AM/Prabhupada 0105 - ይህንን ሳይንስ ለመረዳት የሚቻለው የፓራምፓራ የድቁና ስርዓትን በመከተል ነው፡፡



Lecture on BG 18.67 -- Ahmedabad, December 10, 1972

ድቮቲ:ሽሪላ ፕራብሁፓድ:አንድ ሰው እንዲህ ጠይቆ ነበር:“ከአንተ በኋላ ማን ነው ይህን እንቅስቃሴ የሚመራው?" ፕራብሁፓድ:ማነው የሚጠይቀው?እራሱ ያደርገዋላ!(ሳቅ) ህንዳዊ እንግዳ:እነዚህን ጥሩ ድቮቲዎች እቅድህን ወደ ፊት እንዲገፉ መጠየቅ እችላለሁን? “እንቅስቃሴህን ወደ ፊት እንዲገፉ:ይህንንም ከብሃክቲቬዳንታ ፕራብሁ በኋላ” ”መሰላሉን ከፍ አድርገው እንዲይዙ:ሃሬ ክርሽና:ሃሬ ክርሽና:“ ፕራብሁፓዳ:ይህ በብሃገቨድ ጊታ: ተገልጿል: ”ኢማም ቪቫስቫቴ ዮጋም ፕሮክታቫን አሃም አቭያያም ቪቫስቫን ማናቬ ፕራሃ ማኑር ኢክስቫካቬ ብራቪት“ (ብጊ4 1) በመጀመሪያ ግዜ:ክርሽና ይህንን የክርሽና ንቃት ሳይንስ:ለፀሀይ አምላክ አስተማረ: የፀሀይ አምላክ ቪቫሽቫን ደግሞ: ይህንን ሳይንስ ለልጁ ለማኑ አስተማረ: ማኑም እንዲሁ ለልጁ ለኢክስቫኩ አስተማረው: ”ኤቫም ፓራምፓራ ፕራፕታም ኢማም ራጃርሳዮ ቪድሁ:“(ብጊ 4 2) እንደዚሁም ሁሉ ይህ ሳይንስ የተላለፈው:ይህን በመሰለ ተያይዞ በመጣ ክትትል ነው: ልክ እኛም ከጉሩ ማሃራጅ መንፈሳዊ መምህራችን እንደተረዳነው: የእኔም ተማሪዎች ተረድተውን ይህን እንቅስቃሴ ወደ ፊት ሊገፉት ይችላሉ: ይህ ነው ሂደቱ:ይህም አዲስ ነገር አይደለም: ፊትም የነበረ ነው:እኛ ግን በትክክል መልእክቱን ማስተላለፍ አለብን: ልክ ከፊታችን እንደነበሩት: እንደ አርአያዊ መምህሮቻችን: ስለዚህም በብሃገቨድ ጊታ እንዲህ ብሎ ተነግሯል:”አቻርያም ኡፓሳናም“ ”አንድ ሰው አርአያዊ መምህርን መቅረብ አለበት“ ”አቻርያ ፑሩሾ ቬዳ“ ዝም ብሎ በመገመት እና:ምሁራን ነን ብሎ ትእቢተኛ መሆን:አያዛልቀንም: ይህም አይቻልም:አንድ ሰው አርአያ ያለውን መመህር መቅረብ አለበት: አርአያ ያለውም መምህር የሚመጣው:ከዚሁ ከፓራምፓራ ተያይዞ እና ተከታትሎ ከመጣ ትምህርት አሰጣጥ ነው: ስለዚህም ክርሽና ይህን ይመክረናል:”ታድ ቪድሂ ፕራኒፓቴና ፓሪፕራሽኔና ሴቫያ“ (ብጊ4 34) አንድ ሰው አቻርያን መቅረብ እና ”ፕራኒፓትን“ መረዳት አለበት:(ሙሉ ልቦና ስለመስጠት) ይህ ሁሉ ስርአት ከልቦና ከመስጠት ጋር የተያያዘ ነው:“ዬ ያትሃ ማም ፕራፓድያንቴ” ክርሽናን እንድንረዳው ሊወስን የሚችለው:የልቦና የመስጠት ሂደታችን:እና: የምንሰጠውም የልቦና መጠን:ነው: ሙሉ ልቦናችንን ከሰጠን:ክርሽናን በሙሉ ልናውቀው እንችላለን: ነገርግን ግማሽ ልቦናችንን ከሰጠን:ክርሽናንም ልናውቀው የምንችለው በግማሹ ነው: ስለዚህ “ዬያትሃ ማም ፕራፓድያንቴ” የልቦና የመስጠቱ መጠን ይወስናል: ሙሉ ልቦና የሰጠው:ይህን ፍልስፍና ለመረዳት ይችላል: በክርሽና ምርቃትም:ሊሰብክ እና ሊያስተምርም ይችላል: