AM/Prabhupada 0106 - የትሁት አገልግሎትን ሊፍት በመጠቀም ወደ ክርሽና በቀጥታ ሂዱ፡፡



Lecture on BG 18.67 -- Ahmedabad, December 10, 1972

“ማማ ቫርትማኑ ቫርታንቴ” ማለት: ለምሳሌ:በአሜሪካ ውስጥ ብዙ ረጃጅም ህንፃዎች ይገኛሉ: በቅርብ ግዜ የሰማነውም:105 ፎቅ ነው: ወደ ከፍተኛው ፎቅ ለመሄድም ደረጃ ይኖራል: ለምሳሌ ሁሉም ሰው ደረጃ ለመውጣት እየሞከረ ነው እንበል:አንዳንዶቹ 10 ደረጃ አልፈዋል እንበል: ሌሎች 50 ደረጃ እንዲሁም ሌሎች 100 ደረጃ:አልፈዋል እንበል: 200 ደረጃም መጨረስ አለባቸው እንበል: ደረጃዎቹ ተመሳሳይ ናቸው:“ማማ ቫርትማኑ ቫርታንቴ” አላማውም ወደ ከፍተኛው ፎቅ ለመድረስ ነው: እንዲሁም 10 ደረጃ የወጣው ሰው:50 ደረጃ ከወጣው ዝቅተኛ ነው: 50 ደረጃ የወጣው ደግሞ:100 ደረጃ ከወጣው ዝቅተኛ ነው: ቢሆንም እንኳን:የተለያዩ የዓላማ ሥርአቶች አሉ:ሁሉም የዓላማ ሥርአቶች አንድ አይደሉም: መንፈሰ ንቁ የሆኑ ሁሉ:አምላክን ለመቅረብ አላማቸው አንድ ነው:ይህም በሥርአተ ካርማ:ግናና:ዮጋ:ብሃክቲ:ለመቅረብ ነው:ነገር ግን ከፍተኛው ሥርአት “ብሃክቲ” ነው:(አምላክን በፍቅር ማገልገል) የብሃክቲም መድረክ ላይ ስትወጡ:ክርሽናን ለመረዳት ትችላላችሁ: በካርማ:በግያና:በዮጋ ሳይሆን: ትሞክራላችሁ:ወደ መድረሻችሁም ለመድረስ ትሞክራላችሁ: ክርሽና ግን እንዲህ አለ:“ብሃክትያ ማም አብሂጃናቲ (ብጊ18 55)(በብሃክቲ ብቻ) በግያና:በካርማ:በዮጋ:አይለንም: በዚህ መንገድ ወይንም ሥርአት ክርሽናን ልትረዱት አትችሉም ወይንም ወደ ፊት ልትራመዱ አትችሉም: ክርሽናን ለመረዳት ከፈለጋችሁ ግን:በብሃክቲ ነው: ”ብሃክትያ ማም አብሂጃናቲ ያቫን ያሽ ቻስሚ ታትቫታሃ“ (ብጊ18 55) ይህ ነው ስርአቱ:ስለዚህ እንዲህ ተብሏል:”ማማ ቫርትማኑ ቫርታንቴ“ ክርሽናም እንዲህ አለ: "ሁሉም ወደ እኔ:እንደ አቅሙ እና እንደ ችሎታው ለመምጣት ይሞክራል“ ”ነገርግን እኔን በትክክል ሊረዳኝ የሚፈልግ:የቀላሉን የብሃክቲን ሥርአት ይከተላል“ ልክ እንደ ደረጃው:በአሜሪካ እና በዩሮፕ: በጎን እና በጎን ሊፍት እና ደረጃዎችን እናገኛለን: ደረጃውንም ላይ ድረስ ከመውሰድ:ሊፍቱን መውሰድ ትችላላችሁ: እንደዚሁም በቶሎ መድረስ ትችላላችሁ: እንደዚሁም የብሃክቲን ሊፍት ብትወስዱ:ወዲያውኑ ከክርሽና ጋር መገናኘት ትችላላችሁ: ደረጃ በደረጃ ከመሄድ ማለት ነው:ለምን ብላችሁ? ስለዚህ ክርሽና እንዲህ ይላል:”ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ“ (ብጊ18 66) ”ለእኔ ብቻ ሙሉ ልቦናችሁን ስጡኝ እና ሌላውን ሃላፊነታችሁን እኔ እጨርስላችኋለሁ“ ለምን ብላችሁ ደረጃ በደረጃ መታገል አለባችሁ?