AM/Prabhupada 0129 - በክርሽና መተማመን ያስፈልጋችኋል፡፡ ምንም ዓይነት እጥረት የለም፡፡

From Vanipedia
Jump to: navigation, search

በክርሽና መተማመን ያስፈልጋችኋል፡፡ ምንም ዓይነት እጥረት የለም፡፡ -
Prabhupāda 0129


Lecture on SB 7.6.1 -- Vrndavana, December 2, 1975

ክርሽና እንዲህ ይላል:”ማን ማና ብሃቫ ማድ ብሃክቶ ማድ ማጂ ማም ናማስኩሩ“ (ብጊ 9 34) ይህን እየሰበክን ነው:እዚህ በቤተ መቅደሳችን ለሁሉም እንግዳ “ክርሽና እዚህ ነው” “ሁልግዜም ክርሽናን አስታውስ:ሀሬ ክርሽናንም ዘምር” እንላለን: ከዚያም እንዲህ ማሰብ አለባችሁ:“ሀሬ ክርሽና:ሀሬ ክርሽና” ይህንም መዘመር ክርሽናን ማሰብ ነው ልክ የክርሽናን ስም እንደሰማችሁ:ይህ “ማን ማና” ይባላል: ይህንንስ ማን ያደርገዋል:“ማድ ብሃክታ” የክርሽና ድቮቲም ትሆናላችሁ:ግዜያችሁንም አታባክኑም:“ሀሬ ክርሽና:ሀሬ ክርሽና” ይህም ማለት የሀሬ ክርሽናን ማንትራ በመዘመር ብቻ የክርሽና ድቮቲ መሆን ትችላላችሁ: “ማን ማና ብሃቫ ማድ ብሃክቶ ማድ ያጂ” ድቮቲ የክርሽና ስግደት ለይ ይሰማራል: ሙሉ ቀን እያገለገለ ይገኛል:ሞንገል አራቲ ለክርሽና:ጃፓ መቁጠሪያ ለክርሽና: ምግብ ለክርሽና ማዘጋጀት:የክርሽናን ፕራሳዳም ማቅረብ:እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች ያገለግላል: ድቮቲዎች በአለም ላይ በየአገሩ አሉን:ወደ 102 ቅርንጫፎች አሉን:እነዚህም ሁሉ በክርሽና ንቃት ላይ የተሰማሩ ናቸው: ይህ ነው የእኛ ስብከት:ሌላ ስራ የለንም: ምንም ንግድ የለንም ነገር ግን እስከ 25 ላክ ሩፒስ እናጠፋለን: 25 ላክ ሩፒ በየወሩ:ይህንንም ክርሽና እያቀረበ ነው: “ቴሻም ኒትያ ብሂ ዩክታናም ዮጋ ክሼማም ቫሃሚ አሃም” (ብጊ 9 22) በክርሽና ንቃት የዳበራችሁ እና በክርሽና የምትተማመኑ ከሆነ ምንም የሚጎል ነገር አይኖርም: እኔም ይህን የክርሽና ንቃት ማስፋፋት የጀመርኩት:በ40 ሩፒ ነበር:አሁን ግን 40 ከሮር አለን: ታድያ በዚህ አለም በ40 ሩፒ ተነስቶ:በ10 አመት 40 ከሮር የሚያተርፍ ነጋዴ አለ? ሊኖር አይችልም:በዚህም ላይ:10000 ሰው በቀን በቀን ምግብ እየበላ ይገኛል: ይህም የክርሽና ንቃት ነው:“ዮጋ ክሼማም ቫሃሚ አሃም” (ብጊ 9 22) የክርሽና ንቃትህ እንደዳበረ:በእርሱ ተማምነህ አገልግሎትህን በትጉህነት ቀጥል: ክርሽና ታድያ የሚያስፈልግህን ሁሉ ያቀርብልሃል:ሁሉን ነገር: ይህ በተግባር የታየ ነው: ለምሳሌ:ቦምቤይ ያለው መሬቶች እስከ ከሮር ሩፒ ይጠይቃሉ: እኔ ግን ቅርንጫፋችንን ስገዛ:የነበረኝ ገንዘብ 3 ወይንም 4 ላክ ነበር ብዙ ግምትም አድረገን ነበረ:ቢሆንም ልከፍል እንደምችል እርግጠኛ ነበርኩኝ:ምክንያቱም ክርሽና እንደሚረዳኝ ተማምኜ ነበር: የሚበቃ ገንዘን አልነበረንም:ይህም ረጅም ታሪክ ነው:ለመወያየትም አልሻም: ታድያ እንደዚህም:ተግባራዊ ልምድ አለኝ:በክርሽና ከተተማመንን የሚያጥረን ነገር ሊኖር አይችልም: የተፈለገው ነገር ሊገኝ ይችላል:“ቴሻም ኒትያብሂ ዩክታናም” ስለዚህም በክርሽና ንቃት ሁልግዜ ተሰማሩ: ያላችሁም ፍላጎት ሁሉ ሊሟላላችሁ ይችላል: