AM/Prabhupada 0099 - እንዴት በክርሽና ለመታወቅ እንደምትችሉ፡፡



Lecture on BG 13.4 -- Bombay, September 27, 1973

በዚህ አለም ላይ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ሰዎች አሉ:ምንም እንኳን ብዙዎቹ እንድ ሙምባይ አይነት ወይንም ሌላ ከተማ ውስጥ ቢኖሩም: እንደዚሁም ሁሉ: ሁሉም ነዋሪ ፍጥረታት በአንድ አይነት ደረጃ: የሚገኙ አይደሉም: አንዳንዶቹ “በአለማዊ ጥሩ ባህርይ” የተመሰጡ ናቸው (በጎ አድራጎት): አንዳንዶቹ ደግም “በአለማዊ የቅብዝብዝነት ባህርይ” የተመሰጡ ናቸው አንዳንዶቹ ደግሞ “በአለማዊ የድንቁርና ባህርይ” የተመሰጡ ናቸው: እነዚህም በድርቁርና ባህርይ የተመሰጡ:ልክ ውሃ ውስጥ እንደወደቁ: የእሳት ፍንጣቂዎች ናቸው: የእሳት ፍንጣቂ ልክ ውሀ ላይ እንደወደቀ:እራሱ ወዲያውኑ ይጠፋል: የደረቀው ሳር ላይ ደግሞ:ይኅው የእሳት ፍንጣቂ ቢወድቅበት:የደረቀውን ሳር ተጠቅሞ: እሳት ይለኮስ እና እንደ ገና እሳት ይሆናል: እንደዚሁም ሁሉ:በጥሩ ባህርይ አንደበት የሚገኙ ሰዎች:የክርሽና ንቃታቸውን በቀላሉ ሊቀሰቅሱት ይችላሉ: ምክንያቱም በብሃገቨድ ጊታ እንዲህ ብሎ ተጠቅሷል:“ዬሻም ትቭ አንታ ጋታም ፓፓም” ለምንድን ነው ብዙ ሰዎች ወደ ቤተ መቅደስ የማይሄዱት? ምክንያቱም አንዳንዱ ሰው ባልታረመ ድንቁርና ውስጥ ስለሚገኝ ነው: “ናማም ዱስክሪቲኖ ሙድሃህ ፕራፓድያንቴ ናራድሃማህ (ብጊ7 15) እነዚህም ለመምጣት ፍላጎቱ የላቸውም:በሃጥያታዊ ስራዎች የተሰማሩ ሰዎች:የክርሽናን ንቃት ሊያወድሱ አይችሉም: ይህ የማይሆን ነው:ነገር ግን እድሉ ለሁሉም ተሰጥቷል: እኛም እያቆላመጥናቸው እንገኛለን ”እባክህ ና:እባካችሁ“ ክርሽናን ወክለን የምንሰራው ስራ ይህ ይሆናል ማለት ነው: ልክ ክርሽና እዚህ አለም ላይ ብሃገቨድ ጊታን ለማስተማር: መጥቶ እንደጠየቀን ሁሉ: ”ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጃ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ“ (ብጊ18 66)(ሙሉ ልቦናህን ስጠኝ) ክርሽናም ይህንን በጣም ያመሰግነዋል ”እነዚህ አገልጋዮች በእኔ ተወካይነት እያስተማሩ ነው“ ”እዚያ ለማስተማር ባልሄድም:እነርሱ ስራዬን እየሰሩልኝ ነው:“ ምን አይነት ስራ ላይ ነው የተሰማራነው?ሰዎችን ”እባካችሁ ለክርሽና ልቦናችሁን ስጡ“:ብቻ ነው የምንለው: ስለዚህም ለክርሽና ተወዳጅ ሁነን እንገኛለን:ክርሽናም እንዲህ ብሏል:”ናቻ ታስማን ማኑስዬሱ ካሽቺን ሜ ፕሪያ ክርታማህ (ብጊ18 69) ስራችን ሁሉ እንዴት በክርሽና ታዋቂነትን እንደምናገኝ ነው: አንድ ሰው ወደ ክርሽና ንቃትም ተመለሰ ወይንም አለተመለሰም ግድ አይሰጠንም: ስራችን ማቆላመጥ ነው:ይኅው ነው:“የእኔ ጌታ:እባክህ ወደ እዚህ ና:የክርሽናንም ደይቲ ቀረብ ብለህ እየው” “ስገድለትም እና የሚበላ ፕራሳድም: ቤት ከመሄድህ በፊት ውሰድ” ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች እሺ አይሉም:ለምን? ይህ ሰራ በሃጥያት ባህርይ በሞላባቸው ሰዎች ሊወሰድ አይችልም: ስለዚህም ክርሽና እንደዚህ ብሏል:“ዬሻም ትቭ አንታ ጋታም ፓፓም” ከሀጥያቱ ነፃ የሆነ ሰው: “ዬሻም ትቭ አንታ ጋታም ፓፓም ጃናናም ፑንያ ካርማናም” ማነው ከሀጥያት ነፃ ሊሆን የሚችለው?እርሱም በመንፈሳዊ ግልጋሎት ውስጥ የሚገኘው ሰው ነው: በመንፈሳዊ አገልግሎት ሁሌ የተሳተፈ:እንዴት ወደ ሃጥያተኛ መንገድ ሊወድቅ ይችላል? ስለዚህም ዋናው የመንፈሳዊ ስራችን የሃሬ ክርሽናን ቅዱስ ስም ሁል ግዜ መዘመር ነው: ሁል ግዜ ቅዱስ ስሙን ከዘመራችሁ:”ሃሬ ክርሽና:ሃሬ ክርሽና:ክርሽና ክርሽና “ እንደዚሁም በክርሽና ንቃት አእምሮዋችሁ ሁሌ ከተሞላ: በዚህ ሁኔታ:ሌላ የተበከለ አስተሳሰብ ወደ አእምሮዋችሁ ሊገባ አየችልም:ይህ ነው የክርሽና ንቃት ሥርአቱ: ክርሽናን ልክ እንደረሳነውም ግን:የማያ ወጥመድ ወዲያውኑ ትይዘናለች: