AM/Prabhupada 0103 - ከትሁት አገልጋዮች ማህበር ርቃችሁ ለመሄድ እንዳትሞክሩ፡፡

From Vanipedia


Never Try to Go Away From the Society of Devotees - Prabhupāda 0103


Lecture on CC Adi-lila 7.91-2 -- Vrndavana, March 13, 1974

መንፈሳዊው ናሮታማ ዳስ ታኩር እንዲህ አለ፡ “ከትውልድ እስከ ትውልድ” ምክንያቱም የክርሽና ንጹህ አገልጋይ፡ ወደ መንፈሳዊ አለም ወደ ጌታ ቤት ለመመለስ ትኩረት የለውም፡፡ ነገርግን ምኞቱ፡ በተገኘው ቦታ ሁኖ አምላክን ማወደስ ብቻ ነው፡፡ አምላክን ባለበት ቦታ ሁኖ ማመሰገን ብቻ ነው ምኞቱ፡፡ ይህ ነው የንጹህ አገልጋይ ባህሪይ፡፡ ንጹህ አገልጋይ አምላክ ፊት የሚዘምረው እና የሚያወድሰው፡ ወይንም የፍቅር አገልግሎቱን የሚያበረክተው፡ ወደ ቫይኩንታ ወይንም ወደ ጎሎካ ቭሪንዳቫና ለመሄድ ሰለፈለገ አይደለም፡፡ ይህም የክርሽና ምኞት ነው፡፡ ክርሽና ከተመኘ አገልጋዩን ወደ መንፈሳዊው አለም ሊወስደው ይችላል፡፡ ብሃክቲቪኖድ ታኩርም እንዲህ ብሎ ተናግሯል፡፡ “ኢቻያ ያዲ ቶራ” “ጃንማኦቢ ያዲ ሞሬ ኢቻ ያዲ ቶራ ብሃክታ ግርሄቴ ጃንማ ሃ ኡፓ ሞራ” የንጹህ አገልጋይ ፀሎት፡ እንዲህ ነው፡ ክርሽናን እንዲህ ብሎ እንኳን አይለምንም፡ “እባክህ ወደ ቫይኩንታ ወይንም ወደ ጎሎካ ቭሪንዳቫና ውሰደኝ” ብሎ አይለምንም፡፡ አገልጋይ ጸሎቱ እንዲህ ነው፡ “እንደገና ተወለድ የምትለኝም ከሆነ፡ በደስታ እቀበለዋለሁ” “ነገር ግን፡ የምጠይቅህ ነገር ቢኖር ግን፡ በንጹህ የአንተ አገልጋዮች ቤት ውስጥ እንድወለድ አድርገኝ” “ይኅው ነው ምኞቴ፡፡ ይህም አንተን እንዳልዘነጋ እና እንዳገለግል ይረዳኛል” የንጹህ አገልጋይም ፀሎት ይኅው ነው፡፡ ለምሳሌ ይህችን ልጅ እይዋት፡፡ የተወለደችው፡ ከቫይሽናቫ የክርሽና አገልጋይ አባት እና እናት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው፡ ከዚህ ትውልድ በፊት ቫይሽናቫ አገልጋይ እንደነበረች ነው፡፡ ይህም ትውልድ ለማገልገል እድል የሚሰጥ ነው፡፡ ልጆቻችን ሁሉ እና ከቫይሽናቫ እናት እና አባት የተወለዱ ሁሉ፡ በጣም እድለኞች ናቸው፡፡ ልጆቹም ህይወታቸውን ከጀመሩ ጀምሮ፡ የሀሬ ክርሽናን ዝማሬ ለመስማት እድል አግኝተዋል፡፡ ከቫይሽናቫዎችም ጋር፡ እየዘመሩ እና እየደነሱ ይገኛሉ፡፡ በእርግጥም ሆነ በማሰመሰል ቢዘምሩም ችግር የለውም፡ እድለኞች መሆናቸው ግን የተረጋገጠ ነው፡፡ “ሱቺናም ስሪማታም ጌሄ ዮጋ ብራስታህ ሳንጃያቴ” (ብጊ 6 41) ስለዚህ ተራ ልጆች አይደሉም፡፡ እነዚህም ልጆች ከአገልጋዮች ማሃከል ለመሆን ነው ምኞታቸው፡፡ ሀሬ ክርሽና በመዘመር እና ወደ እዚህ ቤተ መቅደስ በመምጣት ግዜያቸውን ለመጠቀም ይሻሉ፡፡ ስለዚህ ተራ ልጆች አይደሉም፡፡ “ብሃክቲ ሳንጌ ቫስ” ይህ እድል በጣም ጥሩ ነው፡፡ “ብሃክታ ሳንጌ ቫስ” እንደዚሁም ሁሉ የክርሽና ንቃተ ማህበራችን፡ ይህንኑ “ብሃክታ ሳንጋ” የሚያቀርብ ነው፡፡ (የአገለጋዮችን ህብረተሰብ የሚያፈራ) ከዚህም ህብረተሰብ በፍጹም በፍጹም ለመራቅ እንዳትሞክሩ፡፡ አንዳንድ ግዜ ስህተቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እያስተካከላችሁ መኖር አለባችሁ፡፡ ይህም ከአገልጋዮች ጋር በህብረት ሁኖ፡ መዘመር እና ማወደስ፡ ትልቅ በረከት አለው፡፡ ይህም በቅዱስ መፃህፍት የተደጎመ ነው፡፡ በቫይሽናቫዎችም የተደገፈ ነው፡፡ “ታንዴራ ቻራና ሴቪ ብሃክታ ሳኔ ቫስ፡ ጃናሜ ጃናሜ ሞራ ኤይ አብሂላስ” “ጃናሜ ጃናሜ ሞራ” ማለት፡ ለመሄድ ጉጉት የለውም ማለት ነው፡፡ ይህ አይደለም ምኞቱ፡፡ ክርሽና እንድመለስ ሲሻ እመለሳለሁ ብሎ ያሰባል፡፡ አለበለዛ ግን እንዲሁ እየዘመርኩ እና አማላክን እያወደስኩ፡ ባለሁበት ፀንቼ፡ ልቀጥል ብሎ ይመኛል፡፡ ይህም፡ ህይወቱን ከአገልጋዮች ጋር በህብረት እየዘመረ እና እያወደሰ በመኖር ነው፡፡ ይህ ነው የሚያሰፈልገው እና የሚጠበቅብን፡ ሌላ ምንም አያሰፈልግም፡፡ ከዚህ ሌላ ውጪ የሆነ ፍላጎት ሁሉ፡ “አንያብሂላሳ” ይባላል፡፡ “አንያብሂላሳ ሱንያም” (ብሰ 1 1 11) አገልጋር ከዚህ ውጪ ሌላ ነገር መመኘት አይገባውም፡፡ ምኞቱም ሁሉ፡ እንዲህ መሆን አለበት፡ “ሁሌ ከአገልጋዮች ህብረት ማሀከል ሁኜ፡ የአምላክን ሀሬ ክርሽና መሃ ማንትራ (አብዩ ፀሎት)መዘመር እና ማወደስ እሻለሁ፡፡” ይህ ነው ህይዋታችን፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡