AM/Prabhupada 0098 - በክርሽና መተማመን ያስፈልጋችኋል፡፡ ምንም ዓይነት እጥረት የለም፡፡



The Nectar of Devotion -- Vrndavana, November 11, 1972

"ማደን ሞሃን" ማደን ማለት የወሲብ ፍላጎት ማለት ነው፡፡ "ማደን" የወሲብ ፍላጎት የሚያሳድርብን ክዩፒድ የተባለው መልአክ ሲሆን ክርሽና ደግሞ "ማደን ሞሃን" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህም ማለት አንድ ሰው የክርሽና ፍቅር ጉጉት ካለው ለወሲብ ፍላጎት ግድ ሊሰጠው አይችልም፡፡ ፈተናውም ይኀው ነው፡፡ "ማዳን" በዚህ ቁሳዊ ዓለም ውስጥ የሁሉን ፍላጎት እየሳበ ይገኛል፡፡ እያንዳንዱም ሰው በወሲብ ፍላጎት ተስቦ ወይንም ተመስጦ ይገኛል፡፡ ይህም መላው የቁሳዊ ዓለም የሚንቀሳቀስበት መሰረቱ በወሲብ ሕይወት አማካኝነት ነው፡፡ "ያን ማይቲሁናዲ ግርሀሜዲ ሱክሀም ሂ ቱቻም" (SB 7.9.45) በዚህ ዓለም ላይ የሚገኘው ደስታ ወይንም ደስታ ተብሎ የሚታወቀው "ማይትሁና ማይትሁናዲ" ነው፡፡ ማይትሁናዲ ማለትም በዚህ ዓለም ውስጥ ደስታ የሚጀምረው ከማይትሁና ወይንም ከወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ ባጠቃላይ ለመናገር ሕብረተሰቡ ወይንም አንድ ሰው ሊያገባ ይችላል፡፡ የትዳር አንደኛ አላማውም የወሲብ ፍላጎትን ለማርካት ነው፡፡ ከዚያም ልጆች ይወለዳሉ፡፡ ከዚህም በኋላ ልጆች በወላጆቻቸው ስር ሲያድጉ ይታያሉ፡፡ ከዚያም ልጃገረዷ ለሌላ ወንድ ስትዳር ወንዱም ልጅ እንዲሁ ለሌላ ልጃገረድ ይዳራል። የዚህም ትዳራቸው አንዱ ዓላማ የወሲብ ግንኙነት ነው፡፡ ከዚያም የልጅ ልጆች ይወለዳሉ፡፡ በዚህም መንገድ ይኅው የዓለማዊው ደስታ ለዘመናት ሲቀጥል ይታያል፡፡ ይህም "ሽሪያይሽቫራያ ፕራጄፕሳቫሀ" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ እንደተወያየነውም "ሽሪ" ማለት ውበት ማለት ሲሆን "አይሽቫራያ" ማለት ደግሞ ሀብት ማለት ነው፡፡ "ፕራጃ" ማለት ደግሞ ትውልድ ማለት ነው፡፡ ባጠቃላይ የሲህ ዓለም ሰዎች ይህ ዓይነቱ ኑሮ ያስደስታቸዋል፡፡ ጥሩ ቤተሰብ መያዝ፣ ጥሩ የባንክ ሀብት መያዝ፣ ጥሩ ሚስት መያዝ፣ ጥሩ ልጅ መያዝ፣ ጥሩ የወንድም ልጅ ወይንም የእህት ልጅ መያዝ ይመኛሉ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አንድ ቤተሰብ ቆንጆ ሴቶች እና ሀብት በቤተሰቡ ከያዘ እንዲሁም ብዙ ጥሩ ጥሩ ልጆች ካሉት በሕይወቱ እንደተሳካለት ቤተሰብ ተደርጎ ይታያል፡፡ ባለቤቱም በጣም የተሳካለት ሰው እንደሆነ ተደርጎ ይታያል፡፡ ስለዚህም "ሻስትራ" (ቅዱስ መፃህፍት) እንዲህ ብለው ይጠይቃሉ፡፡ "የሕይወታችን ስኬት ምንድነው?" በዚህ ዓለም ላይ ይህ ስኬት የሚጀምረው በወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ ይኅው ነው፡፡ ከዚያም ይህንኑ ተከታትሎ መያዙ ነው፡፡ እንደተጠቀሰውም "ያን ማይትሁናዲ ግርሀሜዲ ሱክሀም ሂ ቱቻም" (SB 7.9.45) በዚህ ዓለም ላይ ደስታ የሚባለው የሚጀምረው ከወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ "ማይትሁናዲ" በተለያየ መንገድ አሳምረነው እንቀርብ ይሆናል፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ይኅው "ማይትሁና" ነው፡፡ ይህም ለደስታ የሚደረግ የወሲብ ግኑኝነት ነው፡፡ ይህም ዓይነቱ የደስታ ጉጉት በአሳማዎችም የሚገኝ ነው፡፡ አሳማዎች እዚህም እዚያም እየተንቀሳቀሱ ሙሉ ቀን ሲበሉ ይታያሉ፡፡ "ሰገራው የት ነው?" "ሰገራው የት ነው የሚገኘው?" ከዚያም ምንም ዓይነት ልዩነት ሳያደረጉ ከሴቶች አሳማዎች ጋር የወሲብ ግኑኝነት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ አሳማዎች እናት፣ እህት ወይንም ሴት ልጄ በማለት ልዩነት አያደርጉም፡፡ ስለዚህ "ሻስትራ" ወይንም ቅዱስ መፃህፍት እንዲህ በማለት ያሳውቁናል፡፡ "በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ በእንደዚህ ዓይነት ኑሮ ተወሳስበን እንገኛለን፡፡" በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስጥ የተጠመድነውም በወሲብ ፍላጎታችን አማካኝነት ነው፡፡ ይህንንም እንድናደርግ የሚገፋፋን ክዩፒድ ነው፡፡ ክዩፒድ የወሲብ ሕይወት አምላክ ነው፡፡ ማደን ተብሎም ይታወቃል፡፡ አንድ ሰው በማደን ወይንም ክዩፒድ ካልተገፋፋ በስተቀር የጋለ የወሲብ ግኑኝነት ፍላጎት ሊኖረው አይችልም፡፡ የሽሪ ክርሽና ስም ደግሞ "ማደን ሞሃን" ነው፡፡ "ማደን ሞሀን" ማለት ደግሞ ለወሲብ ግኑኝነት ያለውን ፍላጎት እርግፍ አድርጎ ትቶ ፍላጎቱ ወደ ክርሽና ያመዘነ ማለት ነው፡፡ ይህ ነው ፈተናው፡፡ በዚህም ምክንያት የሽሪ ክርሽና ስም "ማደን ሞሀን" ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ነው ማደን ሞሀን ማለት፡፡ ሳናታን ጎስዋሚ "ማደን ሞሀን" የተባለ የክርሽና ሙርቲ ነበረው፡፡ ማደን ወንም ማአደን የተባሉ ቃሎች አሉ፡፡ ማአደን ማለት እብድ ማለት ሲሆን ማደን ማለት ደግሞ ክዩፒድ ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በወሲብ ፍላጎት ሀይል ሲጎተት ይታያል፡፡ ይህም በየቦታው የሚታይ ነው፡፡ በሽሪማድ ብሀገቨታም ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠቅሶ ይታያል፡፡ "ፑምሳህ ስትሪያ ሚትሁኒ ብሀቫም ኤታት ታዮር ሚትሆ ህርዳያ ግራንትሂም አሁር" መላ የቁሳዊው ዓለም በዚህ መንገድ ሲንቀሳቀስ ይታያል፡፡ ወንድ ልጅ በሴት ልጅ ጉጉት ሲንቀሳቀስ ይታያል፡፡ ሴትም ልጅ እንዲሁ በወንድ ልጅ ጉጉት ስትንቀሳቀስ ትታያለች፡፡ በዚም በወሲብ አማካኝነት ከተገናኙም በኋላ ለዚህ ዓለም ያላቸው ፍቅር ከፍ ከፍ እያለ ሲመጣ ይታያል፡፡ በዚህም መንገድ ከተገናኙም በኋላ ወይም አንድ ወንድ እና ሴት ትዳር ከመሰረቱም በኋላ ቆንጆ ቤት ለማያዝ ጥረት ያደረጋሉ፡፡ ይህም "ግሪሀ ሼትራ" እንቅስቃሴ ይባላል፡፡ ከዚያም ንግድ፣ ፋብሪካ ወይንም እርሻ ለማቋቋም ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ይህም ምክንያቱ ገቢ ማግኘት ስለሚያስፈልግ ነው፡፡ ምግብም አስፈላጊ ነው፡፡ "ግሪሀ ሼትራ" ሱታ ወይንም ልጆች፣ አብታ ወይንም ጓደኞች፣ ቪታ ወይንም ሀብት "አታሀ ግሪሃ ሼትራ ሱታፕታ ቪታዬር ጃናስያ ሞሆ ያም" (SB 5.5.8)— በእነዚህም ሁሉ ነገሮች ጉጉት ለቁሳዊው ዓለም ያለን ፍላጎት እየጨመረ ይመጣል፡፡ ይህም ማዳን ወይንም ለማደን ያለን ጉጉት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የሕይወታችን ዓላማ ለዚህ ዓለም ብልጭልጭ ነገሮች መጓጓት አይደለም ፡፡ ጉጉት እንዲያድርብን የሚገባው ግን ለሽሪ ክርሽና ፍቅር ነው፡፡ ለዚህም የክርሽና ንቃተ ማህበሩ እንቅስቃሴ ዋናው ዓላማ ነው፡፡ በሽሪ ክርሽና ቁንጅና በጉጉት የተመሰጥን ካልሆንን ጉጉታችን ወደዚህ ቁሳዊ ዓለሙ የሀሰት ቁንጅና የሚያደላ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ባህታዊው ያሙና አቻርያ እንዲህ ብሎ ጠቅሶ ነበር፡፡ "ያደቫድሂ ማማ ቼታሀ ክርሽና ፓዳራቪንዳዮር ናቫ ናቫ ድሃማ ራንቱም አሲት" "በሽሪ ክርሽና ቁንጅና መሰመጥ ከጀመርኩ ግዜ ጀምሮ ይህንን የሎተስ አበባ የመሰለውን የሽሪ ክርሽና እግር ማገልገል ጀምሬአለሁ፡፡" ከዚያም ግዜ ጀምሮ በየግዜው የሚታደስ ሀይል እያገኘሁ እገኛለሁ፡፡ በዚህም ግዜ ውስጥ ስለ ወሲብ ባስታወስኩ ግዜ በሀሳቡ ላይ ለመትፋት እቃጣለሁ፡፡ ይህም "ቪትርስና" ይባላል፡፡ ይህም ማለት ለዚሁ ጉጉት የሌለው ማለት ነው፡፡ የዚህ ቁሳዊ ዓለም ማእከላዊው የደስታ ምንጭ የወሲብ ፍላጎት ነው፡፡ አንድ ሰው የዚህን የወሲብ ፍላጎት የሚቆጣጠር ወይንም እርግፍ አድርጎ የሚተው ከሆነ "ታዳቫድሂ ማማ ቼታህ" ያዳቫድሂ ማማ ቼታህ ክርሽና ፓዳራቪንዳዮር ናቫ ናቫ (ራሳ) ድሀም (አኑድያታ) ራንቱም አሲት ታዳቫድሂ ባታ ናሪ ሳንጋሜ ስማርያማኔ ባሀቫቲ ሙክሀ ቪካራሀ ሱስቱ ኒስትሂቫናም ቻ "የወሲብ ግኑኝነትን ባስታወስኩኝ ቁጥር ወዲያውኑ አፌ ዝግጁ ይሆን እና በላዩ ላይ ለመትፋት እቃጣለሁ፡፡" ስለዚህ ሽሪ ክርሽና ማደን ሞሃን ተብሎ ይታወቃል፡፡ ማዳን ወይንም የወሲብ ፍላጎት ሁሉን ሲጎትት ይታያል፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው በክርሽና ፍቅር የተመሰጠ ከሆነ ማዳንን ሊሸነፍ ይችላል፡፡ በዚህም መንገድ ማደንን ለማሸነፍ የምንበቃ ከሆንን መላ የቁሳዊ ዓለምን አሸነፍን ማለት ነው፡፡ አለበለዛ ግን መንፈሳዊ ሕይወታችን ግብ ለማድረስ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡