AM/Prabhupada 0109 - ሰነፍ የሆነ ሰው አንቀበልም፡፡
Lecture on SB 1.7.24 -- Vrndavana, September 21, 1976
ስራችሁን በጥሩ ሁኔታ እያካሄዳችሁ ነው፡፡ የእናንተ "ድሀርማ" ወይንም ሀይማኖት ማለት የተመደበላችሁን እና የሚጠበቅባችሁም ስራ እና ሀላፊነት መወጣት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ኢንጂኔር ነህ እንበል፡፡ ስራህን በደንብ እየሰራህ ሊሆን ይችላል፡፡ የህክምና ባለሙያ፣ የንግድ ሰው ወይንም ማናቸውም ሙያ ሊኖሯችሁ ይችላል፡፡ ይህንንም በመሰለ ሙያ እያንዳንዱ ሰው በስራ ላይ መሰማራት ይገባዋል፡፡ እንዲሁ ያለ ስራ በመቀመጥ የእለት እንጀራችንን ለማግኘት አንችልም፡፡ ምንም እንኳን አንበሳ ብንሆንም ስራ መስራት ግዳጃችን ነው፡፡ "ና ሂ ሱፕታስያ ሲምሀስያ ፕራቪሻንቲ ሙክሄ ምርጋህ" ይህ ቁሳዊ ዓለም ወይንም ተፈጥሮ ይህንን የመሰለ ሕግ ይዞ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን እንደ አንበሳ በጣም ሀይለኛ ብንሆንም ያለስራ መተኛት ብቻ አንችልም፡፡ "እኔ አንበሳ ነኝ እኔ የጫካው ንጉስ ነኝ" ብለን እናስብ ይሆናል፡፡ ስለዚህም እንስሶቹ ወደ እኔ በመምጣት ወደ አፌ ይገባሉ ለማለት አንችልም፡፡ ይህ የማይቻል ነገር ነው፡፡ የዱር እንስሶች ሌሎች እንስሶችን አድኖ መብላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህም ስርዓት ብቻል የእለት ምግባቸውን ለማግኘት ይችላሉ፡፡ አለበለዛ ግን እንስሶቹ ለመራብ ይበቃሉ፡፡ ስለዚህም ክርሽና እንዲህ ብሏል፡፡ "ኒያታም ኩሩ ካርማ ትቫም ካርማ ግያዮ ሂ አካርማናህ፡፡" የተመደበላችሁን ስራ መስራት ይገባችኋል፡፡ "ሻሪራ ያትራፒ ቻ ቴ ና ፕራሲድህዬድ አካርማናህ" እንዲህም ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ "የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ሰዎች ስራ እንሳይሰሩ ያስተምራል" ይህ የክርሽና ትእዛዝ አይደለም፡፡ እኛም ስንፍና የተሞላበትን ሰው አንቀበልም፡፡ ሁሉም በስራ ላይ መሰማራት ይጠበቅበታል፡፡ የክርሽና ንቃተ ማህበር እንቅስቃሴ ማለትም ይኅው ነው፡፡ የሽሪ ክርሽና ትእዛዝም ይኅው ነው፡፡ "ኒያታም ኩሩ ካርማ" አርጁና በጦር ሜዳው ላይ አልዋጋም ብሎ ነበር፡፡ ልክ እንደ እልኅኛ ተዋጊ እራሱን ለማቅረብ አልፈለገም ነው፡፡ ሽሪ ክርሽና ግን ይህንን አልፈቀደለትም፡፡ "ከመዋጋት መሸሽ አይገባህም፡፡ ከሸሸህማ ይህ ደካማ ወገንህ ነው፡፡" "ኩታስ ትቫ ካሽማላም ኢዳም ቪሳሜ ሳሙፓስቲሂታም" ከጦር ሜዳ በመሸሽም እራስህን እንዳልሰለጠነ ሰው እያስቆጠርክ ነው፡፡ "አናንያ ጁስታም" እንዲህ ዓይነቱም አስተሳሰብ "ለአናርያዎች" ወይንም ላልሰለጠኑ ሰዎች ነው፡፡ ስለዚህም ከጦር ሜዳው አትሽሽ፡፡ ክርሽናም እንዲህ በማለት ይመክረው ነበር፡፡ ስለዚህ በክርሽና ንቃተ ማህበር ውስጥ የሚኖሩም ሁሉ ወይንም በክርሽና ንቃት የዳበሩ ሁሉ በስንፍና የተሞላባቸው እና የሀሪዳስ ታኩርን በጎ ተግባር የሚያስመስሉ ብቻ ናቸው ብላችሁ እንዳታስቡ፡፡ እንዲህ ዓይነቱም ስንፍና በክርሽና ንቃት ውስጥ አይገኝም፡፡ የክርሽና ንቃት ማለትም ሽሪ ክርሽና እንዳዘዘው ለሀያ አራት ሰዓት ግዜውን በአግባቡ በስራ ላይ ማዋል ማለት ነው፡፡ ይህም የክርሽና ንቃት ነው፡፡ በስንፍና መጠቃት፣ መብላት እና መተኛት ብቻ አይኖርብንም፡፡ ይህም ማለት "ድሀርማስያ ግላኒህ" አስተያየታችንን መቀየር ይገባናል፡፡ በዚህ በቁሳዊ ዓለም ውስን ኑሮ ውስጥ እያለን ዓላማችን ሁሉ ስሜታችንን ለማርካት ነው፡፡ ክርሽና ንቃት ማለት ደግሞ በዚሁ መንፈስ በስራ ላይ በደንብ መሰማራት ሲሆን ዓላማው ግን ስሜቶቻችንን ለማርካት ሳይሆን የሽሪ ክርሽናን ስሜት ማርካት ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ ህይወት ማለትም ይኅው ነው፡፡ በስንፍና መቀመጥ ማለት አይደለም፡፡ የሁለቱም ልዩነት በደራሲው ክርሽና ዳስ ተገልፆልናል፡፡ "አትሜንድሪያ ፕርቲ ቫንቻ ታሬ ባሊ ካማ" (CC Adi 4.165) "ካማ" ማለት ምን ማለት ነው? ካማ ማለት የግል ስሜቱን ለማርካት ጥረት የሚያደርግ ማለት ነው፡፡ ካማ ማለት ይኅው ነው፡፡ “ክርሽኔድሪያ ፕሪቲ ኢቻ ድሀሬ ፕሬማ ናማ” ፕሬማ ማለትስ ምን ማለት ነው? "ፕሬማ“ ማለት ደግሞ የሽሪ ክርሽናን ስሜት ለማስደሰት የምናደርገው ጥረት ማለት ነው፡፡ ጎፒዎቹ በጣም የገነነ ዝና ያላቸው ለምንድነው? ይህም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ የክርሽናን ስሜት ለማስደሰት ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ቼታንያ መሀብራብሁ እንዲህ ብሎ መመሪያ ሰጥቶናል፡፡ ”ራምያ ካቺድ ኡፓሳና ቭራጃ ቫድሁ ቫርጌና ያ ካልፒታ“ ከዚህም የተለየ ሌላ ስራ አልነበራቸውም፡፡ ”ቭርንዳቫና“ ማለት በቭርንዳቫና ውስጥ ያሉ ማለት ነው፡፡ በቭርንዳቫና ውስጥ ለመኖር የተፈለጉ ከሆነ ስራቸውም ሁሉ ሽሪ ክርሽናን ማስደሰት መሆን አለበት፡፡ የቭርንዳቫን ሕይወት ማለት ይኅው ነው፡፡ በቭርንዳቫን ውስጥ እየኖሩ የግል ስሜትን ለማስደሰት መኖር አይጠበቅብንም፡፡ የቭርንዳቫን ነዋሪ መንፈስም እንዲህ መሆን አይገባውም፡፡ እንዲ ከሆነው ከእንስሶቹ ኑሮ ተነጥሎ አይታይም፡፡ በቭርንዳቫን ውስጥ ብዙ ዝንጀሮዎች፡ ውሾች እና አሳማዎች ይገኛሉ፡፡ ታድያ እነዚህ እንስሶች የቭርንዳቫንን መንፈስ ይዘው የሚገኙ ይመስላችኋልን? አይደለም፡፡ በቭርንዳቫን ውስጥ እየኖረ ስሜቱን ለማስደሰት የሚጥር ሁሉ በሚቀጥለው ሕይወቱ እንደ ውሻ፣ አሳማ ወይንም ዝንጀሮ ሆኖ ይፈጠራል፡፡ ይህንንም መገንዘብ ይኖርብናል፡፡ ስለዚህ በቭርንዳቫን ውስጥ እየኖሩ ስሜቶቻችንን ለማስደሰት መሰማራት አይኖርብንም፡፡ ይህም ሀጥያት ነው፡፡ ሀላፊነታችንም የሽሪ ክርሽናን ስሜት ብቻ ለማርካት መሆን ይገባዋል፡፡