለኛውን እውቀት መውሰድ ይሻላል: