AM/Prabhupada 0110 - የቀድሞዎቹ አቻርያ መምህሮች አሻንጉሊት ሁኑ፡፡



Morning Walk -- April 19, 1973, Los Angeles

ስቫሩፕ ዳሞዳር:ሽሪማድ ብሃገቨታምን ቢሰሙ:ልቦናቸው ሊቀየር ይችላል:

ፕራብሁፓድ:በእርግጥ:ትላንትና አንዱ: ተማሪዎቻችንን አመስግኖ ነበር: “ይህንን ብሃገቨታም ስለምታቀርቡልን በጣም ለምስጋና ተገደናል” አንዱ እንደዚህ አላለምን? ድቮቲ:አዎን:ትሪፑራሪ እንዲህ ብሎ ነበር:

ፕራብሁፓድ:አዎን ትሪፑራሪ:እንደዛ ብሎ ነበርን? ትሪፑራሪ:አዎን:ሁለት ልጆች አይሮፕላን ማረፊያ:ሁለት ጥንድ የሽሪማድ ብሃገቨታም መጽሃፍቶች ገዝተው ነበረ: ጃያቲርትሃ:ሙሉውን ጥንድ?ስድስት ቮሉዩም: ብሃገቨታሙንም ይዘው በጣም እናመሰግናለን አሉ: ከዚያም ወደ ሎከራቸው ውስጥ:አስቀመጥዋቸው እና:አይሮፓላናቸውን እየጠበቁ እያሉ:በእጃቸው የመጀመሪያውን ካንቶ ያዙ: ፕራብሁፓዳ:አዎን:ማንም ታማኝ እና ትሁት ጥረት ያለው ሰው ለዚህ ለእንቅስቃሴያችን ለምስጋና ይገደዳሉ: እነዚህንም መፃህፍቶች በማከፋፈላችሁ:ለክርሽና ትልቅ አገልግሎት እያበረከታችሁ ነው: ለሁላችንም ክርሽና እንዲህ ብሎናል:“ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅሃ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ” (ብጊ 18 66) ስለዚህ ማነም ይህንን አገልግሎት የሚሰጥ ሰው: “ልቦናውን የሰጠ ሰው” በክርሽና በደንብ አድርጎ የታወቀ ይሆናል: ይህም በብሃገቨድ ጊታ ተጠቅሷል:“ናቻ ታስማን ማኑሽዬሹ (ብጊ 18 69) በሰው ልጅ ህብረተሰብ ውስጥ:ክርሽናን ለማስተማር ከሚያግዘው ሰው በላይ ማንም:ውድ አይሆነውም: ሃሬ ክርሽና: ብራህማናንዳ:እኛ የእናንተ አሻንጉሊት ነን:ሽሪላ

ፕራብሁፓድ:መጽሃፍቶቹን የሰጠህን አንተው ነህ:

ፕራብሁፓድ:አይደለም: እኛ ሁላችንም የክርሽና አሻንጉሊቶች ነን:እኔ ራሴ አሻንጉሊት ነኝ: አሻንጉሊት:ይህ ሲወርድ ሲዋረድ ተያይዞ የመጣ ነው:ሁላችንም አሻንጉሊቶች መሆን አለብን: እኔም የጉሩ ማሀራጄ አሻንጉሊት እንደሆንኩኝ ሁሉ:እናንተም እንደዚሁ ብትሆኑ:ወደፊት መራመድ ትችላላችሁ: የኛ ኑሮ ማሳካት የሚመጣው:ያለፉት መሪዎቻችን አሻንጉሊት ስንሆን ነው: “ታንዴራ ቻራና ሴቪ ባሃክታ ሳኔ ቫስ” በድቮቲዎች ክበብ መሃከል መኖር እና: የቀድሞ አርአያዊ መምህሮቻችን አሻንጉሊት መሆን ነው: ይህ ውጤታማ ያደርገናል:ስለዚህ ይህን ለማድረግ ጥረት ላይ ነን: የክርሽና ንቃተ ማህበረተኛ መሆን እና የቀድሞ መሪዎቻችንን ማገልገል:ይኅው ነው: “ሃሬር ናማ ሃሬር ናማ” (ቼቻ አዲ 17 21) ህብረተሰቡ ወደ እኛ ይመጣል:የእኛንም ትምህርት ያመሰግኑታል:ነገር ግን ጊዜ ይወስዳል: ስቫሩፕ ዳሞዳር:በአሁኑ ግዜ ከሁለት አመቱ በፊት በላይ:እያመሰገኑት ነው ያለው:

ፕራብሁፓድ:አዎን: ስቫሩፓ ዳሞዳር:አሁን ትክክለኛ ፍልስፍና መረዳት ጀምረዋል: