AM/Prabhupada 0102 - የሀሳባችን ፍጥነት፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search
Go-previous.png የቀድሞው ገፅ - ቪድዮ 0101
የሚቀጥለው ገፅ - ቪዲዮ 0103 Go-next.png

የሀሳባችን ፍጥነት፡፡
- Prabhupāda 0102


Lecture on SB 5.5.1-8 -- Stockholm, September 8, 1973

በአሁኑ ግዜ አይሮፕላኖች አሉን፡፡ ይህም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ቢሆንም ግን በእነዚህ አይሮፕላኖች ወደ ሌሎች ፕላኔቶች ለመጓዝ አንችልም፡፡ ለምሳሌ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ለመሄድ የምትፈልጉ ከሆነ ከሀሳባችን በላይ ፍጥነት ያለው አይሮፕላን እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡ ወይንም እንደ አየር ፍጥነት ያለው ሊሆን ይችላል፡፡ የፊዚክስ ምሁራን የሆኑት ሁሉ የአየር እና የብርሀን ፍጥነት ምን ያህል እንደሆነ በትክክል ተረድተውታል፡፡ ከእነዚህ ፍጥነቶች በላይ የሆነው ደግሞ የሀሳብ ፍጥነት ነው፡፡ የፊዚክስ ምሁራን የአየር እና የብርሀን ፍጥነት ምን ያህል እንደሆነ በትክክል ተረድተውታል፡፡ ሆኖም ግን የሀሳባችን ፍጥነት ከእነዚህ ሁሉ በላይ ነው፡፡ ለዚሁም ልምዱ አለን፡፡ ለምሳሌ አሁን እዚህ ተቀምጣችኋል፡፡ ቢሆንም ግን በሴኮንድ ውስጥ ሀሳባችሁ ወደ አሜሪካ ወይንም ወደ ሕንድ አገር ለመሄድ ይችላል፡፡ ወይንም ወደ ቤታችሁ ለመሄድ ትችላላችሁ፡፡ በሀሳባችሁም ውስጥ የምታሰላስሉትን ለማየት ትችላላችሁ፡፡ ይህም የሚቀርብልን ሀሳባችን በሚያመጣው ፍጥነት ነው፡፡ ብራህማ ሰሚታ በተባለው የቬዲክ ስነፅሁፍ ውስጥ እንደተጠቀሰው ምንም እንኳን እንደ ሀሳብ ፍጥነት ያለው አይሮፕላን ብንፈለስፍ እንኳን ወይንም እንደ አየር ፍጥረት ያለው ቢሆንም "ፓንትሀስ ቱ ኮቲ ሻታ ቫትሳራ ሳምፕራጋምያሀ" በዚህም ፍጥነት ለሚሊዮን አመታት ብንጓዝም እንኳን ዞሮ ዞሮ ጎሎካ ቭርንዳቫን ተብሎ የሚታወቀውን የዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ ዓለም ልንደርስበት አንችልም፡፡ በዚህ ፍጥነት እንኳን ሊደረስበት አይቻልም፡፡ "ፓንትሀስ ቱ ኮቲ ሻታ ቫትሳራ ሳምፕራጋምዮ ቫዮር አትሀፒ ማናሶ ሙኒ ፑንጋቫናም" (ብሰ 5 34) ከዚህ ቀደም የነበሩት መምህራኖቻችን ወይንም የቀድሞው የቬዲክ ህብረተሰብ ሰለዚህ እውቀት አልነበራቸውም ማለት አይደለም፡፡ ይህም ማለት ስለ አይሮፕላን ወይንም ስለዚህ ዓይነት ፍጥነት ወይም እንዴት አይሮፕላንን ለማሽከርከር እውቀት አልነበራቸውም ማለት አይደለም፡፡ ይህንን ዓይነት ፍጥነት ያላቸውን አይሮፕላኖች በአሁኑ ግዜ ፈጥረዋል ብላችሁም በሞኝነት እንዳታስቡ፡፡ በአሁኑ ግዜ የተፈጠሩትም ሊወዳደሩ አይችሉም፡፡ በሶስተኛ፣ በአረተኛ ወይንም በአስረኛ ደረጃ እንኳን ሊቆጠሩ አይችሉም፡፡ በቀድሞ ግዜ በጣም የሚያማምሩ አይሮፕላኖች ነበሩ፡፡ አሁን ለምሳሌ እንደ ሀሳብ ፍጥነት ያለው አይሮፕላን ፍጠሩ እንበል፡፡ ይህን ዓይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን ፍጠሩ እንበል፡፡ እንደ ዓየር ፍጥነት ያለው አይሮፕላን ግን ለመፍጠር ይቻል ይሆናል፡፡ በአሁኑ ግዜ እንደ ብርሀን ፍጥነት ያለው አንድ እንኳን አይሮፕላን ለመስራት እየታሰበ ነው፡፡ ይህም ቢፈጠር እንኳን በቁሳዊው ዓለም ውስጥ ወደሚገኘው ከፍተኛው ፕላኔት በዚህ ዓይነት ፍጥነት ለመሄድ እንኳን እስከ 40,000 ዓመታት ሊፈጅ ይችላል፡፡ ሳይንቲስቶች ግን ይህ የሚቻል ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ቢሆንም ግን እስከ እስካሁን ግዜ ድረስ እንዳየነው ምንም እንኳን ከቡሎን ጋር ትግል የሚያደርጉ ቢሆንም በዚህ በደካማ አእምሮ እንዲህ ዓይነት ረቂቅ የሆነ ስራ ለመስራት አይቻልም፡፡ ይህንንም ለመፍጠር የተለየ ዓይነት አእምሮ ያስፈልገናል፡፡ ዮጊዎች ወደ እነዚህ ዓይነት ፕላኔቶች ለመሄድ ይችላሉ፡፡ ይህም ልክ እንደ ዱርቫሳ ሙኒ ነው፡፡ እርሱም በቀጥታ ወደ ቫይኩንታ የዓብዩ ጌታ መንፈሳዊ ዓለም ለመሄድ ቻለ፡፡ እዚያም በመሄድ ዓብዩ ጌታ ቪሽኑን ለማየት በቃ፡፡ ይህንንም ለማድረግ የበቃው ምህረት እንዲደረግለት ነው፡፡ ምክንያቱም በአደረገው ጥፋት በጌታ ቪሽኑ የመግደያ "ቻክራ" በመሳደድ ላይ በመሆኑ ነበረ፡፡ ይህም ጥፋት የዓብዩ ጌታን ታላቅ አገልጋይ ቫይሽናቫ በንቀት በመበደሉ ነው፡፡ ይህም የተለየ ታሪክ አለው፡፡ ይህንንም በመሰለ መንገድ የሰው ልጅም ሕይወት ዓላማ ወደ ዓብዩ ጌታ ቪሽኑ መንፈሳዊ ዓለም መመለስ ነው፡፡ ይህም የሚከሰተው ዓብዩ ጌታን በትክክል ስንረዳው እና ሀይሉኑ ስንገነዘበው ነው፡፡ ቀድሞ የነበረንንም ግኑኝነት እንደገና ለመቀስቀስ መቻል ነው፡፡ የሰው ልጅ ትክክለኛው ስራ ይህ መሆን አለበት፡፡ ሆኖም ግን የሚያሳዝን ሆኖ ግዜያችን ሁሉ በፋክተሪ ውስጥ እና በተለያዩ ግዜ የሚያብክኑ ስራዎች ስናጠፋ እንገኛለን፡፡ እንደ አሳማ እና እንደ ውሾች የሰው ልጅ ብርቅ ግዜያችን ሁሉ ሲባክን ይታያል፡፡ ግዜ ማባከን ብቻም ሳይሆን አንደበታችን ሁሉ ትግል በተሞላበት ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ ይህንንም ያህል በስራ ላይ ከደከሙም በኋላ ወደ መጠጥ እና ስካር ያመራሉ፡፡ አልኮል ከጠጡም ሀኋላ ስጋ ወደ መብላት ያመራሉ፡፡ ከዚህም ሁሉ በኋላ ወደ ዝሙት ያመራሉ፡፡ በዚህም ዓይነት እንቅስቃሴ ላይ በመሰማራት በድንቁርና ውስጥ ተመስጠው ይገኛሉ፡፡ በዚህም ጥቅስ በርሻብሀዴቭ እንደተገለፀው ወደዚህ ዓይነቱ ድንቁርና ውስጥ እንዳንገባ እያስጠነቀቀን ይገኛል፡፡ መልእክቱንም የሚያስተላልፈው ለልጆቹ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ይህ ለኛም ትምህርት ይሆነናል፡፡ በጥቅሱ እንዲህም ተናግሯል፡፡"ናያም ዴሆ ዴሃ ብሀጃም ንርሎኬ ካስታን ካማን አርሀቴ ቪድ ብሁጃም ዬ" (SB 5.5.1) "ካማን" ማለት ለሕይወት አስፈላጊ ነገሮች ማለት ነው፡፡ ለሕይወት የሚያስፈልጉን ነገሮችን ሁሉ በቀላሉ ለማግኘት እንችላለን፡፡ ይህም መሬትን በማረስ እህልን ለማፍራት እንችላለን፡፡ ላሞችንም የምናረባ ከሆነ ወተት ለማግኘት እንችላለን፡፡ ይኅው ነው፡፡ ይህም በቂ ነው፡፡ ቢሆንም ግን መሪዎቻችን የተለየ ፕላን እያደረጉልን ነው፡፡ ሕብረተሰቡ በእርሻ ብቻ ደስተኛ ከሆነ ይህም በትንሽ ጥራጥሬ እና ወተት ደስተኛ ከሆነ ማን ወደ ፋክተሪ በመሄድ ስራውን ይሰራልናል ብለው ያስባሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ሕብረተሰቡ ቀለል ያለ ኑሮ እንዳይኖር ታክስ ያስከፍሉታል፡፡ ይህ ነው ሁኔታው፡፡ ምንም እንኳን ቀለል ያለ ኑሮ ለመኖር ብንሻም በአሁኑ ወቅት የሚገኙት መሪዎች ሲፈቅዱልን አይታዩም፡፡ ልክ እንደ ውሾች፣ አሳማ እና አህያ ለመስራት ተገደን እንገኛለን፡፡ ይህ ነው ያለንበት ሁኔታ፡፡