AM/Prabhupada 0131 - ለአባት ልቦናን መስጠት በተፈጥሮ ያለ ነገር ነው፡



Lecture on BG 7.11-16 -- New York, October 7, 1966

በዚህ አለም ላይ ያለውን:ይህን እብደት:ይህን ቅዥት:ይህን ምትሃት:ትቶት ለመሄድ በጣም አሰቸጋሪ ነው: በጣም አስቸጋሪ ነው: ክርሽና ግን እንዲህ ይለናል:”ማም ኤቫ ዬ ፕራፓድያንቴ ማያም ኤታም ታራንቲቴ“ (ብጊ 7 14) አንድ ሰው በፍቃዱ ወይንም:የአለምን ስቃይ አይቶ:ወደ ክርሽና ልቦናውን ቢሰጥ: ”ውድ ክርሽና ሆይ:በብዙ በሚቆጠሩ ህይወቶች:ረስቼሃለሁ“ ”አሁን ግን:አባቴ እና ጠባቂዬ እንደሆንክ ተረድቼአለሁ:ልቦናዬንም ሰጥቼሃለሁ“ ብለን ብንፀልይ: ልክ የጠፋ ልጅ ወደ አባቱ እንደተመለሰ: ”አባቴ ሆይ:በድንቁርናዬ:ከአንተ ጥበቃ:ትቼህ ጠፋሁ:ስለዚህም ብዙ ተሰቃየሁ“ ”አሁን ግን ወደ አንተ መጥቼአለሁ“ ብንል:አባት እቅፍ አድርጎ ይቀበለናል:”ውድ ልጄ: እንኳን ተመለስክ:ለዚህም ግዜ ሁሉ እኔ በጣም ሃሳብ ላይ ነበርኩኝ“ “ያንተ መምጣት ደስታችን ነው” እንደዚሁም ሁሉ:አባት ርሁሩህ ነው:እኛም በዚህ ሁኔታ ላይ ነው ያለነው: ልክ ልቦናችንን ለፈጣሪ ጌታ እንደሰጠን: ይህ አስቸጋሪ አይደለም: የልጅ ለአባቱ ልቦናውን መስጠት:ይህ አስቸጋሪ ነውን? አስቸጋሪ ይመስላችኋል? ልጅ ለአባቱ ልቦናውን መስጠት:በተፈጥሮ ያለ ነው: ምንም ዝቅተኛነት የሚሰማ ነገር የለም:ምክንያቱም አባት ሁልግዜ የበላይ ነው: የአባቴን እግር ብነካ:ለአባቴ ብሰግድለት:ይህ የሚመሰገን ነው: ይህም ለእኔ የሚያስመሰግን ነው:ውርደት የለውም:የሚያስቸግር ነገርም የለውም: ለምንድነው ለክርሽና ታድያ መሉ ልቦናችንን የማንሰጠው? ይህ ነው ስርአቱም:”ማም ኤቫ ዬ ፕራፓድያንቴ“ ”እነዚህ ሁሉ ግራ የተጋቡ ነፍሳት:ሙሉ ልቦናቸውን ሲሰጡኝ“ ”ማያም ኤታም ታራንቲቴ“ (ብጊ 7 14) ”በዚህም ግዜ ምንም አይነት መሰቃየት ሊኖርባቸው አይችልም“ በአባቱ ጠለላ ስር ይሆናል ማለት ነው: በብሃገቨድ ጊታም መጨረሻ ላይ:እንዲህ ተጠቅሷል:”አሃም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሻዪስያሚ ማ ሱቻሃ“ (ብጊ 18 66) ህፃን ወደ እናቱ ጡት ሲጠጋ: እናትም ትጠብቀዋለች: አደጋ ቢኖርም:እናት ህይወቷን ከመስጠት አትቆጠብም: እንደዚሁም ሁሉ:በፈጣሪ ጌታ ጠለላ ስር ካለን:ምንም አየት ፍርሃት አይኖረንም: