AM/Prabhupada 0156 - ላስተምራችሁ ጥረት የማደርገው የረሳችሁትን ነው፡፡



Arrival Address -- London, September 11, 1969

ጋዜጠኛ:ለማስተማር የምትሞክረው ትምህርት ምንድን ነው?

ፕራብሁፓዳ:እኔ ለማስተማር የምሞክረው:እናንተ የረሳችሁትን ትምህርት ነው:

ድቮቲዎች:ሀሪ ቦል!ሀሬ ክርሽና!(ሳቅ)

ጋዜጠኛ:የትኛውን:ማለትህ ነው?

ፕራብሁፓድ:ይህም ፈጣሪን ነው: አንዳንዶቻችሁ ፈጣሪ የለም ትላላችሁ:አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ፈጣሪ ሞቷል ትላላችሁ: አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ፈጣሪ ሰብአዊ ባህርይ የለውም ትላላችሁ:ወይንም ባዶ ነው ትላላችሁ: ይህ ሁሉ ስሜት የማይሰጥ ነው: ስለዚህ እነዚህን ስሜት የማይሰጡ ሰዎች ሁሉ:ፈጣሪ እንደ አለ:ለማስተማር ነው የመጣሁት:ይህ ነው የእኔ ሚሽን: ማንም ስሜት የማይሰጥ ሰው ወደ እኔ መምጣት ይችላል:እኔም ፈጣሪ እንደ አለ ማስረጃ አቀርብለታለሁ: ይህ ነው የእኛ የክርሽና ንቃት እንቅስቃሴ: ይህም ፈጣሪ የማያምኑ:ህብረተሰቦችን መቋቋም ነው: ፈጣሪ አለ:እዚህ ፊት ለፊት እንደምንትየያይም ሁሉ:ከፈጣሪ ጋር ፊት ለፊት ለመተያየት እንችላለን: ታታሪ እና ኮስተር ብላችሁ መንፈሳዊ ኑሮ የምትከታተሉ ከሆነ:ፈጣሪን ማየት ይቻላል: ነገር ግን:ፈጣሪን ለመርሳት እየሞከርን ነው:ስለዚህም ብዙ ስቃይ ላይ እየወደቅን እንገኛለን: ስለዚህ እኔም የማስተምረው:ክርሽና ንቃትን ወስዳችሁ:ደስተኛ እንድትሆኑ ብቻ ነው: በዚህ ስሜት በማይሰጥ:የማያ ማእበል:ወይንም ምትሃት:ተጎትትችሁ አትወሰዱ: ይህ ነው የእኔ መጠይቅ:

ድቮቲዎች:ሀሪ ቦል!